መሥመርና መደመር
መሥመርና መደመር ሁለት ጽንፍ ጎራ
ሒሳብ ሠርቶ እየመጣ ሁሉም በየተራ
ያኛው በጂኦሜትሪ ይኼ በአልጄብራ
መሪ ለመጨበጥ ፥ መርቶ ሺ ሊመራ
የማትስ ተንኮል የሒሳብ ክፋቱ
ከቀማሪ በፊት ቁጥር ማጣፋቱ
አንድ አለኝ ያልኩት ወርዶ እየተጣፋ
የቀየስኩት መሥመር ድንገት እየጠፋ
ደህና ክብ የነበረውን ቤት
ደህና አይደለም ብለውት
ቤቴን ሠርቼ ባራት ባራት ማዕዘን
ሲከፈል ሁለት ሌላ ሦስት ማዘን
ሲቆረጥ ሲሰነጠቅ መሥመር ፥ ሸርፎ ተሸራርፎ
ባቡር መንገድ ተኛ ያገር ሰው፥ እጅ እግሩን ሸክፎ
ዓይኑን ጨፍኖ አስሮ አንጀቱንም አጥፎ
ደሞ ይኼኛው ስባዝን ጎዳና ላይ አግኝቶኝ
መሥመር መንገድ ነው አያልቅም ብሎኝ
አራት ሒሳብ ቤት ባንዴ ተፊቴ ተገልጦ
በቁጥር ሲታይ ፥ ታየኝ ከሁሉ በልጦ
ግን የረሳሁት ለዘመናት ጎዳና መቆሜ
ሒሳብ አይገባኝም በየትኛው አቅሜ
ባዶና አንድ ዐዲስ ዓለም እንደፈጠሩ
የሁለቶሽ ባይናሪ ለሁሉ ከሠራ ቀመሩ
መሥመርና መደመር ይፍጠሩ አዲስ ቀመር
አይደምሰስ አይነካ የተሠመረ መሥመር
አይቀነስ አይጥፋ አለኝ ያሉት ቁጥር
ሒሳብ ያልገባው በሰላም እንዲኖር
ሒሳብ ሠርቶ እየመጣ ሁሉም በየተራ
ያኛው በጂኦሜትሪ ይኼ በአልጄብራ
መሪ ለመጨበጥ ፥ መርቶ ሺ ሊመራ
የማትስ ተንኮል የሒሳብ ክፋቱ
ከቀማሪ በፊት ቁጥር ማጣፋቱ
አንድ አለኝ ያልኩት ወርዶ እየተጣፋ
የቀየስኩት መሥመር ድንገት እየጠፋ
ደህና ክብ የነበረውን ቤት
ደህና አይደለም ብለውት
ቤቴን ሠርቼ ባራት ባራት ማዕዘን
ሲከፈል ሁለት ሌላ ሦስት ማዘን
ሲቆረጥ ሲሰነጠቅ መሥመር ፥ ሸርፎ ተሸራርፎ
ባቡር መንገድ ተኛ ያገር ሰው፥ እጅ እግሩን ሸክፎ
ዓይኑን ጨፍኖ አስሮ አንጀቱንም አጥፎ
ደሞ ይኼኛው ስባዝን ጎዳና ላይ አግኝቶኝ
መሥመር መንገድ ነው አያልቅም ብሎኝ
አራት ሒሳብ ቤት ባንዴ ተፊቴ ተገልጦ
በቁጥር ሲታይ ፥ ታየኝ ከሁሉ በልጦ
ግን የረሳሁት ለዘመናት ጎዳና መቆሜ
ሒሳብ አይገባኝም በየትኛው አቅሜ
ባዶና አንድ ዐዲስ ዓለም እንደፈጠሩ
የሁለቶሽ ባይናሪ ለሁሉ ከሠራ ቀመሩ
መሥመርና መደመር ይፍጠሩ አዲስ ቀመር
አይደምሰስ አይነካ የተሠመረ መሥመር
አይቀነስ አይጥፋ አለኝ ያሉት ቁጥር
ሒሳብ ያልገባው በሰላም እንዲኖር
ድሬዳዋ ሐምሌ 21 ፥ 2018 (በቁጥር ሲቀለድ)
No comments:
Post a Comment