Thursday, December 27, 2018

አዲስ አባ

አዲስ አባ
 
ለፈላጊዋ ሰፍታ ለተፈላጊዋ ጠባ
አዲስ ከተማ ጫካ ሸገር ወጣ ገባ
ሲመሽ እየነጋች በቀን ሌት ደምቃ
ሀብታም ከነዳይ አንድ ላይ አምቃ
አዱ ገነት የአምባዎች ሁሉ አናት
ሰማይ ጠቀስ ያገር እርግብግቢት
ባራት አፍ ውጣ ባራት አፍ ተፍታ
ያገር እስትንፋስ ያገር ልብ ትርታ
ሚሊዮን ፀንሳ ሚሊዮን ወልዳ
ሚሊዮን አስይዛ ሚሊዮን ሰዳ
በሰፈር መንደሯ ራሷን አዳቅላ
ሽቅብ ቁልቁል ወርዳ ተሰቅላ
የአብራኳን ከጉዲፈቻ እኩል ዐይታ
ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሁሉንም አንሥታ
እኩይ ከጻዲቅ ጡቷን የምታጠባ
የሰው ዘር እናት አዲስ፣ አዲስ አባ
ለፈላጊው ሰፍታ ለተፈለገው ጠባ
አዲስ የሰው ጫካ ሸገር ወጣ ገባ
ትሳስ ኪዳነምህርት ለዐሥራ ሰባት አጥቢያ ተሌቱ 8 ሰዓት ተአምስት ከእንቅልፍ መሃል መጥቶ የተቸከቸከ (2018)
ብሩክ በየነ

No comments:

Post a Comment