
Miss Me But Let Me Go
[To Sir Fred]
When I come to the end of
the road
And the sun has set for
me
I want no rites in a
gloom-filled room
Why cry for a soul set
free?
Miss me a little-but not
too long
And not with your head
bowed low
Remember the love that we
once shared
Miss me-but let me go
For this is a journey
that we all must take
And each must go alone.
It's all part of the
Master's plan
A step on the road to
home
When you are lonely and
sick of heart
Go to the friends we know
And bury your sorrows in
doing good deeds
Miss me but let me go.
Author: Anonymous English Poem
Translation in Amharic By Brook Beyene
To my beloved brother His Honor Great Artist Empis Fred (Ras Fredo),
and his beloved spouse Ariane Le Lay, the lover of Ethiopia and Ethiopians
On the day of his last journey out today December 13, 2017
|
እቴ ትንሽ ናፍቂኝ፣
ግን ልሂድበት! እዚህ ቆይ አትበይኝ
ለአያ ፍሬድ
ከመንገዱ ጫፍ
ላይ ስደርስ፣ መንገዴ ሲያልቅ
ፀሐይዋ ከሰማይ
ለእኔ ስታዘቀዝቅ ልትጠልቅ
ደብዛዛ ብርሃን
በተሞላ ቀዬ፣ አያሻኝም ፍትሃት
ለነፍስ ምን
ያረጋል ለቅሶ፣ አግኝታ ሳለ ሃርነት?
ትንሽ ብቻ ናፍቂኝ
ብዙ እንዳይሆን ግን አደራሽን
ባጎነበሰ አንገትሽ
ሸጉጠሽ፣ እንዳትቀብሪው ፊትሽን
ስላለፈ ፍቅራችን
ብለሽ፣ መቼም እንዳትረሺኝ!
እቴ ትንሽ ናፍቂኝ፣
ግን ልሂድበት! እዚህ ቆይ አትበይኝ
እነሆ ዛሬ ተራዬ
ደርሶ መሳፈር አለብኝና ለዚህ ጉዞ
ለብቻ እንጅ፣
አይኬድምና እዚህ፣ እጅ ለእጅ ተያይዞ
እንደ ፈጣሪያችን
ዕቅድ ሐሳብ፣ አንዱ መገለጫ ምክንያት
ከዋናው ቤታችን
ለመድረስ፣ ይኸው አንድ እርምጃ ወደፊት
ብቸኝነት ሲውጥሽ
ሲከፋ ክፉኛ ልብሽ
ጓደኞቻችን እንደኔ፣
ላንቺ ዛሬም አሉልሽ
እናም ያን ሐዘንሽ
ገንዘሽ፣ በጎ ሥራ እየሠራሽ ቅበሪልኝ
እቴ ትንሽ ናፍቂኝ፣
ግን ልሂድበት! እዚህ ቆይ አትበይኝ
ደራሲው ያልታወቀ የእንግሊዝኛ ግጥም
ትርጉም በብሩክ በየነ
ለውድ ወንድሜ ክቡር ታላቅ አርቲስት
ኤምፒስ ፍሬድ (ራስ ፍሬዶ) እና ለውድ ባለቤቱ ኧሪያን ለ ሌይ፣
የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን ወዳጅ በዕለተ ሕልፈቱ ዛሬ ታህሳስ ፬፣ ፳፻፲
|
No comments:
Post a Comment