ብርጭቆ የሰቀልን ለታ
ስፖርት ነገር ትንሽ ጂም ሠራሁ ብዬ
ቅዳሚት ሰንበትን በጎርደን ጂን አክፍዬ
ከቼቫዝ አብሶልዩት እስከ አፕሬትቭ አረቂ ጠላ
ሁሉን ስሸፍጠው ከብርዙ ጠጅ እስከ አምቡላ
ስደሰት ስከፋ ብርጭቆ ሳነሣ
ስመዠርጠው ለራሴ ሳልሣሣ
ለፓስታ ወይን ስናዝለት ኮንስፓኛን ለጥሬ
ስንታጠብ ውስኪ፣ ከኮኝክ እስከ ካምፓሬ
የለጋነው ሻምፓኝ እሳቱን የጫርንለት ኮክቴል
ቲያ ማሪያው ባካርዲው መች ልኑር ያሰኛል
ዓለምን እሳንሶ በመለኪያ ውስጥ ከቷት
ኢምንት አሳክሏት የመጠጥ ምትሃት
የዋጥነው ታኪላ፣ ሳምቡካና ኳንትሮ
ያኖረልን አልኮል ድሮን በዘንድሮ
ጽዋ እያጋጨን ነገን ዛሬ ሠራነው
ኮማሪን ካጎት ካክስት ፈረጅነው
ሰኞን አጥቁረን ስንቴ ሥራ ቀርን
ስንት ጊዜስ ከሰው መሃል ጎደልን
ቃል አባይ ሆነን ቃላችንን በላን
ለአቅመ ቤት ሳይደርስ እንዲያው በበራሪ
ስንት ደሞዝ ቀረ ከንቱ ወድቆ ከግሮሰሪ
ያ የልብ ወዳጄ የምለው የምሽታ ቤቱ
ከልቡ ሳላድር ሠርክ ሸንቶኝ በሽንቱ
ከሆዱ አራግፎኝ ሲገባ ከቤቱ
የኔ ነው የሱ የማን ነው ጥፋቱ
ደሞ ጠዋት እነሣና እሾህን በእሾህ ብዬ
ስታደም በራሴ የተዝካሬን ድንኳን ጥዬ
በራሴው ደጀ ሰላም መክፈልቴ ሆኖ ቢራ
አዲሱን ቀኔን ሳጨልመው ከፍቼ ዳንኪራ
ወዳጅ ዘመድ ቤተሰብ ሲገታተረኝ
ተስፋ ቆርጦ በኔ ዐይኑን ሲደብቀኝ
ከነ ማሪንጌ ቻ ስንል ቸበርቻቻ
ለኛ ፍቅር ደስታ የት ተገኝቶ አቻ
ቧልስ ቡጊ ቡጊ ዲስኮና ሳልሳ
ዕድሜ በሮ ሄዶ ስንወድቅ ስንነሣ
ያ ደሞ ትልቁ ኮማሪ በኃላፊነት ጠጡ ባይ
አዛኝ ቅቤ አንጓች የእፉኚት ልጅ አስመሳይ
ቀድሞ እሱ ራሱ ራሱን ኃላፊነት ቢሰማው
ንዋይ ባያሰክረው ህሊናውን ባይረግጠው
ለኛ ጠላ ቢራ ባልነበር ጠምቆ የሚሸጠው
የፊደል ገበታን በጠ-ጡ ባልጀመረው
ስካራችን ሆኖ አዳራችን
ሌት ተቀን ሕይወታችን
ከጠጣህ አትንዳ ብለው ደርሶ የሞገቱን
እነሱ አልነበሩ እንዴ ወደዚህ የነዱን
በእባብ አንደበት እንደ ቆሪጥ
አመላክተው አቅጣጫ
ጡጦ አስጥለውን ሲግቱን መጠጥ
አድባራቸውን ልናሞቅ ስንንጫጫ
ይኸው ኖረን ኖረን ስንጨልጥ ስንለጋ
መድከም አይቀር ከጠላነው አልጋ፣
የማታ ማታ ስንዘረጋ
ኮሮሸራችን ሲያዝ ሲያብይ ጉልበታችን
ጽልመቱን አልብሶን ሲያበራ ጉበታችን
ጥፋቱ የማን ነው ውሃን የተውን ለታ
የጥፋት ውሃ ሲወስደን የማታ የማታ
ውሃ ሲወስደን አሳስቆ
ከሰው መሃል ነጥቆ
ድንገት ደርሶ ጎርፉ ሲወስደን አንቦጫርቆ
ውስጥ ውስጡን ገሎን ሥራውን አጠናቆ
ባንገት እስኪከትልን ሸምቀቆ
ሞት ሲፈርደን ማን ሰምቶ፣ ማን ዐውቆ
ቀምቅሜ ፈጅቼው
ጤናዬን በገንዘቤ
ልሄድ ነው መሰል
ገንዘብን ተገንዝቤ
ካለቀ በኋላ ከደቀቀ
ክፋትሽ ታወቀ
አዲዮስ ግሮሰሪ
እያማርሽኝ ቅሪ
ብርጭቆ የሰቀልን ለታ
ሆን-ለት የራሳችን ጌታ
ትሳስ 12 ዕለተ ሚካኤል 2017
ስፖርት ነገር ትንሽ ጂም ሠራሁ ብዬ
ቅዳሚት ሰንበትን በጎርደን ጂን አክፍዬ
ከቼቫዝ አብሶልዩት እስከ አፕሬትቭ አረቂ ጠላ
ሁሉን ስሸፍጠው ከብርዙ ጠጅ እስከ አምቡላ
ስደሰት ስከፋ ብርጭቆ ሳነሣ
ስመዠርጠው ለራሴ ሳልሣሣ
ለፓስታ ወይን ስናዝለት ኮንስፓኛን ለጥሬ
ስንታጠብ ውስኪ፣ ከኮኝክ እስከ ካምፓሬ
የለጋነው ሻምፓኝ እሳቱን የጫርንለት ኮክቴል
ቲያ ማሪያው ባካርዲው መች ልኑር ያሰኛል
ዓለምን እሳንሶ በመለኪያ ውስጥ ከቷት
ኢምንት አሳክሏት የመጠጥ ምትሃት
የዋጥነው ታኪላ፣ ሳምቡካና ኳንትሮ
ያኖረልን አልኮል ድሮን በዘንድሮ
ጽዋ እያጋጨን ነገን ዛሬ ሠራነው
ኮማሪን ካጎት ካክስት ፈረጅነው
ሰኞን አጥቁረን ስንቴ ሥራ ቀርን
ስንት ጊዜስ ከሰው መሃል ጎደልን
ቃል አባይ ሆነን ቃላችንን በላን
ለአቅመ ቤት ሳይደርስ እንዲያው በበራሪ
ስንት ደሞዝ ቀረ ከንቱ ወድቆ ከግሮሰሪ
ያ የልብ ወዳጄ የምለው የምሽታ ቤቱ
ከልቡ ሳላድር ሠርክ ሸንቶኝ በሽንቱ
ከሆዱ አራግፎኝ ሲገባ ከቤቱ
የኔ ነው የሱ የማን ነው ጥፋቱ
ደሞ ጠዋት እነሣና እሾህን በእሾህ ብዬ
ስታደም በራሴ የተዝካሬን ድንኳን ጥዬ
በራሴው ደጀ ሰላም መክፈልቴ ሆኖ ቢራ
አዲሱን ቀኔን ሳጨልመው ከፍቼ ዳንኪራ
ወዳጅ ዘመድ ቤተሰብ ሲገታተረኝ
ተስፋ ቆርጦ በኔ ዐይኑን ሲደብቀኝ
ከነ ማሪንጌ ቻ ስንል ቸበርቻቻ
ለኛ ፍቅር ደስታ የት ተገኝቶ አቻ
ቧልስ ቡጊ ቡጊ ዲስኮና ሳልሳ
ዕድሜ በሮ ሄዶ ስንወድቅ ስንነሣ
ያ ደሞ ትልቁ ኮማሪ በኃላፊነት ጠጡ ባይ
አዛኝ ቅቤ አንጓች የእፉኚት ልጅ አስመሳይ
ቀድሞ እሱ ራሱ ራሱን ኃላፊነት ቢሰማው
ንዋይ ባያሰክረው ህሊናውን ባይረግጠው
ለኛ ጠላ ቢራ ባልነበር ጠምቆ የሚሸጠው
የፊደል ገበታን በጠ-ጡ ባልጀመረው
ስካራችን ሆኖ አዳራችን
ሌት ተቀን ሕይወታችን
ከጠጣህ አትንዳ ብለው ደርሶ የሞገቱን
እነሱ አልነበሩ እንዴ ወደዚህ የነዱን
በእባብ አንደበት እንደ ቆሪጥ
አመላክተው አቅጣጫ
ጡጦ አስጥለውን ሲግቱን መጠጥ
አድባራቸውን ልናሞቅ ስንንጫጫ
ይኸው ኖረን ኖረን ስንጨልጥ ስንለጋ
መድከም አይቀር ከጠላነው አልጋ፣
የማታ ማታ ስንዘረጋ
ኮሮሸራችን ሲያዝ ሲያብይ ጉልበታችን
ጽልመቱን አልብሶን ሲያበራ ጉበታችን
ጥፋቱ የማን ነው ውሃን የተውን ለታ
የጥፋት ውሃ ሲወስደን የማታ የማታ
ውሃ ሲወስደን አሳስቆ
ከሰው መሃል ነጥቆ
ድንገት ደርሶ ጎርፉ ሲወስደን አንቦጫርቆ
ውስጥ ውስጡን ገሎን ሥራውን አጠናቆ
ባንገት እስኪከትልን ሸምቀቆ
ሞት ሲፈርደን ማን ሰምቶ፣ ማን ዐውቆ
ቀምቅሜ ፈጅቼው
ጤናዬን በገንዘቤ
ልሄድ ነው መሰል
ገንዘብን ተገንዝቤ
ካለቀ በኋላ ከደቀቀ
ክፋትሽ ታወቀ
አዲዮስ ግሮሰሪ
እያማርሽኝ ቅሪ
ብርጭቆ የሰቀልን ለታ
ሆን-ለት የራሳችን ጌታ
ትሳስ 12 ዕለተ ሚካኤል 2017