የሥራ ቅጥር ቃለ መጠይቅ ላይ ነው አሉ። ፈተኙ የመ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ
እና ቃለ መጠይቅ አድርጊ ኮሚቴ አንድ ገና ከቴክኖሎጂ ፋክሊቲ ተመርቶ የመጣ ፍሬሽ ኢንጂነርን እያነጋገረ ነው። የጽሑፍ ፈተና፣
ሌሎች ሌሎች መስፈርቶችን ሁሉ አሟልቷል። ቀጣሪው ኮሚቴ ሊቀጥሩት ፈልገዋል ስለዚህ ወደ “ገደለው” (ዋናው ቁምነገር) ገቡ።
“እሺ እንደ ጀማሪነትህ ስንት ብንከፍልህ ጥሩ ይመስልሃል?”
“ሌሎች፣ ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች እንደ ተጠበቁ ሆነው ከ 40 ሺ እስከ
50 ሺ በወር አይከፋም እላለሁ። ቅር የሚላችሁ ነገር አለ?”
ቃለ መጠይቅ አድራጊው ኮሚቴ አባላት እርስ በርስ ተያዩ እና “መልካም እንግዲህ በደምዎዙ ተስማምተናል። ጥቅማ ጥቅም ላልከው መ/ቤታችን ሊሰጥህ የሚችለው ጥቅማ ጥቅም በዓመት ሦስት ወር ከሙሉ ደምዎዝህ ጋር ዕረፍት፣ ሙሉ የሕክምና ወጪ፣ ተጨማሪ መሉ
የጥርስ እና የዓይን ሕክምና ወጪህን መሸፈን፣ በዓመት አንድ ጊዜ ወደ ፈልግከው አገር ከቤተሰብህ ጋር ሄደህ ለ12 ቀናት የምትዝናናበትን ሙሉ
ወጪ መሸፈን፣ በየሁለት ዓመቱ የሚቀየር ዘመናዊ መኪና ከናሽናል ሞተርስ ባንተ ምርጫ ተገዝቶ እንዲሰጥህ ማድረግ እንዲሁም ጡረታ ስትወጣ የደምዎዝህን ግማሽ መክፍል ነው እንደ ጥቅማ ጥቅም ልንሰጥህ የምንችለው። ቅር የሚልህ ነገር አለ?”
ኢንጂነሩ ወደ ኋላው ወንበሩ ላይ ለጠጥ አለና “ምን እየቀለዳችሁ ነው
እንዴ . . .?”
የመ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅም “አዎ። ግን ቀልዱን የጀመርከው እኮ አንተው ራስህ
ነህ!”
The original English version of the above joke
Reaching
the end of a job interview, the Human Resources Officer asks a young engineer
fresh out of the Massachusetts Institute of Technology, "And what starting
salary are you looking for?" The engineer replies, "In the region of
$125,000 a year, depending on the benefits package." The interviewer
inquires, "Well, what would you say to a package of five weeks vacation,
14 paid holidays, full medical and dental, company matching retirement fund to
50% of salary, and a company car leased every two years, say, a red
Corvette?" The engineer sits up straight and says, "Wow! Are you
kidding?" The interviewer replies, "Yeah, but you started it."
No comments:
Post a Comment