Dear Brothers and Sisters I have a dedication or rather a gift for you all. Thank you for all your support you gave during my fight against the odds and finding my true self. Each one of you had an important role in changing my life. I just thank God for giving me these blessing: the love and trust of you all. Thank you for your patience and encouragement whatever the situation was. I am now a different Brook, no kidding. Merci a vous tous! Amesgenallehu! Yekeneyley! Geletoma! Shukeren! Danks! Grace mille! And with all other languages of the world and the heaven. My gift to you is a quot that I found from great quotations of Bob Marely. I also translated it.
“Only once in your life, I truly believe, you find someone who can completely turn your world around. You tell them things that you’ve never shared with another soul and they absorb everything you say and actually want to hear more. You share hopes for the future, dreams that will never come true, goals that were never achieved and the many disappointments life has thrown at you. When something wonderful happens, you can’t wait to tell them about it, knowing they will share in your excitement. They are not embarrassed to cry with you when you are hurting or laugh with you when you make a fool of yourself. Never do they hurt your feelings or make you feel like you are not good enough, but rather they build you up and show you the things about yourself that make you special and even beautiful. There is never any pressure, jealousy or competition but only a quiet calmness when they are around. You can be yourself and not worry about what they will think of you because they love you for who you are. The things that seem insignificant to most people such as a note, song or walk become invaluable treasures kept safe in your heart to cherish forever. Memories of your childhood come back and are so clear and vivid it’s like being young again. Colours seem brighter and more brilliant. Laughter seems part of daily life where before it was infrequent or didn’t exist at all. A phone call or two during the day helps to get you through a long day’s work and always brings a smile to your face. In their presence, there’s no need for continuous conversation, but you find you’re quite content in just having them nearby. Things that never interested you before become fascinating because you know they are important to this person who is so special to you. You think of this person on every occasion and in everything you do. Simple things bring them to mind like a pale blue sky, gentle wind or even a storm cloud on the horizon. You open your heart knowing that there’s a chance it may be broken one day and in opening your heart, you experience a love and joy that you never dreamed possible. You find that being vulnerable is the only way to allow your heart to feel true pleasure that’s so real it scares you. You find strength in knowing you have a true friend and possibly a soul mate who will remain loyal to the end. Life seems completely different, exciting and worthwhile. Your only hope and security is in knowing that they are a part of your life.”
― Bob Marley
“በሕይወት ዘመንህ ሁሉ አንድ ጊዜ ብቻ ዓለምን ሁሉ እንደ አዲስ የሚፈጥሩልህን ሰዎች ታገኛለህ ብዬ ከልቤ አምናለሁ። ከሌላ ነፍስ ጋር ያልተጫወትካቸውን ነገሮች ትነግራቸዋለህ እና የምትናገረውን ሁሉ አጣጥመው ይውጡታል ብሎም እንደገና ተጨማሪ ነገር እንድታወራላቸው ይፈልጋሉ። የወደፊት ተስፋህን፣ ምን ጊዜም ዕውን የማይሆን ሕልምህን፣ ግብ ያልመቱ ዕቅዶችህን፣ ሕይወት ባንተ ላይ የወረወረቻቸውን አስቀያሚ ነገሮችን ሁሉ ታጫውታቸዋለህ። የሆነ አስደናቂ፣ ግሩም ነገር ሲፈጠር አግኝተህ እስክትነግራቸው ስሜትህን መቆጣጠር ያቅትሃል፣ የደስታህ ተካፋይ እንደሚሆኑ ልብህ በእርግጠኝነት ይነግርሃል። ስትጎዳ አብረውህ ለማልቀስ ሐፍረት አይገታቸውም፣ ራስህን ቂል ስታደርግ ካንተ ጋር አብረው ከመሳቅ ወደኋላ አይሉም። በጭራሽ ስሜትህን አይጎዱትም ወይም የማትረባ ሰው እንደሆንክ ሆኖ እንዲሰማህ አያደርግሁም፤ ይልቁንስ የጎደለህን ነገር እየሞሉ ያገዝፉህና አንተን ልዩ ሰው የሚያደርጉህን በጎ ጎኖችህን ብሎም ውበትን የሚያጎናጽፉህን ጌጦችህን ከላይህ ላይ አጉልተው በማውጣት መልሰው ላንተ ያሳዩሃል። በግድ አንድን ነገር እንድትቀበል ማስገደድ፣ ባንተ ላይ ምንቀኝነት ሆነ ቅናት፣ ካንተ ጋር ተራ ፉክክር ቦታ አይኖራቸውም፤ ይልቁንስ እነርስሱ አጠገብህ በሚኖሩበት ጊዜ በቦታው ላይ ጸጥታ የተሞላ ፍጹማዊ እርጋታ ይነግሣል። በማንነትህ ብቻ ስለሚወዱህና ራስህን መሆን ስለምትችል ስላንተ ምን እንደሚያስቡ ሙሉ በሙሉ አለመጨነቅ ትችላለህ። የሙዚቃ ኖታ፣ ዘፈን ወይም በእግር ሽርሽር ማድረግ የመሳሰሉ እዚህ ግቡ የማይባሉ ተራ ነገሮች ሁሉ በፍቅር የምትወዳቸው፣ ገንዘብ የማይገዛቸው፣ በስስት የምትይዛቸው፣ ውድ ሀብቶችህ ሆነው በልብህ ሕያው ሆነው ለዘላለም ይኖራሉ። የልጅነት ጊዜ ትዝታዎችህ ተመልሰው እንደገና ይመጣሉ እና ሲመጡም ምንም ብዥታ የሌለባቸው በግልፅ የሚታዩ ይሆናሉ፤ በቃ መልሶ ወደ ልጅነት እንደገና የመመለስና ልጅ የመሆን ያክል ነው። ቀለማት ከበፊቱ ይልቅ ደምቀውና አንጸባራቂ ሆነው ይታዩሃል። ከዚህ ቀደም ሣቅ በስንት አንዴ በመከራ ይከሰት እንዳልነበር ወይም ከናካቴው ጠፍቶ እንዳልነበር የዕለት ተዕለት ተራ ጉዳይ ይሆንልሃል። አንድ ጊዜ ወይም ሁለቴ ስልክ መደወል ረዥሙን ቀንህን በድል እንድትወጣው ያግዝሃል እና ሁልጊዜም ስልኩን ስትዘጋውም ፊትህ ላይ ፈገግታን ይቀራል። ጓደኞችህ ባሉበት፣ ዝምብሎ ሳያቋርጡ ወሬ ማውራት ግድ አይልም፤ በቃ አጠገብህ ስላሉ ብቻ ሐሴትን ታደርጋለህ። ላንተ በጣም ልዩ ለሆነው ሰው በጣም አስፈላጊ ቁምነገሮች እንደሆኑ ስለምታውቅ ከዚህ ቀደም ደንታ የማይሰጡህ የነበሩ ነገሮች አሁን ግን አስደሳች ይሆኑልሃል። ስለዚህኛው ሰው በሁሉም አጋጣሚ እና በሁሉም የምታደርገው ነገር ሁሉ ታስታውሳለህ። ተራ ነገሮች እንደ ደብዘዝ ያለ ሰማያዊ ሰማይ፣ እንደ በሽውታ ቀስ ብሎ የሚነፍስ ነፋስ፣ ወይም በአድማስ ላይ ውሽንፍር እንደ ቀላቀለ ዝናብ እነርሱን ወደ እዝነ ልቦናህ ያመጣቸዋል። ሊሰበር ሊችልበት ዕድል መኖሩን እያወቅክ ልብህን ተከፍተዋለህ እናም ስትከፍተው ሊኖር ይችላል ብለህ አስበህ የማታውቀውን ፍቅር እና ደስታ አገኝተህ ታጣጥማቸዋለህ። በጣም እውነት ከመሆኑ የተነሳ የሚያፈራህን እውነተኛውን ደስታ ልብህ እንዲያጣጥም ለማድረግ ብቸኛው መንገድ ራስህን ለአደጋ ተጋላጭ ማድረግ እንደሆነ ታረዳዋለህ። እውነተኛ ጓደኛ እንዳለህ ምናልባትም እስከ መጨረሻው ካንተ ጋር በታማኝነት የሚዘልቅ የነፍስህ አማሳያ እንዳለ በማወቅህ ጥንካሬን ታገኛለህ። ሕይወት ሙሉ በሙሉ ፍጹም ሌላ መስላ፣ አስደሳች እና ቢያጣጥሟት የማትጎዳ ሆና ትታይሃለች። ተስፋ ብቻ ታደርጋለህ እና የደኅንነት ዋስትናህ ጓደኞችህ የሕይወትህ አንድ አካል መሆናቸውን ማወቅ ብቻ ነው።”
ቦብ ማርሊ
No comments:
Post a Comment