Friday, May 4, 2018

የአንድ ታላቅ ብልህ ሰው ምክር ለወንዶች

የአንድ ታላቅ ብልህ ሰው ምክር ለወንዶች
ከፈስ ቡክ (ፌስቡክ አላልኩም ልብ ይበሉ) ተወስዶ የተመለሰ ትርጉም 
የተርጓሚ እንጂ የቀልባሽ አይሁንብኝ አቦ !
1. ልጄ ሆይ ፥ እቺን ዐለም እለውጣለሁ ብሎ ውስጥህ የሚንተከተክ ከሆነ እነሆ ስታገባ በፊት አድርገው። ካገባህ በኋላ እንኳን ዐለምን የቴሌቪዥን ጣቢያን እንኳ መቀየር አትችልም። [ቃና ወይ ምርቃና ምርጫው ያንተ ነው]
2. ሚስትህ ስታወራ ማዳመጥ ልክ በድረገጽ ላይ ያለውን የስምምነት ውል እንደማንበብ ያለ ነገር ነው። ቢገባህም ባይገባህም ተስማምቼያለሁ ከማለት ውጭ ሌላ ምርጫ የለህም። 
3. ቼዝ የሚባለው ጨዋታ በዐለም ላይ ካሉት ጨዋታዎች ሁሉ የምስኪኑን ባል በቤት ውስጥ ያለውን የአባወራነት ሚና በትክክል ይገልጸዋል። ምስኪኑ ንጉሥ በአንድ ጊዜ አንዴ ብቻ መንቀሳቀስ ይችላል። ታላቋ ንግሥት በፈለገችው አቅጣጫ እንደፈለገች የመብረር እና የፈለገችውን የማድረግ መብቷ እንደተከበረ ሆኖ።
4. ሁሉም ወንዶች ልበ ሙሉ ናቸው። ምንም ዐይነት የሚያስፈራ “ሆረር” የሚባል ፊልም አያንበጫብጫቸውም። ግን አቶ ሚስት 3 ሚስድ ኮል እንዳላት የእጅ ስልካቸው ላይ ካዩ ልባቸው ከደረት ወደ ካልሲ ሲሸጎጥ ኤድና ሞል ያለው ኤይት ዲ ሲኒማ እንኳ እንደዛ አያስፈራቸውም።
Adopted by Brook B. May 4, 2018



No comments:

Post a Comment