Tuesday, March 20, 2018

የአእምሮ ህሙማን ሆስፒታል ውስጥ ነኝ

ይድረስ ለሁሉም የኔ ቢጤ ታካሚ በሽተኞች በሙሉ፣

አሁን አሁን እንደገባኝ ከሆነ፣ ውልፍጭ ሳንል አርፈን እንቀመጣለን፣ ስክሪኑ ላይ እናፈጣለን፣ ከራሳችን ጋር እናወራለን፣ ብቻችን እንስቃለን፣ ወዲያው እንከፋለን፣ እንቆጣለን፣ ሸብለል፣ ሸብለል እንደገና ፈገግ እንላለን . . .። የታመሙትን አሜን ብለን እንፈውሳለን። ለቅሶ RIP ብለን እንደርሳለን። የወንጌል ቃሉን እንሰብካለን። ቁራዓንን እናስተምራለን። ማርክሲስም ሌኒኒዝም እናስፋፋለን። ሚካኤል ገብሪኤል እያለን የቀን መቊጠሪያ እንሆናለን። ሲለን ደግሞ ቁጭ ብለን መንግሥት እንሾማለን፣ ቁጭ ብለን መንግሥት እንሽራለን። የምንፈልገውን ሰው ከየትኛውም ዓለም ቢሆን አምጥተን እናናግራለን። የጠላነውን ደግሞ ያለበት ድረስ ሄደን አፈር ድሜ እናበላዋለን። የማናውቃቸውም ጓደኞች፣ ቤተ እንስሳት፣ (የአንበሳ ግቢዎች)፣ ትላልቅ የሚያምሩ እርሻዎች፣ ገራሚ ከተሞች፣ በምድር ላይ ያልተፈጠሩ ጉዶች በአእምሯችን ይመላለሳሉ። ውድ ምግብ ቤቶች ገብተን እንመገባለን፣ የሰው ድስት እንቀላውጣለን። ሳንቲም ጠብ የማያደርግ ቢንጎ፣ ካንዲ ካራሽ ምናምን እንጫወታለን። ያልሆነውን እንሆናለን። በሄድንበት ሁሉ ቪዛችንን ከዚሁ እናገኛለን። ቤተሰብ ፈልጎ እንዳያጣን ዳራችንን እዚህ እንተዋለን። ዕድሜያችንን፣ ጠላታችንን፣ ገዳያችንን ሁሉ እናስጠነቁላለን። ሰውን ከመሬት ተነስተን እንወርፋለን፣ እንደ ልባችን እንሳደባለን እንዲሁም ሆኖ ችግር የለውም ብለን እናስባለን። ግድግዳ ላይ እንደምንጽፍ ያለን ፍጹም እንረሳለን። ያልተጨበጠ ወሬ ይዘን እንጨነቃለን፣ እናራግባለን፣ የለጠፍነውን የወደዱትን የለጠፉትን እንወድላቸዋለን፣ ዝም ያሉንን ዝም እንላቸዋለን፣ የሰደቡንን እስከ ዘር ማንዘር እንሞልጫቸዋለን። ፖስት ያደረግነውን ስንት Like እንዳገኘ በጉጉት እንቆጥራለን፣ ጠላትና ወዳጅ እዚያው እንለያለን . . . ረጋ ብላችሁ አስቡበት እስኪ ብታምኑም ባታሙኑም አብደናል፣ ንቀውናል፣ ጨርቅ ጥለን ቶኬ ሆነናል! Facebook ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን የአእምሮ ህሙማን መታከሚያ ሆስፒታል ነው። እኛም በሆስፒታሉ ውስጥ ያለን አሊያም ተመላላሽ ወይም ተኝቶ ታካሚ በሽተኞች ነን። አራባ አራት ነጥብ። ። ። ። ። ። እኔ ባለሁበት በዚኛው ዋርድ ዛሬ ማታ ታዋቂ ዘፋኝ የሚገኝበት ፓርቲ ስለደገስኩ አደራ እንዳትቀሩ፣ እንጨሳለን ፒሪ ፒሪ ባጫ ቡጫ ዊሂ ዊሂ ዊሂ

ምንጭ፦

1 comment: