ቁንጫና ትዃን
አንድ ግንባር ፈጥረው
ጠላትን ሊመቱ አብ-ረው
ቃል ኪዳን ተሳስረው
ሲወረዱ ከጦሩ ሜዳ
ከፍልሚያው አውድማ
ምድር ስትዘል ሰማይ
ረመጥ እሳት ላይ ቆማ
የጠላት ክንድ በርትቶ
የሞት ሞቱን
ድንገት ተነሥቶ
ሲወረወር ሲወናጨፍ
ከአጥናፍ አጥናፍ
በግራም በቀኝም
ሲነፋ የእሳት ወናፍ
ቁንጮች በስልት አፈግፍገው
ሲያመልጡ ተፈናጥረው
ናፍጣ እንደ ጨረሰ ታንክ
ሲንተፋተፍ ሲንዘባዘብ
መች ታየው ትዃን
በጠላት ሲከበብ
ትዃን ሞኙ
ቁንጫ አማኙ
እንዲያው እንደ በሬ
ሣሩን ብቻ ዐይቶ
ገደሉን ረስቶ
ልቡን ለሸማቂ
እንካ ብሎ ሰጥቶ
አጓጉል ተሰውቶ
እንዲያው በአጉል ቀን
ከሸማቂ ጋር ዘምቶ
ታየ ከሜዳው ላይ
አከርካሪውን ተመትቶ
ለስትራቴጂያዊ ጠላት
ስትራቴጂያዊ ወዳጅነት
አጉል ጅራትን ማሳየት
ላይቀር ኋላ መበላላት
አንድ ግንባር ፈጥረው
ጠላትን ሊመቱ አብ-ረው
ቃል ኪዳን ተሳስረው
ሲወረዱ ከጦሩ ሜዳ
ከፍልሚያው አውድማ
ምድር ስትዘል ሰማይ
ረመጥ እሳት ላይ ቆማ
የጠላት ክንድ በርትቶ
የሞት ሞቱን
ድንገት ተነሥቶ
ሲወረወር ሲወናጨፍ
ከአጥናፍ አጥናፍ
በግራም በቀኝም
ሲነፋ የእሳት ወናፍ
ቁንጮች በስልት አፈግፍገው
ሲያመልጡ ተፈናጥረው
ናፍጣ እንደ ጨረሰ ታንክ
ሲንተፋተፍ ሲንዘባዘብ
መች ታየው ትዃን
በጠላት ሲከበብ
ትዃን ሞኙ
ቁንጫ አማኙ
እንዲያው እንደ በሬ
ሣሩን ብቻ ዐይቶ
ገደሉን ረስቶ
ልቡን ለሸማቂ
እንካ ብሎ ሰጥቶ
አጓጉል ተሰውቶ
እንዲያው በአጉል ቀን
ከሸማቂ ጋር ዘምቶ
ታየ ከሜዳው ላይ
አከርካሪውን ተመትቶ
ለስትራቴጂያዊ ጠላት
ስትራቴጂያዊ ወዳጅነት
አጉል ጅራትን ማሳየት
ላይቀር ኋላ መበላላት
11/04/2017 ታህሳስ
No comments:
Post a Comment