የኤፍቢአይ
ምልምል ሠራተኛው
ሦስት የደኅንነት
ሠራተኞች የኤፍቢአይ የደኅንነት ሠራተኛ ሆነው ለመቀጠር ትንሽ ነው የቀራቸው። ለቀናት ከቆየ ከባድ ምርመራና ቃለ መጠይቅ ፈተና
በኋላ ታማኝ የኤፍቢአይ ሠራተኛ መሆን መቻላቸውን ለማረጋገጥ የመጨረሻ መውሰድ ያለባቸው አንድ ከባድ ፈተና እንደሚቀራቸው ይነገራቸዋል።
የኤፍቢአይ ዋናው የደኅንነት ሹም የሆኑት አለቃ የመጀመሪያውን ምልምል ሠራተኛ ወደ አንድ ነጠል ያለ ክፍል አጠገብ ብቻውን ይወስዱትና
በሩ ላይ ሲደርሱ ሽጉጥ በእጁ ያስቀምጡለታል። በመቀጠልም «እዚህ ክፍል ውስጥ ትገባና ሚስትህን ገድለሃት ውጣ ! የኤፍቢአይ ትዕዛዝ
ነው። »
ሰውዬው
ክፍሉ ውስጥ ሲገባ ሚስቱ አለች። ወዲያው ተመልሶ ይወጣና « ይቅርታ ጌታዬ ! ሥራው ይቅርብኝ ፣ በጭራስ ሚስቴን መግደል አልችልም።
» ይልና ከዋናው የኤፍቢአይ መሥሪያ ቤት ወጥቶ ይሄዳል።
ሁለተኛው
ሰውዬም በተመሳሳይ አካሄድ ፈተናው ይቀርብለታል። እሱም ሚስቱን ካያት በኋላ ሚስቱ ከሥራው እንደምትበልጥ በማመን እሱም እምቢኝ
አሻፈረኝ ብሎ ሥራውን ጥሎ ይሄዳል።
ሦስተኛው
ሰውዬ ሽጉጡ ተሰጠውና እንደተለመደው ሚስቱን እንዲገድል ተነግሮት ያለችበት ክፍል ገባ። ወዲያውኑ ስድስት የጥይት ጩኸት ተሰማ።
ከትንሽ ሰከንዶች በኋላ ዋናው የኤፍቢአይ ኃላፊ ክፍሉ ውስጥ ጓ ! ድም ! ቡም ! ጓ የሚል ከፍተኛ ጓጓታ መስማት ጀመረ። ከትንሽ
ደቂቃዎች በኋላ ሰውዬው ደም በደም ሆኖ ከክፍሉ ውስጥ ወጣ።
«ምንድነው
የተፈጠረው ? » ዋናው ኃላፊ ጠየቀ።
«ጌታዬ
ሽጉጡን የሰጥዎት ሰው የማይረባ ወታደር ነው። ሁሉም ጥይት ቀልሃ አልባ ባዶ ነበር። ዋናው ነገር በታዘዝኩት መሠረት በተቀመጠችበት
ወንበር ገድያታለሁ። »
ትርጉም
በብሩክ በ. ግንቦት ፲፭ ፣ ፳፩፰ [ቀኑ የራሴ ነው]
[The English Version]
The FBI AGENT
Three men want to
become agents for the FBI. After a day of intensive interviews, they are told
there is one more test to prove their dedication to the FBI. The head FBI agent
takes the first guy into a private room. He hands him a gun and says, “Go into
that room and kill your wife.”
The guy says, “No way”
and leaves FBI headquarters.
The second guy goes
through the same proceedings. He walks into the second room, but on seeing his
wife decides that she is worth more than a good job and he too refuses.
Finally, the third guy
is given the gun and told to kill his wife. He walks into the second room and
six shots are heard. A few seconds later, the head FBI agent hears crashing and
banging from the room. After a few minutes, the guy comes out of the room. “What happened?” asks the FBI agent.
“Some idiot loaded the
gun with blanks. I had to kill her with the chair!”
No comments:
Post a Comment