Friday, March 30, 2018

መሲህ ይመጣል ገና

መሲህ ይመጣል ገና

የያዘ ይዞት ጥላውን ቢሸጠው
ጥላ አይሸጥም'ንጂ ዋለልኝ ማን አለው
የመብራት ልጅ ፋኖስ ማር ነሽ ያሏት
ኃይለመስቀል እንድትሆን ጌጥ ያረጓት
ማር እንደነበር ጌታቸው መች ያኔ ገባቸው
ቼ ብለው ፈረሱን ዘመን ማሰሳቸው
ዓይን ራሱን አለማየቱ መች ያኔ ገባቸው
አይሁድ አላመኑም የጌታን ልጅ አልሰቀሉም
አጭበርባሪውን እንጂ መሲሁን አልነኩም
መሲህ ይመጣል ገና፣ አልቆረጥንም ተስፋ
ሙሴ ይመራናል ሌት ተቀን ሳያንቀላፋ
እያዩ አላዩም ሰምተውም አልሰሙም
ሀብታም ድሀ ቤት በጭራሽ አይገባም


መታሰቢያነቱ ለሁሉም ድሀ ቤት ገብተው ለሞቱ ሀብታሞች

በዕለተ ዑራኤል መጋቢት 2018 (በቊጥር ሲቀለድ)



No comments:

Post a Comment