በሳቅ የሚገድል ገጠመኝ . . .
ይኼን M-Birr የሚሉትን የሞባይል ብር ማስተላለፊያ ተጠቅሜ ለሆነ የማላውቀው ሰው በስህተት 1000 የኢትዮጵያ ብር ላኩለት። . . . አዎ፣ አንድ ቁጥር ብቻ ስለሳትኩ 1000 ብሩ ለሌላ ሰው ፍትልክ ብሎ ሄደ። በምንም ተዓምር ብሬን ማስመለስ እንደማልችል ሲገባኝ፣ ተረጋጋሁና ብሩን የተቀበለው ሰው ወንድ ይሁን ሴት ባላውቅም የሚከተለውን የአጭር ጽሑፍ መልእክት (ኤስ ኤም ኤስ) ላኩለት/ ላኩላት፦
“የተከበሩ አዲስ አባላችን፣ ለሁሉም አዲስ አባል እንደምናደርገው፣ የላክንልዎት ወደ የእኛ የደብረ ሰይጣን ድንግሉ ቤተ አምልኮ የእንኳን ደህና መጡ መልካም ስሜት መግለጫ የሆነውን እጅ መንሻ የኢትዮጵያ 1000 ብር እንደደረስዎት ተስፋ እናደርጋለን። በቤተአምልኳችን ቀኖና ሕግጋት ተገዢ ሆነው ከእርስዎ የሚጠበቅብዎትን ሁሉ እየፈጸሙ ለእምነታችን መለምለም እና መስፋፋት የበኩልዎን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ እምነታችን ከአሁኑ የፀና ነው። ይህ በቅርቡ የሚጀምሩት በሀብት የተትረፈረፈ ጉዞ ማንንም የሚያስቀና ስኬታማ የምድር ሕይወት መጀመሪያው እንጂ መጨረሻው አይደለም። ገና ብዙ ነገር ከእኛ ያገኛሉ። እርስዎ ብቻ በሰይጣን እና በአምልኮተ ሰይጣን ብቻ ይመኑ። ሰይጣን ያድናል። ታላቅ ጌታ ነው! እርስዎ የእኛ አባል በመሆንዎ በእኛ በኩል እንደ ተሰማን ከፍተኛ ደስታ እርስዎም እየተሰማዎት እንደሆነ ከልብ ተስፋ እናደርጋለን። አስቀድሜ እንደገለጽኩልዎት ይኼ የላክንልዎት ብር የእንኳን ደህና መጡ እጅ መንሻ ገጸ በረከት ብቻ ነው። የቅዱስ ሰይጣንን 66ኛ የዓመቱን አዲስ ወር መባቻ ምክንያት በማድርግ በዛሬው ሌሊት ሦስት ኢ-አማኒ ሰዎችን ባርከን በማረድ ወሩን በቅድስና እና በፍጹም ጨዋነት እንጀምራለን። እባክዎ የሚያውቁዋቸውን ለእርስዎ የቅርብ የሆኑ አንስታይ ወዳጆችዎን የቻሉትን ያህል በመጋበዝ ፕሮግራማችን ይበልጥ ድምቀት እንዲኖረው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያድርጉ ይለመናሉ። ፕሮግራሙ ልክ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ላይ በእርስዎ መኖሪያ ቤት ውስጥ ይጀምራል። እንዴት እንደምንመጣ ምንም አያስቡ ራሳችን እንመጣለን።
በእኛ ቤተ አምልኮ አባል ሆነው መቀጠል የማይፈልጉ ከሆነ እና ይህ መልእክት እየደረስዎት ያለው በስህተት ነው ብለው የሚያምኑ ከሆነ እባክዎ የላክንልዎትን ገንዘብ መልሰው በዚህ ስልክ ቁጥር ለማንም ሳይነግሩ ይላኩልን። ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን በቤተ አምልኮዋችን ተልዕኮ እና አገልግሎት ደስተኛ እንደሆኑ ተቆጥሮ ዛሬ ማታ ያዘጋጀነው በዓል በተባለው ሰዓትና የአከባበር ሥነ ሥርዓትና ሁኔታ በእርስዎ ቤት ይከበራል። ማታ እስክንገናኝ ጌታ ሰይጣን ጤና እና ሰላሙን ሁሉ ለእርስዎና ለቤተሰቦችዎ ይስጥልን። ከሰላምታ ጋር፣ መምሬ ምረቱ የደብረ ሰይጣን ድንግሉ ቤተ አምልኮ ኤጲስ ቆጶስ።”
ከአሥር ደቂቃ በኋላ እንዲህ የሚል የአጭር ጽሑፍ መልእክት (ኤስ ኤም ኤስ) ደረሰኝ፦ “የልብ ጓደኛዬን አጫውቸው እሱም አባል መሆን ይፈልጋል። እባካችሁ ሌላ 1000 ብር በዚህ ቁጥር ላኩለት። ስልክ ቁጥር #0911. . .”።
ፌንት ነቀልኩ አይገልጸውም። ኧረ እንዴት ያለ አገር ነው ያለነው ጎበዝ፣ ሰው ሁሉ ቀላል ጠሮበታል እንዴ? . . .
ከሮበርት ሙጋቤ
“LOUGH WITH ME H. E ROBERT MUGABE Quotes”
ከሚለው የ Facebook ገጽ ላይ ተውስዶ
ወደ አማርኛ በአገርኛ አስተኔ የተተረጎመ በብሩክ በየነ
ኦርጂናሉ ጽሑፍ በቴፍሎን ዶን Facebook ላይ የተለጠፈ
Original article posted by Teflon Don on Facebook
CAN'T STOP LAUGHING ....
I mistakenly sent someone
R 1000 through e Wallet...in fact should I say I sent R1000 to
a wrong number.
After realizing this, I calmed down and sent him/her this text
message:
"Hello Dear, I hope you got the membership welcome fee of
R1000 to our Satanism Church. We are glad and looking
forward to having you with us.
That is just the beginning of the richest life you are about to
start living. We hope you are as excited to be joining our
church as we are. As I just said, that is a
welcome salary.
We are having a meeting tonight whereby we will slaughter 3
people in celebration of the start of this month. Please invite
over any female person you may be close to. Lets meet
tonight at 8pm at YOUR PLACE.
If you haven't shown any interest in our church and you
believe this is a mistake, kindly send the money back to this
number otherwise welcome to our Church. See you tonight."
10 Minutes later, I got a message saying send another R1000
my friend is also interested'.
I fainted, people are so broke these days..
No comments:
Post a Comment