Thursday, May 31, 2018

ቀብር

ለአንዲት ድንገት የሞተች ሴት የቀብር ሥነ ሥርዓት እየተከናወነ ነው። በሥነ ሥርዓቱ ማብቂያ ላይ አስክሬን ተሸካሚዎቹ አስክሬኑን ከቤተ ክርስቲያኑ ይዘውት ወደ ውጭ እየወጡ ሳሉ ድንገት ከበሩ አጠገብ ከነበረው ግድግዳ ጋር ይጋጩና ሬሳ ሳጥኑን ክፉኛ አንገጫገጩት።
ድክም ያለ የሲቃ ድምፅ ሰሙ። የሬሳ ሣጥኑን ከፈቱና ሴትዬዋ እንዳልሞተች ዐዩ! ከዚህ በኋላ ለዐሥር ድፍን ዓመታት በሰላም ኖራ በመጨረሻ እንደገና ሞተች።
በድጋሚ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በተመሳሳይ ቤተ ክርስቲያ እየተከናወነ ከቆየ በኋላ በስተመጨረሻ ላይ ሬሳ ሣጥን ተሸካሚዎቹ አስክሬኑን ተሸክመው ለመውጣት ሲሰናዱ ባልየው ጫክ ብሎ ምን ቢላቸው ጥሩ ነው ?

“ግድግዳ ጋር እንዳታጋጩት አሁንም!”

English version

A funeral service is being held for a woman who has just passed away. At the end of the service, the pallbearers are carrying the casket out when they accidentally bump into a wall, jarring the casket.
They hear a faint moan. They open the casket and find that the woman is actually alive! She lives for ten more years and then finally dies.
A ceremony is again held at the same place, and at the end of the ceremony, the pallbearers are again carrying out the casket. As they are walking, the husband cries out, “Watch the wall!”

Thursday, May 24, 2018

ሐበሻ

ሐበሻ
ከነካኩት እንጂ ካልነኩት አይነካም
ሐበሻ ራሱን እንጂ የሰው ዘር አይጠላም
ልብ እና ኩላሊት እንደ ፊት አይታይም
አይቻልም እንጂ ቢቻል ነበር መልካም
የፊጢኝ ታስሮ በውቅያኖስ ዋና
በፋኖስ መለወጥ የፀሐይን ፋና
የነብርን ጅራት ለቆ ሩጫ
አህያ ሰፈር ገብቶ እርግጫ
ጅብን አቅፎ እንቅልፍ
እባብን አምኖ ማሳለፍ
ሐበሻን ሐበሻ በሾኬ ካልጠለፈ
ወንድሙ ላይ ታርጋ ካልለጠፈ
ቃሉን አጥፎ መንገድ ካላጠፈ
አጥፎም በሽብር ደም ካልተራጨ
ሴራ ሸርቦ እንደ ነጠላው ካልቋጨ
ጎረቤቱ በበላው ሆዱን ካልታመመ
እንዲያሽረው ኮሶ በኮሶ ካልታከመ
እንዳይበለጥ በዘመዱ ተንኮል ካልሸረበ
መርፌ ሰክቶ በግድግዳ ጠንቋይ ካልቀለበ
ባላንጣ ሆኖ መሳይ ባልንጀራ
ለታይታ ፍቅሩ መዐድ ካልተጋራ
ግራ እየገባው ካላጋባ ግራ
ዐረብን አርጎ ዲኑ
በራሱ መጨከኑ
ፈረንጅ አርጎ መልአኩ
የጠፋበት ሚዛን ልኩ
ለቀብር ከሰነፈ ጉልበቱ
በሞተ ከጨከነ አንጀቱ
ምቀኛ ካሳጣው ጸሎቱ
ጥሬ ቢያጣ ካልቆረጠመ ጥራጥሬ
ታሪኩን ካላወጋ ተቀምጦ በወሬ
እና ይኼን ሁሉ ዐውቀው እንዳይርቁት
ክፋቱን ብቻ ዐይተው እንዳይጠሉት
ገዳም ገብቶ መላክ ያናግራል
ሰማይ ቤት በምድር ያደናግራል 
የፈጣሪ ስም ጠርቶ ወኔህን ይሰልባል
ችግር ፈጥሮ ራሱ ባካል
ለነፍስ ምስጢር ይፈታል
ምሥራቅ ሲሉት ምዕራብ
ሰሜን ሲሉት ደቡብ
ያለም እንደርቢ አዋኪ ሸዋኪ
እውነትን አንቆ እምነትን ሰባኪ
ሐበሻን ዐውቃለሁ ማለት ዘበት
ብልቃጥ ያልገባ መርዝና መዳኒት
ኋላ ሲሉት ከፊት ከፊት ሲሉት ኋላ
ታንገት ተሽጦ በፍቅር አንገት የሚቀላ
እንብላ ብሎ በአንደበቱ ስተህ ብትበላ
በሆድህ ስም ሰጥቶ አፈር ድሜ የሚያስበላ
ይኼን ዘመን የማይፈታው እንቆቅልሽ
ተዉት ባለበት ሳይነጋ እንዳይመሽ
አይነኬን ነክተን ቀልባችን እንዳይሸሽ
ተሰፍርን ዝም አልን በሥዩመ እዝጊ ዘሐበሽ
ጉያችን ጣፍጦ ገብቶ ሲያቀረናን እንደ አብሽ
ዓሣን ካልበሉት በብላት
ሐበሻን ካላወቁ በሥርዓት
ሕይወትም ይሆናል ለግጥ ዕውቀትም ሁሉ ከንቱ
ሐበሻን ልብ ብለው ካላዩ ከሥር መሠረቱ
ሕይወትም ይሆናል ለግጥ ዕውቀትም ሁሉ ከንቱ
ሐበሻን ልብ ብለው ካዩ ከጥንት ከጠዋቱ
ያው ዞሮ ዞሮ ድንቅነሽ ናት እናቱ



የቅዱስ መርቆርዮስ ለታ ትሳስ 2018 
የሐበሻ ስምንት ዐመት ኋላ መቅረት፣ 
አለው አንዳች ነገር አለው አንዳች ብላት
ብሩክ በ.

Wednesday, May 23, 2018

የኤፍቢአይ ምልምል ሠራተኛው


የኤፍቢአይ ምልምል ሠራተኛው

ሦስት የደኅንነት ሠራተኞች የኤፍቢአይ የደኅንነት ሠራተኛ ሆነው ለመቀጠር ትንሽ ነው የቀራቸው። ለቀናት ከቆየ ከባድ ምርመራና ቃለ መጠይቅ ፈተና በኋላ ታማኝ የኤፍቢአይ ሠራተኛ መሆን መቻላቸውን ለማረጋገጥ የመጨረሻ መውሰድ ያለባቸው አንድ ከባድ ፈተና እንደሚቀራቸው ይነገራቸዋል። የኤፍቢአይ ዋናው የደኅንነት ሹም የሆኑት አለቃ የመጀመሪያውን ምልምል ሠራተኛ ወደ አንድ ነጠል ያለ ክፍል አጠገብ ብቻውን ይወስዱትና በሩ ላይ ሲደርሱ ሽጉጥ በእጁ ያስቀምጡለታል። በመቀጠልም «እዚህ ክፍል ውስጥ ትገባና ሚስትህን ገድለሃት ውጣ ! የኤፍቢአይ ትዕዛዝ ነው። »

ሰውዬው ክፍሉ ውስጥ ሲገባ ሚስቱ አለች። ወዲያው ተመልሶ ይወጣና « ይቅርታ ጌታዬ ! ሥራው ይቅርብኝ ፣ በጭራስ ሚስቴን መግደል አልችልም። » ይልና ከዋናው የኤፍቢአይ መሥሪያ ቤት ወጥቶ ይሄዳል።

ሁለተኛው ሰውዬም በተመሳሳይ አካሄድ ፈተናው ይቀርብለታል። እሱም ሚስቱን ካያት በኋላ ሚስቱ ከሥራው እንደምትበልጥ በማመን እሱም እምቢኝ አሻፈረኝ ብሎ ሥራውን ጥሎ ይሄዳል።

ሦስተኛው ሰውዬ ሽጉጡ ተሰጠውና እንደተለመደው ሚስቱን እንዲገድል ተነግሮት ያለችበት ክፍል ገባ። ወዲያውኑ ስድስት የጥይት ጩኸት ተሰማ። ከትንሽ ሰከንዶች በኋላ ዋናው የኤፍቢአይ ኃላፊ ክፍሉ ውስጥ ጓ ! ድም ! ቡም ! ጓ የሚል ከፍተኛ ጓጓታ መስማት ጀመረ። ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ ሰውዬው ደም በደም ሆኖ ከክፍሉ ውስጥ ወጣ።
«ምንድነው የተፈጠረው ? » ዋናው ኃላፊ ጠየቀ።
«ጌታዬ ሽጉጡን የሰጥዎት ሰው የማይረባ ወታደር ነው። ሁሉም ጥይት ቀልሃ አልባ ባዶ ነበር። ዋናው ነገር በታዘዝኩት መሠረት በተቀመጠችበት ወንበር ገድያታለሁ። »
ትርጉም በብሩክ በ. ግንቦት ፲፭ ፣ ፳፩፰ [ቀኑ የራሴ ነው]
[The English Version]
 The FBI AGENT
Three men want to become agents for the FBI. After a day of intensive interviews, they are told there is one more test to prove their dedication to the FBI. The head FBI agent takes the first guy into a private room. He hands him a gun and says, “Go into that room and kill your wife.”

The guy says, “No way” and leaves FBI headquarters.

The second guy goes through the same proceedings. He walks into the second room, but on seeing his wife decides that she is worth more than a good job and he too refuses.

Finally, the third guy is given the gun and told to kill his wife. He walks into the second room and six shots are heard. A few seconds later, the head FBI agent hears crashing and banging from the room. After a few minutes, the guy comes out of the room. “What happened?” asks the FBI agent.

“Some idiot loaded the gun with blanks. I had to kill her with the chair!”

Friday, May 4, 2018

የአንድ ታላቅ ብልህ ሰው ምክር ለወንዶች

የአንድ ታላቅ ብልህ ሰው ምክር ለወንዶች
ከፈስ ቡክ (ፌስቡክ አላልኩም ልብ ይበሉ) ተወስዶ የተመለሰ ትርጉም 
የተርጓሚ እንጂ የቀልባሽ አይሁንብኝ አቦ !
1. ልጄ ሆይ ፥ እቺን ዐለም እለውጣለሁ ብሎ ውስጥህ የሚንተከተክ ከሆነ እነሆ ስታገባ በፊት አድርገው። ካገባህ በኋላ እንኳን ዐለምን የቴሌቪዥን ጣቢያን እንኳ መቀየር አትችልም። [ቃና ወይ ምርቃና ምርጫው ያንተ ነው]
2. ሚስትህ ስታወራ ማዳመጥ ልክ በድረገጽ ላይ ያለውን የስምምነት ውል እንደማንበብ ያለ ነገር ነው። ቢገባህም ባይገባህም ተስማምቼያለሁ ከማለት ውጭ ሌላ ምርጫ የለህም። 
3. ቼዝ የሚባለው ጨዋታ በዐለም ላይ ካሉት ጨዋታዎች ሁሉ የምስኪኑን ባል በቤት ውስጥ ያለውን የአባወራነት ሚና በትክክል ይገልጸዋል። ምስኪኑ ንጉሥ በአንድ ጊዜ አንዴ ብቻ መንቀሳቀስ ይችላል። ታላቋ ንግሥት በፈለገችው አቅጣጫ እንደፈለገች የመብረር እና የፈለገችውን የማድረግ መብቷ እንደተከበረ ሆኖ።
4. ሁሉም ወንዶች ልበ ሙሉ ናቸው። ምንም ዐይነት የሚያስፈራ “ሆረር” የሚባል ፊልም አያንበጫብጫቸውም። ግን አቶ ሚስት 3 ሚስድ ኮል እንዳላት የእጅ ስልካቸው ላይ ካዩ ልባቸው ከደረት ወደ ካልሲ ሲሸጎጥ ኤድና ሞል ያለው ኤይት ዲ ሲኒማ እንኳ እንደዛ አያስፈራቸውም።
Adopted by Brook B. May 4, 2018



Wednesday, May 2, 2018

የFacebook ቋንቋ




Facebook ቋንቋ
በአማርኛ ሲተረጎም ኪ ኪ ኪ
1. SIGN IN --- ቤቶች
2. CHAT --- ጅንጅን
3. LIKE --- ወንዳታ
4. UNFRIEND---
ዞር በል
5. BLOCK ---
ይድፋህ
6.POKE ---
ነቃ በል
7. TAG ---
አቋቁሙን
8. NOTIFICATION ---
ያልሰማ ይስማ
9. STATUS ---
ድራሽ
10.PROFILE ---
ሁለንተናዬ
11. SEARCH ---
እንደ በሬ ጋጠው
12.ADD FRIEND ---
ሴት ልጃችሁን ዳሩልን
13. Password -
መቀርቀሪያ
14. share -
ተባበሩን
15. SIGN OUT ---
አገር ምድሩ ይስፋላችሁ !
ብለን እንወጣለን

በትግርኛ እንዲህ የተጻፈው የተተረጎመ

ቋንቋ Facebook
ብትግርኛ እንትትርጎም
1. SIGN IN --- ኣቱም ዓዲ

2. CHAT --- ጨጨም

3. LIKE --- የዒስ

4. UNFRIEND--- ችድ ልየኻ
5. BLOCK ---
ኣብ መቓብርካ ደው ኣየብለኒ
6.POKE ---
ተበራበር
7. TAG ---
ደው ኣባህሉና
8. NOTIFICATION ---
ለይሰማዕኻ
9. STATUS ---
ሃለዋት
10.PROFILE ---
ኩለንተናይ
11. SEARCH ---
ብዕራይ ልኣተዎ
12.ADD FRIEND ---
ጓልኻቱም ሃቡና
13. pasward -
መሸጎር
14. share -
ተሓባበሩና
15. SIGN OUT ---
ይግፈሓልኹም !
ይግፈሓልኹም እልና ንወፂእ