የሞት ውበቱ ፲፬ - የካሃሊል
ጂብራን ግጥም
(መታሰቢያነቱ በበራራ ቊጥር ET 302 መጋቢት 1 ፥ 2011 ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት 157 መንገደኞች)
ትርጉም፦ በብሩክ በየነ
ክፍል አንድ - ጥሪው
በፍቅር ሰክራለችና እፎይ ትበል ነፍስያዬ ትተኛበት
ትረፍበት መንፈሴ ስለነበራት የቀንና ሌሊት ቸርነት ፤
ባልጋዬ ዙሪያ ሻማዎቹን ለኩሱዋቸው፣ እጣኑንም አጫጭሱ
የጠምበልልና የጽጌሬዳ አበባ ቅጠል በላዬ ላይ ነስንሱ፤
ጸጒሬንም በሉባንጃ ሞጅራችሁ ቅበሩት፤ እግሬንም ሽቶ ቀቡት
መላከ ሞት በእጁ ግንባሬ ላይ የጻፈውን ጮክ ብላችሁ አንብቡት።
ትረፍበት መንፈሴ ስለነበራት የቀንና ሌሊት ቸርነት ፤
ባልጋዬ ዙሪያ ሻማዎቹን ለኩሱዋቸው፣ እጣኑንም አጫጭሱ
የጠምበልልና የጽጌሬዳ አበባ ቅጠል በላዬ ላይ ነስንሱ፤
ጸጒሬንም በሉባንጃ ሞጅራችሁ ቅበሩት፤ እግሬንም ሽቶ ቀቡት
መላከ ሞት በእጁ ግንባሬ ላይ የጻፈውን ጮክ ብላችሁ አንብቡት።
ዓይኖቼ ማየት
ታክተዋልና በእንቅልፍ እቅፍ ውስጥ ታቅፌ ልተኛበት፤
የክራሩ ብርማ ክሮች ይንዘሩ ነፍስያዬን በእሽሩሩ ያስተኝዋት፤
በገናው ማሲንቆው ሸምነው ዜማ ስልምልም እያለች ያለች ልቤን
የክራሩ ብርማ ክሮች ይንዘሩ ነፍስያዬን በእሽሩሩ ያስተኝዋት፤
በገናው ማሲንቆው ሸምነው ዜማ ስልምልም እያለች ያለች ልቤን
በእንዚራቸው
ዜማ ዓይነርግብ ያልብሷት የደከማት አቅል ነብሴን
ምትኅታዊ አንደምታው ልቤ ዝንት ዓለም የሚያርፍበት ምቹ አልጋው ነውና
ዱሮዋችንን አዚሙልኝ እያያችሁ ዓይኔ ላይ የቀረውን የማለዳውን ብርሃን ፋና።
ዱሮዋችንን አዚሙልኝ እያያችሁ ዓይኔ ላይ የቀረውን የማለዳውን ብርሃን ፋና።
የጠዋቷን ፀሐይ ለሰላምታ እጅ እንደሚነሱት አበቦች
እንባችሁን አደራርቃችሁ ቀና በሉ የኔ ውድ ወዳጆች።
በዚህች አልጋዬና በዘላለማዊው የሰማይ ሕይወት መካከል ባለው ክፍተት
እንደ ብርሃን ዓምድ የቆመችውን የሞት ሙሽራ እይዋት ተመልከቷት
ትንፋሻችሁን ዋጥ አርጉና በጸጥታ አዳምጡ ከኔ ጋራ
በነጭ ክንፎቿ እኔን ስትጣራ።
እንባችሁን አደራርቃችሁ ቀና በሉ የኔ ውድ ወዳጆች።
በዚህች አልጋዬና በዘላለማዊው የሰማይ ሕይወት መካከል ባለው ክፍተት
እንደ ብርሃን ዓምድ የቆመችውን የሞት ሙሽራ እይዋት ተመልከቷት
ትንፋሻችሁን ዋጥ አርጉና በጸጥታ አዳምጡ ከኔ ጋራ
በነጭ ክንፎቿ እኔን ስትጣራ።
ቀረብ በሉና ሸኙኝ ልሒድበት፤ ፈገግ ባሉ ከንፈሮች ዓይኖቼን ዳብሷቸው።
በድንቡሽቡሽ ጣቶቻቸው ሕፃናቱ እጆቼን ይጨብጧቸው ዘንድ ተዉዋቸው፤
አዛውንቱም የተገታተሩ ደም ሥሮች ባሏቸው እጆቻቸው ግንባሬን ይዘው ይመርቁኝ፤
ድንግል ልጃገረዶች ቀርበው የእግዜርን ጥላ ዓይኖቼ ሥር ይመልከቱልኝ፣
የእሱን ፈቃድ በትንፋሼ ሩጫ የገደል ማሚቶውን ሲያስተገባ ይስሙልኝ።
በድንቡሽቡሽ ጣቶቻቸው ሕፃናቱ እጆቼን ይጨብጧቸው ዘንድ ተዉዋቸው፤
አዛውንቱም የተገታተሩ ደም ሥሮች ባሏቸው እጆቻቸው ግንባሬን ይዘው ይመርቁኝ፤
ድንግል ልጃገረዶች ቀርበው የእግዜርን ጥላ ዓይኖቼ ሥር ይመልከቱልኝ፣
የእሱን ፈቃድ በትንፋሼ ሩጫ የገደል ማሚቶውን ሲያስተገባ ይስሙልኝ።
ክፍል ሁለት - ወደ ላይ መነጠቅ
ከተራራው አናት በላይ አልፌ ሔጂያለሁ፤ ነፍስያዬ በፍጹም ነጻነት የሰማይ ባሕር ሰጥማለች
አጋች የላትም በጣም ርቃ መጥቃ ሔዳለች፤
ርቄ ሔጂያለሁ በጣም፣ እጅጉን ርቄያለሁ ባልንጀሮቼ፣
አመልማሎ ደመናዎቹ ጋርደዋቸዋል ተራሮቹን ከዓይኖቼ።
ሸለቆዎቹ በጸጥታ ባሕር ተውጠዋል አይሰማም ኮሽታ
ጎዳናውና ታዛው በሞላ ተረተዋል በአዚሙ ቱማታ፤
መስኩና የሣሩ ሜዳዎች በሞላ ጋልበው እያለፉ ነው ከአንዳች ነጭ ብርሃን ጀርባ
እንደ ጥር ወር ደመና፣ እንደ ሻማው ነበልባል ለግላጋ ልስልስ ቀዘባ
ድንግዝግዝ ያለ ቀይ ብርሃን ፀሐይ ከቤቷ ስትገባ።
አጋች የላትም በጣም ርቃ መጥቃ ሔዳለች፤
ርቄ ሔጂያለሁ በጣም፣ እጅጉን ርቄያለሁ ባልንጀሮቼ፣
አመልማሎ ደመናዎቹ ጋርደዋቸዋል ተራሮቹን ከዓይኖቼ።
ሸለቆዎቹ በጸጥታ ባሕር ተውጠዋል አይሰማም ኮሽታ
ጎዳናውና ታዛው በሞላ ተረተዋል በአዚሙ ቱማታ፤
መስኩና የሣሩ ሜዳዎች በሞላ ጋልበው እያለፉ ነው ከአንዳች ነጭ ብርሃን ጀርባ
እንደ ጥር ወር ደመና፣ እንደ ሻማው ነበልባል ለግላጋ ልስልስ ቀዘባ
ድንግዝግዝ ያለ ቀይ ብርሃን ፀሐይ ከቤቷ ስትገባ።
የወጀቡ ዘፈኖችና የዥረቶቹ ቁዘማ እዚህም እዚያ ተበታትነዋል
የሰዎች ሁካታ ረግቦ ተወደዚህ ሙሉ ጸጥታ እዚህ ሰፍኗል፤
አንዳች ነገር አይሰማኝም ከዘላለማዊው ሙዚቃ ሌላ ቅኝት
ፍጹም ሰምሮ ከተስማማው ከዚያ ከነፍስያዬ ጥልቅ ፍላጎት።
ሙሉ ነጭ ካባ ደርቤያለሁ፤
ምቾትና ሰላሜን አግኝቼያለሁ።
የሰዎች ሁካታ ረግቦ ተወደዚህ ሙሉ ጸጥታ እዚህ ሰፍኗል፤
አንዳች ነገር አይሰማኝም ከዘላለማዊው ሙዚቃ ሌላ ቅኝት
ፍጹም ሰምሮ ከተስማማው ከዚያ ከነፍስያዬ ጥልቅ ፍላጎት።
ሙሉ ነጭ ካባ ደርቤያለሁ፤
ምቾትና ሰላሜን አግኝቼያለሁ።
ክፍል ሦስት - ቀሪው አካል
ከዚህ ነጭ አቡጀዲ ፍቱኝና ክፈኑኝ እንደገና
የጠንበለልና ሊሊ አባባ ቅጠል በላዪ በትኑና፤
በድኔን አውጡት በዝሆን ጥርስ ከተለበጠው ሳጥን
በአፀደ ብርትኳን በቅጠል ክምር አንተርሱት እራሴን።
ሙሾ አትውረዱ አልሻም የሐዘን እንጉርጉሮ፣ ዘምሩ ስለ ልጅነት ዝፈኑ ስለ ደስታ፤
እንባችሁን አቅቡት፤ መከሩ ደርሷልና የወይኑ ይዘፈን ፍስሐ ይሁን ፌሽታ፤
አንዳችም ሲቃ ድምፅ እንዳይሰማ፤ ይልቁንስ የፍቅርና ደስታን ምልክት
በእጃችሁ ሣሉልኝ ከእኔ ፊት።
በሙሾና በቀንዲል ዜማ ሰላማዊው ድባብ አይደንግጥ አይደንብር፣
ልባችሁ ከልቤ ጋር የዘላለምን ሕይወት ዜማን በስምረት ይዘምር፤
ጥቁር ማቅ ለብሳችሁ አትዘኑ ስለእኔ
ደማቅ ቀለም ለብሳችሁ ተደስቱ እንደኔ፤
ሲቃ ተሞልቶ ልባችሁ አታውሩ ስለኔ፤ ዓይናችሁን ጨፍኑትና
እዩ ተመልከቱ ታገኙኛላችሁ በልባችሁ ሰርክ እንደገና።
የጠንበለልና ሊሊ አባባ ቅጠል በላዪ በትኑና፤
በድኔን አውጡት በዝሆን ጥርስ ከተለበጠው ሳጥን
በአፀደ ብርትኳን በቅጠል ክምር አንተርሱት እራሴን።
ሙሾ አትውረዱ አልሻም የሐዘን እንጉርጉሮ፣ ዘምሩ ስለ ልጅነት ዝፈኑ ስለ ደስታ፤
እንባችሁን አቅቡት፤ መከሩ ደርሷልና የወይኑ ይዘፈን ፍስሐ ይሁን ፌሽታ፤
አንዳችም ሲቃ ድምፅ እንዳይሰማ፤ ይልቁንስ የፍቅርና ደስታን ምልክት
በእጃችሁ ሣሉልኝ ከእኔ ፊት።
በሙሾና በቀንዲል ዜማ ሰላማዊው ድባብ አይደንግጥ አይደንብር፣
ልባችሁ ከልቤ ጋር የዘላለምን ሕይወት ዜማን በስምረት ይዘምር፤
ጥቁር ማቅ ለብሳችሁ አትዘኑ ስለእኔ
ደማቅ ቀለም ለብሳችሁ ተደስቱ እንደኔ፤
ሲቃ ተሞልቶ ልባችሁ አታውሩ ስለኔ፤ ዓይናችሁን ጨፍኑትና
እዩ ተመልከቱ ታገኙኛላችሁ በልባችሁ ሰርክ እንደገና።
በአረንጓዴ ቅጠሎች ጠቅልሉኝና በዝምታ
በሚወደኝ ጫንቃችሁ ተሸከሙኝና በርጋታ
ውስዱኝ ከዚያ ጫካ ማንም ከሌለበት በዝግታ።
በአጥንትና ራስ ቅል ኮሽኮሽታና ጫጫታ እንዳይረበሽ እንዳይሸበር
ይኼን የኔን ግኡዝ ገላ ወስዳችሁ ከዚያ የተጨናነቀ መካነ መቃብር።
ወደ ፅዱ ጫካ ውሰዱኝ ወይን ጠጅና ቀይ አበቦች ከበቀሉበት
ቆፍሩት መቃብሬን ካንዱ ቦታ ያንዱ ጥላ ባንዱ ካላጠላበት።
ደራሽ ጎርፍ መጥቶ አጥንቴን ከኦናው ሸለቆ እንዳይወስደው
መቃብሬ ጥልቅ ሆኖ ይቆፈር ምንም እንዳያውከው፤
ግርማ ሞገሴ ቢገንባት የጠዋቷ ድንግዝግዝ ብርሃን መጥታ
ቁጭ እንድትል ከመቃብሬ በላይ ከላዩ ላይ ወጥታ።
በሚወደኝ ጫንቃችሁ ተሸከሙኝና በርጋታ
ውስዱኝ ከዚያ ጫካ ማንም ከሌለበት በዝግታ።
በአጥንትና ራስ ቅል ኮሽኮሽታና ጫጫታ እንዳይረበሽ እንዳይሸበር
ይኼን የኔን ግኡዝ ገላ ወስዳችሁ ከዚያ የተጨናነቀ መካነ መቃብር።
ወደ ፅዱ ጫካ ውሰዱኝ ወይን ጠጅና ቀይ አበቦች ከበቀሉበት
ቆፍሩት መቃብሬን ካንዱ ቦታ ያንዱ ጥላ ባንዱ ካላጠላበት።
ደራሽ ጎርፍ መጥቶ አጥንቴን ከኦናው ሸለቆ እንዳይወስደው
መቃብሬ ጥልቅ ሆኖ ይቆፈር ምንም እንዳያውከው፤
ግርማ ሞገሴ ቢገንባት የጠዋቷ ድንግዝግዝ ብርሃን መጥታ
ቁጭ እንድትል ከመቃብሬ በላይ ከላዩ ላይ ወጥታ።
ምንም ምድራዊ ልብስ በድኔን እንዳታለብሱኝ፤
እንደ ፍጥርጥሬ ከእናት መሬት ክርታስ ውስጥ አኑሩኝ፤ በጡቶቿ መሃል ሸጉጡኝ።
በጠምበለል፣ ሊሊ አበባ አፈር ድቤ አልብሱኝ
የእጣን ዛፍ ዘር ለውሳችሁ በላዬ አፍሱብኝ
እና አንድ ቀን ወደፊት ሲያብብ ፍሬ ሲያፈራ ዘሩ
ከልቤ ሙዳይ ይናኝ ዘንድ መልካም መዓዛ ወደ ሰማይ፤
የሰላሜን ምሥጢር ይገልጹላታል ለራሷ ለፀሐይ፤
ከለስላሳ ነፋስ አብረው እየነፈሱ፣ መንገደኛውን ሁላ ያጽናኑት።
እንደ ፍጥርጥሬ ከእናት መሬት ክርታስ ውስጥ አኑሩኝ፤ በጡቶቿ መሃል ሸጉጡኝ።
በጠምበለል፣ ሊሊ አበባ አፈር ድቤ አልብሱኝ
የእጣን ዛፍ ዘር ለውሳችሁ በላዬ አፍሱብኝ
እና አንድ ቀን ወደፊት ሲያብብ ፍሬ ሲያፈራ ዘሩ
ከልቤ ሙዳይ ይናኝ ዘንድ መልካም መዓዛ ወደ ሰማይ፤
የሰላሜን ምሥጢር ይገልጹላታል ለራሷ ለፀሐይ፤
ከለስላሳ ነፋስ አብረው እየነፈሱ፣ መንገደኛውን ሁላ ያጽናኑት።
ወዳጆቼ በሉ እንግዲህ እዚህ ጋ ተዉኝ
- ኮቴያችሁ ሳይሰማ ሒዱ ቦታውን በጸጥታ ተዉት
በሸለቆው መሃል እንደሚጎማለለው ጸጥታ ሒዱ በእርጋታ
ለእግዚአብሔር ተዉኝና እንደ ለውዙና የቱፋሕ ብናኝ ቅጠሎቹ
ሒዱ በለስላሳው አየር በጸጥታ ብን፣ ብን እያላችሁ።
ተመለሳችሁ ዘና ስትሉ በዚያ ዓለም በመኖሪያችሁ
ሞት ከእኔና ከእናንተን ማስወገድ የማይቻለው ምን እንደሆነ ያኔ ታውቁታላችሁ።
እዚህ ያያችሁት ከምድሩ ዓለም እጅግ የራቀ ነውና
ተዉኝና ሒዱ፣ ከዚህ በሰላም ሒዱ።
ካህሊል ጂብራንበሸለቆው መሃል እንደሚጎማለለው ጸጥታ ሒዱ በእርጋታ
ለእግዚአብሔር ተዉኝና እንደ ለውዙና የቱፋሕ ብናኝ ቅጠሎቹ
ሒዱ በለስላሳው አየር በጸጥታ ብን፣ ብን እያላችሁ።
ተመለሳችሁ ዘና ስትሉ በዚያ ዓለም በመኖሪያችሁ
ሞት ከእኔና ከእናንተን ማስወገድ የማይቻለው ምን እንደሆነ ያኔ ታውቁታላችሁ።
እዚህ ያያችሁት ከምድሩ ዓለም እጅግ የራቀ ነውና
ተዉኝና ሒዱ፣ ከዚህ በሰላም ሒዱ።
መጋቢት 3 ፥ 2011
ትርጉም ብሩክ በየነ

No comments:
Post a Comment