Thursday, April 5, 2018

ለፈገግታና ለታሪክ ትውስታ

ለፈገግታና ለታሪክ ትውስታ



በጌታቸው ታረቀኝ ከተጻፈው አቤቶ ልጅ እያሱ ከሚለው ታሪካዊ ድራማ መግቢያ ላይ የተወሰደ

ገቢር 1
ትዕይንት 1

መብራት ሲጠፋ መጋረጃው ከመከፈቱ በፊት ለተመልካች የሚነበብ

«የተከበራችሁ ተመልካቾቻችን ዛሬ የምትመለከቱት . . . »
መጋረጃ ይነሳል። . . .  በጨለማው ነጋሪት ይሰማል። ጥሩምባ ይሰማል . . . (ጣሴ በባህላዊ የቤተመንግስት ስርአት ለብሶ ይገባል።)

ጣሴ ፦ (በአዋጅ ነጋሪ ስልት) . . .  ስማ ስማ . . . ጆሮ ያለህ ስማ . . .  የሰማህ ላልሰማው አሰማ  . . . ስሚ ስሚ ጆሮ ያለሽ ስሚ . . . የሰማሽ ላልሰማችው አሰሚ  . . . አፈሩ በጎርፍ ተሸርሽሮ እንዳያልቅ አቧራው እየተነሳ በንፋስ እንዳይቦን ከፈረንጅ አገር አስመጥቼ የተከልኩትን የባህር ዛፍ እየዘነጠፍክ ጥርስህን የምትፍቅ የምትፍቂ . . . ጥርስ አባታችሁ ይርገፍና በድዳችሁ ነው የማስቀራችሁ። ቢሻው ጥርሳችሁ በስብሶ ይርገፍ እንጂ የባህር ማዶ ዛፌን እንዳትነኩ ብያለሁ!!! የኮረንቲ መብራት ተከተማው አልፎ በየባላገሩ እንዲደርስ የዘረጋሁትን የመዳብ ሽቦ እየበጠሳችሁ የእጅ አምባርና የጆሮ ጉትቻ የምትሰሩና የምታጌቱ . . . እጅ እና እግራችሁን እያስቆረጥኩ መቀጣጫ ነው የማደርጋችሁ . . . በነገይቱ ተሲአት ደግሞ የንጉሰ ነገስት እያሱ አምስተኛ . . . የንግስ በዓል በታላቁ ቤተ መንግስት ስለሚከበር ሙላሽ ሁላ መጥተሽ ምሳ እንድተበይ ተጠርተሻል!! በማትመጡት ላይ ግን . . .


No comments:

Post a Comment