Tuesday, June 5, 2018

እኛና ከ«ፐ» ፊደል ጋር ያለን ፀብ


እኛና ከ«ፐ» ፊደል ጋር ያለን ፀብ
 
 እኛና ከ«ፐ» ፊደል ጋር ያለን ፀብ
 
ፖለቲካ፣ ፓርቲ፣ ፓስፖርት፣
ፖስታ፣ ፓስታ፣ ካፖርት፣
ፕሮፓጋንዳ፣ ስፖርት፣ ፓኬጂንግ
ፕላን፣ ፕሮግራም፣ ፕሮግራሚንግ
ፓትሪያርክ ፥ ፓስተር
ብሎም እስከ ፕሮፌሰር
መች ይሆን ያገር ሰው የሚያውቅበት
መች ይሆን በኒህ ሠልጥኖ የሚገንበት
ከ«ፐ» ተግባብቶ
ከ«ፑ» ተስማምቶ
ከ«ፐ» እስከ «ፖ» ዘልቆ
ቃላቱን ዐውቆ ጠንቅቆ
የሚዘንጥ፣ የሚያምርበት፣
የማያፍርበት፣ የሚታፈርበት
ከዓለም ጭራነት ተራ ተላቆ
ከፊት ታደባባይ ቆሞ ተራቆ
ክኅሎቱ ዕውቀቱ ታምኖ የማይሣቅበት
አሜሪካ ወጌሻ የማትጠራበት
ራሱን ችሎ «ሀ» ብሎ «ፐ» የሚልበት
«ፈ» እና «ፐ» የማይምታቱበት
 
ዕለተ አማኑኤል፥ ግንቦት 2018 [በራሴ አቆጣጠር]
 
ብሩክ በ.

No comments:

Post a Comment