Tuesday, November 8, 2016

እኩልነት



እኩልነት
ቀልቤ ሲነግረኝ እምቢ አልኩትና
መታረዝ መጠማቴን ችላ አልኩትና
እንደ ዲዮጋን ሰው ፍለጋ ወጣሁና. . .

ግራ ቀኝ ብዳክር ሳልቆርጥ ተስፋ
እንኳን ሰዉ እኔው ራሴ ለራሴ ጠፋ
ለካስ ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ አገሩ በሞላ
ሳናውቀው ተሽጠን ኖሯል እንዳለን በጅምላ

ለመሸጤ እንደ ደረሰኝ የቆረጡልኝ
እያለሁ ላለመኖሬ ያረጋገጡልኝ
መሸጫ ዋጋዬን ነው መሰል
አንተም እኩል ነህ ነው ያሉኝ!

#ብሩክ ዶን ብሩኖ፣ አዲስ አበባ ሐምሌ 22፣ 2008 ዓመተ ኢትዮጵያ

No comments:

Post a Comment