ሦስት ሞቅ ጀቴው በዝቶ ጥንብዝ ብለው በስካር
ላዳ ታክሲ ይይዛሉ።
ባለ ላዳው ከአነጋገራቸው በጣም እንደሰከሩ ስለገባው ሞተሩን አስነሣ
በደንብ ካስጮኸው በኋላ እና መልሶ አጠፋው።
“ይኸው ደርሳችኋል ውረዱ” አላቸው።
1ኛው ሰኬ የተስማሙበትን ገንዘብ መዥረጥ አድርጎ
ሰጠው።
2ኛው ደግሞ “አመሰግናለሁ” አለው።
3ኛው ግን በጥፊ አላሰው።
ይኼን ጊዜ ባለ ታክሲው 3ኛው ሰኬ የነቃበት መሰለው።
ምእንተ
ህፍረቱን “ምን ያማትሃል?” ብሎ አፈጠጠ።
3ኛው ሰኬም “ሌላ ጊዜ እንዲህ እነዳለሁ ብለህ እንድትሞክራት።
እንዲህ ምታበረው አይሮፕላን
መሰለህ እንዴ፣ ገድለህን ነበርኮ!”
No comments:
Post a Comment