ከበሮ በሥዕሉ ላይ እንደሚታየው ሦስት ዋንኛ ክፍሎች አሉት። አፉ ሰፋ የሚለው እና በዋንኛነት የሚመታው "ደባይ" ሲባል ሁለተኛው ጫፍ ጠበብ የሚለው እና ከጸናጽል ጋር እየተንሰላሰለ አልፎ አልፎ ምትን ለመጠበቅ ብቻ የሚነካው ወይም የሚመታው "ጥራይ" ይባላል። የከበሮውን አብዛኛውን ክፍል የሚሸፍነው ሆዱ ደግሞ "ከርሰ ከበሮ" ወይም "የድምፅ ሳጥን" በመባል ይታወቃል።
የሰው ልጅም በአጠቃላይ ሲታይ በእነዚህ ሦስት የከበሮ ክፍሎች ተለይቶ ሊታይ ይችላል። ሕይወት ደግሞ እንደ ከበሮ መቺው። ደባይ የሚባለው ክፍል ታዋቂ ሰዎችን፣ ዝነኖችን፣ ፖለቲከኞችን፣ የሃይማኖት መሪዎችን፣ ባለልዩ ተሰጥዖ ሰዎችን ወዘተ ይወክላል። ምንም ያድርጉ ምን ጩኸታቸው ገኖ ቁልቁል እስከ ታች ይሰማል።ሦስተኛው ክፍል "ጥራይ" ደግሞ የለየለትን መናጢ ድሃ ይወክላል። ችግሩ ጥርስ ሲያወጣ፣ ጠኔው ሲበዛ ወደ ላይ ዘልቆ የላይኛውን ክፍል ደባዩን ቀልብ ይስባል።
መሀለኛው ክፍል ማለትም ከርሰ ከበሮው ደግሞ በተለምዶ "አማካይ" የሚባለውን ወይም "መካከለኛውን ክፍል" ይወክላል። ከላይና ከታች የሚመጣውን ድምፅ ያስተጋባል። በሁለቱ ጠርዞች መካከል ያለውን ግንኙነት ወዲህና ወዲህ እያለ ድምፃቸውን በማቀባበል አንድ ወጥ ዜማ እንዲሰማ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል።
ሕይወት በፈለገችው ምት እየደበደበች በነፍስ ወከፍና በጅምላ ከእያንዳንዱ የሰው ልጅ መስማት የምትፈልገውን ዜማ ትሰማለች። እያንዳንዱ ዘመንም የየራሱ ከበሮ ይኖረዋል። ለምሳሌ የግሪክ የዴሞክራሲ ዘመን፣ የሮማ ዘመን፣ የመስቀል ጦርነት፣ የተሃድሶ ዘመን፣ አንደኛ የዓለም ጦርነት፣ ሁለተኛ የዓለም ጦርነት፣ ቀዝቃዛው ጦርነት፣ ሽብርተኝነት፣ ግሎባይላይዜሽን እያለ ይቀጥላል።
ደባዮች ገነው ይጮኸሉ። ጥራዮችም በአቅማቸው የደባይን ምት ይቆጣጠራሉ። መሃል ሰፋሪዎችም መሃል ላይ ሆነው ሁለቱን ጫፍ ሲያዳምቁና ሲያደንቁ ይኖራሉ። ሁሉም ሕይወት የቀመረችላቸውን ዜማ እየተደለቁ አዚመው ያልፋሉ።
ከሣቴ ብርሃን ቡሩክ በዕለተ ገብሪኤል (2019 በራስ አቆጣጠር)

መነሻ ሐሳብ THE SUBTLE ART OF NOT GIVING A F*CK

No comments:
Post a Comment