Tuesday, January 10, 2017

የቦሌ ሰዎች አጭር ጨዋታ



የቦሌ ሰዎች አጭር ጨዋታ
ሰውዬው ከመሥሪያ ቤት ሆኖ ወደ ቤቱ ይደውላል እና የስምንት ዓመት ሴት ልጁ ስልኩን ታነሳዋለች፦
«ሃይ የኔ ማር፣ አባቢ ነኝ። ማሚ አጠገብሽ አለች?»
«አይ አባቢ የለችም፣ ከአጎቴ ሰይፉ ጋር ላይ ቤት መኝታ ቤት ውስጥ ነች።» ትንሿ ልጅ ፈገግ አለች።
ከትንሽ አፍታ በኋላ አባትየው «ግን ማሬ፣ አጎቴ ሰይፉ የሚባል እኮ የለሽም ! »
« አረ ባቢ አለኝ ! እንዲያውም አሁን ላይ ቤት በመኝታ ቤት ውስጥ ከማሚ ጋር አንድ ላይ ነው። »
አሁንም ትንሽ አፍታ ዕረፍት።
« እሺ እንግዲህ ጥሩ ! አሁን የምታደርጊውን በደንብ አዳምጪኝ። ስልኩን ሳትዘጊ ጠረጴዛው ላይ አስቀምጪ እና ወደ ላይ ቤት ቶሎ በሩጫ ሂጂና የመኝታ ቤቱን በር አንኳኪውና የባቢ መኪና የግቢው በር ላይ ነው ብለሽ ንገሪያቸው። »
« እሺ አባቢ። አንዴ ጠብቀኝ . . .»
ከትንሽ ጊዜ በኋላ ትንሿ ልጅ ተመልሳ መጥታ ስልኩን አነሳቸውና «አባቢ እንዳልከኝ አደረግኩ።»
«እና ምን ተፈጠረ ማሬ ? »
«እንጃ አላወቅኩም። ለምን እንደሆነ እንጃ ብቻ ማሚ በጣም ደነገጠች። ከመኝታ ቤቱ ራቁቷን እየጮኸች በሩጫ ወጣች። ስትሮጥ የሆነ ነገር አደናቀፋትና ደረጃው ላይ ወደታች እየተንከባለለች ወደቀች። ጭንቅላቷን መሬቱ መታት፣ እና አሁንም ምንም አትንቀሳቀስም። »
«አጎቴ ሰይፉስ ? » ሲል ጠየቀ አባትየው ተረጋግቶ።
«እሱ በመስኮት በኩል መዋኘት ፈልጎ ነው መሰለኝ ወደ መዋኛ ገንዳችን ዘለለ፣ ግን አንተ የገንዳውን ውኃ ባለፈው ሳምንት ባዶ እንዳደረግከው አላወቀም መሰለኝ። ሲፈጠፈጥ ሰምቼያለሁ እና የሞተ ይመስለኛል። በጣም ፈርቼያለሁ አባቢ።»
ረዘም ላሉ ሰኮንዶች ዝም ብሎ ከቆየ በኋላ . . .
አባትየው «መዋኛ ገንዳ ? ማሬ የምን መዋኛ ገንዳ ነው የምትይው፣ እኛ መች የመዋኛ ገንዳ አለን ? ይኼ ስልክ ቁጥር 01-6-66588978 አይደለም እንዴ ? »
« አረ 01-6-66588979 ነው። »
« ኦው፣ ተሳስቼ ነው፣ ይቅርታ ! ! ! ? ? ? . . . »
==============================================================================================
A man at work calls home and his 8 years old daughter picks the phone:
“Hi honey,this is daddy.Is mommy near the phone?”
“No daddy she is upstairs in the bedroom with Uncle Paul.” The little girl quipped.
After a brief pause daddy says,“But honey you haven’t got uncle Paul!”
“Oh yes I do,and he is upstairs in the room with mommy right now.”
Brief pause, “Uh okay then, this is what I want you to do: Put the phone down on the table, run upstairs, knock on the bedroom door, and shout to mommy that daddy’s car has just arrived at the gate.”
“Ok daddy just a minute....”
A while later the little girl comes back to the phone, “Done it daddy. ”
"What happened honey?”
“Well, mommy got scared and jumped out of the bed naked,ran round the room screaming, tripped over, and knocked her head on the staircase, now she is not moving at all.”
“What about Uncle Paul?” asked Dad. He jumped out the window into the swimming pool, but I guess he didn’t know you emptied the water last week. He hit the bottom and I think he’s dead.”
After a really long pause this time...
Daddy says, “Swimming pool, but we don't have a swimming pool! Is this 073-8078-495?”
“No, this is 073-8078-459”
“Sorry wrong number....!!!!”

No comments:

Post a Comment