ቀን_____________________________________
በባል እና ሚስት የሚፈረም ሕጋዊ የፕሪሚየር ሊግ ውል
ከዚህ በመቀጠል የተዘረዘሩትን ደንቦች ጥሶ መገኘት በመሃላችን ያለውን ጋብቻ በፍቺ እንዲጠናቀቅ
ሊያደርገው ይችላል!
1ኛ. ከነሐሴ ወር ጀምሮ እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ቴሌቪዥኑ በማናቸውም ጊዜ የእኔ እና የእኔ ብቻ ነው።
2ኛ. ከቲቪው ፊት ለፊት በማናቸውም ጊዜ መተላለፍ ወይም እንደ ጅብራ መገተር በጥብቅ የተከለከለ ነው።
3ኛ. የሚገቡት ግቦች በድጋሚ በዝግታ እንቅስቃሴ መደገማቸው በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ከዚህ በፊት ባያቸው ባላያቸው
ጉዳዬ አይደለም። እንደገና ላያቸው እፈልጋለሁ፣ አራት ነጥብ።
4ኛ. እኔ የምደግፈው ቡድን ሲሸነፍ፣ በጭራሽ እነዚህ ቃላት መጠቀም አይፈቀድም፦
“አይዞህ፣ ደሞ ለኳስ! / መሸነፍ ያለ ነው / ዕድላቸው ነው፣ አንተ ምን ጨነቀህ ወይም አንተ ምን ቤት ነህ?” [ማሳሰቢያ
በተለይ የመጨረሻው አባባል ቤቱን አይደለም ሠፈሩ እንዲፈርስ ጠንቅ ሊሆን ይችላል]
5ኛ. ማናቸውም ፍቅር ነክ እና ሌሎች መሰል ተቀባይነት ያላቸው ወሬዎች ዕረፍት እስከሚወጡ ወይም ጨዋታው ሙሉ በሙሉ
እስከሚጠናቀቅ ድረስ ተራቸውን መጠበቅ አለባቸው።
6ኛ. በፕሪሚየር ሊጉ የውድድር ዘመን የሚያጋጥሙ ማናቸውም ኹነቶች ጨዋታ እንዳያስመልጡ ወይም ጭቅጭቅ እንዳያስነሱ በቅድሚያ
ሊነገሩኝ እና መስማማቴን በጽሑፍ ከፊርማ ጋር ማረጋገጥ አለብኝ። (ሁለት እግር ኳስ አፍቃሪ እማኞች ባሉበት ካልተፈረመ የስምምነት
ሰነዱ ተቀባይነት ላይኖረው ይችላል)
7ኛ. ከጨዋታ ውጭ (ኦፍሳይድ) ምን ማለት እንደሆነ ጥያቄ መጠየቅ አያስፈልግም። ዳኛ ካላየ እኔ ማየት መብቴ ነው፤
የያሁትንም እናገራለሁ። ለዚህ ሆነ ለሌሎች መሰል ጥያቄዎች ጊዜ አይኖረኝም።
8ኛ. የዕለቱን ምርጥ ጨዋታ (ማች ኦፍ ዘ ዴይ) ደግሜ ባየው ለምን ደግሜ እንደማየው ጥያቄ ማቅረብ አያስፈልግም።
9ኛ. መብራት ጠፍቶ ከቤት ወጥቼ ባመሽ ብቸኛ ተጠያቂው መብራቱን እንዲጠፋ ያደረገው አፍራሽ ኃይል ብቻ ነው።
10ኛ. ሕፃናት እና መሰል ባዕድ ድምፅ ፈጣሪዎችን ከአካባቢው እንዲርቁ ባለማድረግ ሊወሰድ በሚችለው እርምጃ ተጠያቂው
በቸልታ ሁከት እንዲፈጠር ያደረገው አካል እንጂ ኳስ ወዳዱ ኳስ ብቻ የሚመለከተው ወገን አይሆንም።
የባል ፊርማ የሚስት ፊርማ
________________________________________ _____________________________
እማኞች
1_____________________________________________
2____________________________________________
No comments:
Post a Comment