Us vs Them
My childhood was not an anxious place,
though I lay
in my bed, awake, thumbing
my sheets
like beads, wondering when the sun
imploded
would Russian astronauts be OK,
they in their
Sputniks, with their space dogs,
they that chased their own tail
around this
water bowl
we call Earth. When I was a child,
in elementary
school
we practiced a type of
protection
called Duck
and Cover,
where we
huddled
under desks in case of a nuclear
attack
by the Russians.
They were communists,
had the bomb, and were evil
Reagan told
us
from the
small grave
of a TV screen.
In the
sixties, Nixon said the same
thing, and the Panthers
countered with "the Viet Cong never
called me
nigger"
With their picks
like
unclenched fists,
with their afros like the plume of an atom
bomb,
they scared
white and black folks alike. It is 2014,
and America
is still scared of
the Russians and black people;
now the American Dream is to be debt
free,
which I am
not, nor may ever be, but at least
I'm no longer afraid of the Russians.
የእኛና የእነሱ ፍጥጫ
በዴቪድ ቶማስ ማርቲኔዝ
ልጅነቴ
አልነበረም አስጨናቂ ቦታ፣
ምንም እንኳ ሳልተኛ ብተኛ
በቁም ባልጋዬ ባንቀላፋ፣ አንሶላዬን
ውስጥ ብንከባለል እንደ ዶቃ፥ ፀሐይ ስትወድቅ
ያኔ ፈንድታ
ይበልጥ ያሳሰበኝ ውስጤን ቀልቤን ገዝቶ
የሩሲያ ጠፈርተኞቹ ምን ይውጣቸው ይሆን ከቶ፣
በስፑትኒካቸው ውስጥ፣ ከነጠፈር ውሻዎቻቸው፣
እኒያ የገዛ ጭራቸውን የሚያሳዱት
እኛ መሬት በምንላት፣ የሚዞሩት
በዚያች የውሃ ጉድጓድ። ልጅ እያለሁ ገና
ጨቅላ፣
በተማሪ ቤት የነበረው ውሪ በሞላ
ዱክ እና ካቨር የተባለ ልምምድ
ስንለማመድ፣
ድንገት ሩሲያዎች በኒውክሊየር ቢያጠቁን፣
ብለን ከዴስክ ሥር ተመራርተን ታጉረን።
እነሱ ኮሚኒስት ናቸው፣
ደሞም ቦምብ አላቸው
በዚያ ላይ አረመኔ፣ ክፉ ናቸው
ከሚጢጢው መቃብር ውስጥ ሆኖ
ከቴሌቭዥኑ መስኮት
ሬገን ነው የነገረን ይኼን እውነት።
በፊትም በስልሳዎቹ፣ ኒክሰን ይህንኑ ብሎ
ነበር
እነዚያ ፓንተር የሚባሉት ሲነሱ “ማንም ቬትናም
ኔግሮ ብሎ ጭራሽ አልሰደበኝም” ሲሉ
እንደ መሃመድ
ዓሊ ቡጢ ሲምዘገዘግ ምርጫቸው
አፍሮዋቸው፣ እንደ አቶም ቦምብ ደመና ሲያደምን በላያቸው ፣
ያስፈሩ ነበር ጥቁርንም ነጩንም ዘር።
አሁን ግን ሃያ አሥራ አራት ነው ዘመን
ሲቆጠር፣
ዛሬም ትፈራለች አሜሪካ፣ የሩስያና ጥቁር
ሰዎችን ፣
ያ ታላቁ የአሜሪካ ሕልም የሚሉትን
ሕልም ነው አሁን፣ ከዕዳ ነጻ የመሆን
እኔም ከዕዳ ነጻ አይደለሁም፣
ወደፊትም አልሆንም፣
ቢያንስ ግን አሁን፣
ሩሲያዎችን
ከእንግዲህ አልፈራቸውም።
ኖቨምበር 15፣ 2016 ተተረጐመ
No comments:
Post a Comment