Thursday, November 17, 2016

Us vs Them with Amharic translation



Us vs Them
My childhood was not an anxious place, 
though I lay
              in my bed, awake, thumbing
my sheets like beads, wondering when the sun
              imploded
              would Russian astronauts be OK,
they in their Sputniks, with their space dogs,
              they that chased their own tail 
around this water bowl
              we call Earth. When I was a child,

in elementary school
             we practiced a type of
             protection 
called Duck and Cover, 
where we huddled
                             under desks in case of a nuclear
attack
by the Russians. They were communists,
              had the bomb, and were evil

Reagan told us 
from the small grave
                 of a TV screen.

In the sixties, Nixon said the same
              thing, and the Panthers
              countered with "the Viet Cong never 
called me nigger" With their picks
like unclenched fists,
              with their afros like the plume of an atom bomb, 
they scared white and black folks alike. It is 2014,

and America is still scared of
                            the Russians and black people;
              now the American Dream is to be debt free, 
which I am not, nor may ever be, but at least
              I'm no longer afraid of the Russians.


የእኛና የእነሱ ፍጥጫ
በዴቪድ ቶማስ ማርቲኔዝ
ልጅነቴ አልነበረም አስጨናቂ ቦታ፣ 
ምንም እንኳ ሳልተኛ ብተኛ
              በቁም ባልጋዬ ባንቀላፋ፣ አንሶላዬን
ውስጥ ብንከባለል እንደ ዶቃ፥ ፀሐይ ስትወድቅ ያኔ ፈንድታ
             ይበልጥ ያሳሰበኝ ውስጤን ቀልቤን ገዝቶ
              የሩሲያ ጠፈርተኞቹ ምን ይውጣቸው ይሆን ከቶ፣
በስፑትኒካቸው ውስጥ፣ ከነጠፈር ውሻዎቻቸው፣
              እኒያ የገዛ ጭራቸውን የሚያሳዱት 
እኛ መሬት በምንላት፣ የሚዞሩት
              በዚያች የውሃ ጉድጓድ። ልጅ እያለሁ ገና ጨቅላ፣
በተማሪ ቤት የነበረው ውሪ በሞላ
ዱክ እና ካቨር የተባለ ልምምድ
             ስንለማመድ፣ 
ድንገት ሩሲያዎች በኒውክሊየር ቢያጠቁን፣
ብለን ከዴስክ ሥር ተመራርተን ታጉረን። 
እነሱ ኮሚኒስት ናቸው፣
                             ደሞም ቦምብ አላቸው
በዚያ ላይ አረመኔ፣ ክፉ ናቸው

ከሚጢጢው መቃብር ውስጥ ሆኖ 
ከቴሌቭዥኑ መስኮት
ሬገን ነው የነገረን ይኼን እውነት።

በፊትም በስልሳዎቹ፣ ኒክሰን ይህንኑ ብሎ ነበር
              እነዚያ ፓንተር የሚባሉት ሲነሱ “ማንም ቬትናም
             ኔግሮ ብሎ ጭራሽ አልሰደበኝም” ሲሉ 
እንደ መሃመድ ዓሊ ቡጢ ሲምዘገዘግ ምርጫቸው
              አፍሮዋቸው፣ እንደ አቶም ቦምብ ደመና ሲያደምን በላያቸው ፣ 
ያስፈሩ ነበር ጥቁርንም ነጩንም ዘር።
አሁን ግን ሃያ አሥራ አራት ነው ዘመን ሲቆጠር፣

ዛሬም ትፈራለች አሜሪካ፣ የሩስያና ጥቁር ሰዎችን ፣
              ያ ታላቁ የአሜሪካ ሕልም የሚሉትን
       ሕልም ነው አሁን፣ ከዕዳ ነጻ የመሆን
እኔም ከዕዳ ነጻ አይደለሁም፣
ወደፊትም አልሆንም፣
             ቢያንስ ግን አሁን፣
ሩሲያዎችን
 ከእንግዲህ አልፈራቸውም።

ኖቨምበር 15፣ 2016 ተተረጐመ


የአንድ አበሻ አጭር የሕይወት ታሪክ



የአንድ አበሻ አጭር የሕይወት ታሪክ

ምዕራፍ አንድ፦
ተዕለታት አንድ ቀን
ከቀናት መካከል
ባንድ ቅዳሜ ቀን
ተፀነሰ ድንገት ሳይታሰብ ሳይወጠን
ወላጆቹ አሉ አንድዬ ነው የሰጠን
በቦታው አልነበረን፣ እኛ ምንም አላየን!!

ምዕራፍ ሁለት፦
ተዕለታት አንድ ቀን
ከቀናት መካከል
ባንድ አፍለኛ ቀን
ተወለደ እንደ ሰው
ሳይረጋገጥ ማን እንደፈጠረው
ካባት ከናቱ ነው?
ወይስ ከላይ አለ የወረወረው?

ድክ ድክ ብሎ ቆመ
እናም. . .  እናም
አደገ እንደ ምንም ሆዱን እየራበው
ሌት ተቅን ዕንቅልፍ የሚነሳው
ሆድ ሆኖት ባለንጣው
አደገ እንደም ምንም
ማጣት ጣት እያስመሰለው
ከሰው ተራ አውጥቶ፣
እንደ ውሃ ያጣ ተክል እያመነመነው

ምዕራፍ ሦስት፦
ተዕለታት አንድ ቀን
ከቀናት መካከል
ባንድ የሠመረ ቀን
ሰባ እንደ ሠንጋ፣ ጠረቃ አበጠ
እንደ ደረሰ ማሽላ ሆዱ አገነበጠ
እንደ እመጫት ላም አነጠነጠ
እና ከዚያማ አገርና ወንዙንጂ
ወገንና እትብቱን እንጂ. . .
ሆዱን ከቶ አልረሳም
ተመቸው አማረበት ተባለ
ወፈረ ደለበ አንዳች አከለ
ኋላውን ረሳና ራሱን ወደ ላይ ቆለለ
መሬትን ረሳና አየር ላይ ተዘናጐለ

ምዕራፍ አራት፦
ተዕለታት አንድ ቀን
ከቀናት መካከል
ባንድ ጎዶሎ ቀን
ድንገት ጤናው ታውኮ ካልጋ ላይ ዋለ
የነካው ሳይታወቅ ሰውነቱ ሰለለ
ታኪም ከጠበሉ ከቃልቻው አልቀረ
ላንድዬ ምህረት፣ ተቀደሰ፣ ተዘየረ
ጤናው እንዲመለስ ብዙ ተሞከረ
ሆንኮንግ ነው ማነው ታይላንድ የሚሉት
ሄደ ምን ያድርግ ‘ንግዲህ ሂድ ሲሉት
ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ እንደሚሉት
ሆዱ እንደው ጠላቱ ደበቁ ሳይነግሩት

ምዕራፍ አምስት፦
ተዕለታት አንድ ቀን
ከቀናት መካከል
ባንድ ክፉ ቀን
እንደ ሰው ተወልዶ
በሆድ ተቀይዶ
ሲበላ ኖሮ እንደ አሳማ
ድንገት መሞቱ ተሰማ

እነሆ ይኼ ሰው
አጭር ታሪኩ ረዥም ነው
የታመመ ሆዱን ሳያድን
ሳያሽር ወስፋቱን
ያን የተጣባውን
ጠኔውን ሳይቀብረው
ቀድሞ የቀበረው ጠኔው።

ተዕለታት አንድ ቀን
ከቀናት መካከል
ባንድ ክፉ ቀን
መዳኑ ሳይሰማ፣
መሞቱ ተሰማ . . .


አብረን ነውና ይህችን በቡና ያማጥነው
ብሥራት አጥላባቸው ወሮታው ላንተ ነው
ኖቨምበር 17፥ 2016