ወርሐ ግንቦት
ግንቦት ፩
·
፲፱፻፳፰ ዓ/ም - የኢጣልያ ንጉሥ ቪክቶርዮ ኢማኑኤል ሣልሣዊ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ እና ግዛት በኢጣልያ አስተዳደር ሥር የሚያደርግ አዋጅ አስንገረው፣ ይሄንኑ አዋጅ ለዓለም መንግሥታት እንዲሰራጭ አዘዙ። የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትነት ማዕርግ ከዚህ ዕለት ጀምሮ የእሳቸውና የወራሾቻቸው እንደሆነ፣ የኢትዮጵያም ሕዝብ እና ግዛት በእንደራሴ እንደሚታደደር በዚሁ አዋጅ ይፋ ተደርገ።
·
፲፱፻፷፫ ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስ ስርዓተ ሲመት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናውኗል።
·
፲፱፻፺፫ ዓ/ም - በጋና ርዕሰ ከተማ አክራ የእግር ኳስ ሜዳ በሚካሄድ ጨዋታ ላይ ተመልካች ሕዝብ በዳኛው ውሳኔ ባለመስማማቱ የተነሳውን ረብሻ ለማብረድ፣ ፖሊሶች የተኮሱት የጢስ ቦምብ ሕዝቡን የባሰውን ሲያተራምሰው በተከሰተው ትርምስና የሰው ግፊያ ፻፳፱ ሰዎች ተቸፍልቀው ህይወታቸውን አጡ።
·
፲፰፻፵፬ ዓ/ም - ራስ መኮንን ከ ልዕልት ተናኘወርቅ ሣህለ ሥላሴ እና ከደጃዝማች ወልደሚካኤል ወልደ መለኮት ጎላ ወረዳ ደረፎ ማርያም በሚባል ሥፍራ ተወለዱ።
ግንቦት ፪
·
፲፱፻፹፮ ዓ/ም - ለሃያ ሰባት ዓመታት በእሥራት የቆዩት ኔልሰን ማንዴላ ለአገራቸው ደቡብ አፍሪቃ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚደንት በመሆን ቃለ-መሐላቸውን ፈጸሙ።
ግንቦት ፫
·
፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ “የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጣልቃ ገቦች በአገሪቱ ጉዳይ ውስጥ እየገቡ አስቸግረዋል በሚል መነሻ የፈረንሳይን፤ አሜሪካን፤ ግብጽን፤ የሶቪዬት ሕብረትን፤ የብሪታኒያን እና የዩጎዝላቪያን የልዑካን አለቆች ሰብስበው አነጋገሩ። በማግሥቱ ይፋ የተደረገው ጽሑፋዊ ቃለ-ጉባኤ አምባሳደሮቹ የተጠሩት “የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ጉዳዮች ላይ የባዕዳንን ጣልቃ ገብነት በብርቱ እንደሚቃወም እና በኢትዮጵያ ግዛትና ሉዐላዊነት ላይ የሚሰነዘሩትን ማናቸውንም እርምጃዎች ለመከላከል ቆራጥ መሆኑን እንዲገነዘቡ ነው።” ይላል።
·
፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከግብጽ ፕሬዚደንት ሳዳት ጋር ለውይይት ወደካይሮ ሲጓዙ፣ እግረ መንገዳቸውን ካርቱም ላይ አርፈው ከፕሬዚደንት ኒሜሪ ጋር ተለወያዩ።
ግንቦት ፬
ግንቦት ፭
ግንቦት ፮
*********
ግንቦት ፯
*********
ግንቦት ፰
·
፲፱፻፰፩ ዓ/ም - በኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማርያም ላይ የመፈንቀለ መንግሥት ሙከራ
ተደረገ።
·
፲፱፻፴ ዓ/ም - ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ምሑር፤ አስተማሪ፤ ደራሲ እና የቅዱስ ያሬድ የሙዚቃ ትምሕርት ቤት መሥራች ዶክቶር አሸናፊ ከበደ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ተወለዱ።
·
፲፱፻፺ ዓ/ም - ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ምሑር፤ አስተማሪ፤ ደራሲ እና የቅዱስ ያሬድ የሙዚቃ ትምሕርት ቤት መሥራች ዶክቶር አሸናፊ ከበደ በዛሬው ዕለት በተወለዱ በስልሳ ዓመታቸው አረፉ።
ግንቦት ፱
ግንቦት ፲
*********
ግንቦት ፲፩
·
፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የኤርትራ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያጸደቀውን ሕገ-መንግሥቱን በመለወጥ አገሪቱን ከ’ኤርትራ መንግሥት’ ወደ ‘የ ኤርትራ አስተዳደር’ በመለወጥ ወደፊት ሙሉ የኢትዮጵያ አካል ለማድረግ የሚስችላትን ውሳኔ አጸደቀ።
ግንቦት ፲፪
·
፲፬፻፹፮ ዓ/ም - ዓፄ እስክንድር በነገሡ በ፲፮ ዓመታቸው አረፉና በደብረ ወርቅ ተቀበሩ። ሥልጣነ መንግሥታቸውም ወደ ፯ ዓመቱ ልጃቸው ዓምደ ጽዮን ሣልሳዊ ተዘዋወረ። ሆኖም ዓምደ ጽዮን በነገሡ በ፯ ወራቸው ድንገት ስለሞቱ አልጋው ወደ አባታቸው ወንድም አጼ ናዖድ ተላልፏል።
ግንቦት ፲፫
·
፲፱፻፳፱ ዓ/ም - የየካቲት ፲፪ ቀን አዲስ አበባ ላይ ግራዚያኒ ላይ የተወረወረውን ቦምብ ምክንያት በማድረግ ፋሺስቶች ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገብተው ፫፻፳ መነኮሳትን በግፍ ጨፈጨፉ፤ ገዳሙንም አቃጠሉ።
·
፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የአሩሲ ጠቅላይ ግዛት (አሁን አርሲ) እንደራሴ ሆነው የተሾሙትን አቶ ተስፋ ቡሸን የጠቅላይ ግዛቱ ሕዝብ አባሮ አስወጣቸው።
·
፲፱፻፹፫ ዓ/ም - የኢሕዲሪ (የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ) ፕሬዚዳንትና የኢሠፓ (የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ) ዋና ጸሐፊ የነበሩት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አገር ጥለው በመኮብለል ዚምባብዌ ገቡ።
ግንቦት ፲፬
*********
ግንቦት ፲፭
*********
ግንቦት ፲፮
ግንቦት ፲፯
·
፲፱፻፷፫ ዓ/ም - በአዲስ አበባ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ፤ በከተማው አውቶብሶች እና ንብረት ላይ ጉዳት አደረሱ። በዚህም ምክንያት አሥር ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤቶች ተዘጉ።
ግንቦት ፲፰
·
፲፯፻፲፫ ዓ/ም - ከወህኒ በወረዱ በሁለተኛው ቀን የአፄ አድያም ሰገድ ኢያሱ ልጅ አፄ በካፋ ጎንደር ላይ በጳጳሱ አባ ክርስቶዶሉ እና እጨጌ ተክለ ሃይማኖት ተቀብተው ነገሡ።
ግንቦት ፲፱
·
፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኤርትራ ነጻ አውጪ ግንባር አባላት ጊንዳ ውስጥ በሉተራን ሚሲዮን ሆስፒታል ውስጥ የሚሠራ ዶክቶርን የመጥለፍ ሙከራ ሲያደርጉ አንዲት አስታማሚ (ነርስ) ተገደለች።
ግንቦት ፳
·
፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው መኮንን መንግሥት የሚኒስትሮችን ለውጥ ይፋ አደረገ። ከነዚህም አንዱ የአገር ግዛት ሚኒስትር የነበሩትን ደጃዝማች ዘውዴ ገብረ ሥላሴን ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መዛወር ያካትታል።
ግንቦት ፳፩
ግንቦት ፳፪
·
፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመጽ ቆስቋሽነት የተሠየመው የሙስና እና የሥልጣን በደል መርማሪ ሸንጎ ሥራውን የሚመራበት ሕግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ።
ግንቦት ፳፫
ግንቦት ፳፬
·
፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በ፳ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በትልቅነቱ በኢትዮጵያ ታሪክ አቻ የሌለው በ”ሪክተር” ሚዛን ስድስት ነጥብ ሰባት ያስመዘገበ የመሬት እንቅጥቅጥ ተከስቶ የማጀቴን ከተማ ሲደመስስ፣ በጎረቤቷ ካራቆሬ ደግሞ ከመቶ እጅ አርባ አምሥቱ መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። ከካራቆሬ በስተሰሜን የሚያልፈው ዋናው የአዲስ አበባ፦ አስመራ መንገድ እና ድልድዮችም እንቅጥቅጡ ባስከተለው የድንጋይ ናዳ ወደ አሥራ ሰባት ኪሎ ሜትር ርዝመት ላይ አደጋ ደረሰ
ግንቦት ፳፭
·
፲፱፻፳፩ ዓ/ም - የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የመጀመሪያዎቹን አራት ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት (አቡነ አብርሓም - የጎንደር እና የጎጃም፤ አቡነ ይስሐቅ - የትግሬ እና የስሜን፤ አቡነ ጴጥሮስ የወሎ እና የላስታ፤ አቡነ ሚካኤል - የኢሉባቡር እና የምዕራብ ኢትዮጵያ) ከግብጻዊው ሊቀ ጳጳሳት (አቡነ ቄርሎስ)ጋር ካይሮ ላይ ተቀብተው ተሾሙ።
ግንቦት ፳፮
ግንቦት ፳፯
·
፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በመከላከያ ሚኒስትር ጄኔራል ሊዩቢቺክ የሚመራ የዩጎዝላቪያ ወታደራዊ ቡድን ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ጋር አዲስ አበባ ላይ ያካሄደውን የአራት ቀን ውይይት ጀመረ።
ግንቦት ፳፰
·
፲፱፻፹፫ ዓ/ም - በአዲስ አበባ ከተማ በቆሎ ሰፈር አካባቢ የሚገኝ ወታደራዊ
ካምፕ ውስጥ በተነሣ ፍንዳታ በርካታ ሕይወት አለፈ፤ ብዙ ቤቶችና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።
ግንቦት ፳፱
*********
ግንቦት ፴
No comments:
Post a Comment