Friday, April 6, 2018

የሺህ ዓመት ለፈጣሪ አንድ ቀን ነው ምሥጢር

የሺህ ዓመት ለፈጣሪ አንድ ቀን ነው ምሥጢር


አንድ ቀን ለግዜር ከሆነ ሽህ ዓመት
አንድ ቀን ለፈጣሪ ከሆነ ሽህ ዓመት
ላበሻ የግዜር ሰው ድሀ የምትሉት
አክሱምን ገትሮ ጠፋ የምትሉት
ከላሊበላ ወዲህ አልታየም
የፈሰሰ ውሃ አላቀናም
ብላችሁ ያማችሁ
ሥጋውን የበላችሁ
ሲያረፍድ ተቀጠሮ
ቢቀር ተደማምሮ
ሐበሻ የግዜሩ ሰው
ለእምነቱ የሚሞተው
ደቂቃን ቢያደርግ ሰዓት
ቀንን ብዙ ወራት 
ወራትን ዘመናት
አሁን ምን አለበት ብትተዉት
ድሀው ተስፋን ቢቆጥርበት
መጋቢት የጊዮርጊስ ቀን 2018 በጊዜ ሲቀለድ
ብሩክ በ.

No comments:

Post a Comment