Monday, June 12, 2017

ለባለወይራ ቅጠሉ ጥምጣማም

ያኔ በሞኝ ዘመን በየዋሆቹ
እረኛው ሲሞት ለበግ ግልገሎቹ
ሕሊና ካገር ሳትሰደድ እውነትም ሳታብድ
አንድ ለብዙ ብዙ ለአንድ ለመኖር ሲገደድ
ለጋራ ጥቅም ለአንድነት ሀብቱ
ሰው ሲሞት ለማተብ ለእምነቱ
የምንትስዬ ቦታ፣ ሚና ግራ ቢገባህ
ዋሾውን አስመሳይ መቅጣት ቢዳዳህ
ያኔ በዛ ዘመን ቅዱስ፣ በተባረከው
"እውነት ማነው ማንትስ?" ነበር ያልከው
ያኔ በዛ ዘመን ሳይረክስ በፊት ሰው
*****
አሁን ግን በዚህ ቆቅ ዘመን በቁራዎቹ
ቄራ በተስፋፋበት ሲሳይ ለአሞሮቹ
አንዲት ብልት ብቻ ናት በጣም ኢምንት
የማይሸጥ የለም አሁን ጸጉርም ዋጋ አላት
*****
እና ባለወይራው ቅጠል ዘውድ፣ የዋሁ ዳኛ
እንኳንም አላየህ በል በሰላም ባለህበት ተኛ
ብትጠይቅ ባትጠይቅ ላንተ ማን ቦታ ሰጥቶ
ራሱን እየቸበቸበ ነው ሰው በዝቶ አብዝቶ
እና በዚህ ደግ ዘመን ሰው አካሉን የሚሸጥበት በችርቻሮ
ማነው ምንትስ ብትል ማን ሊሰማ ማን ሊሰጥህ ጆሮ
ሁሉም ተነካክቷል ራስን ሸጦ ማደርን ተክኖበታል
ዘመነ ምንትስ መሆኑን ምንትስ ሁሉ ገብቶታል
ራሳችንን አንድ ባንድ ቆጥረን ስናከራይ
በልቶ ለማደር ለአዱኛ ክብር ለሆድ ሲሳይ
ባለወይራው ቅጠል ጥምጣም ምንኛ እግዜሩ ወዶሃል
ይኼን ሁሉ ሸቀጥ ሳታይ በጊዜ ከቤቱ ወስዶሃል
ላንዲት ምንትስ ሲገርምህ አገሩ ሁሉ ምንትስ ሆኖልሃል
ሰኔ 3፣ 2017
ለሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
በዓመቱ ላይ የተጨመረው ስምንት ዓመት
ሌላ ምሥጢር የለውም ቀድሞ ነው ለማርጀት
ብ. በየነ

Thursday, March 16, 2017

The Poor's gonna be winning

The poor's gonna be winning

Ethiopia is mourning
'n Babilon seem winning
But underneath the dark sky
I see clouds of hope float by
They say here often
It's deep dark before dawn
Babilon might rejoice before its falling
I know for sure that
The poor's gonna be winning

In remembrance of the victims of landslide on March 11, in Addis Ababa

Friday, March 10, 2017

ፍቅረኛዎት በላይዎት ላይ እየማገጡ እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማረጋገጫ መንገድ (እነዚህን ስድስት መንገዶች በመጠቀም መቼ ከማን ጋር ምን እንዳወሩ ቅልብጭ ብሎ መስማት ይችላሉ)

ፍቅረኛዎት በላይዎት ላይ እየማገጡ እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማረጋገጫ መንገድ (እነዚህን ስድስት መንገዶች በመጠቀም መቼ ከማን ጋር ምን እንዳወሩ ቅልብጭ ብሎ መስማት ይችላሉ)

1. ስልኩን ቀስ ብለው ይቀበሉና *#06# በመጫን አንድም ቁጥር ሳያዛንፉ በትክክል በወረቀት ወይም በስልክዎ ላይ የፍቅረኛዎን ስልክ IMEI ቁጥር ይመዝግቡ።
2. በተመሳሳይ መንገድ የራስዎትን IMEI ቁጥር እና የራስዎትን ስልክ ትክክለኛ የምርት ምዝገባ ተከታታይ ቁጥር (serial number) ከቅንብር (Setting) - > ስለ ስልክ (About Phone) ከሚለው ላይ ይመዝግቡና ይያዙት።
3. የቴሌ ኮምፒውተሮች ለአዲስ ቀን ሥራ ለመጀመር እንደገና መቀነባበር እስከሚጀምሩበት እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ይጠብቁ እና ስልክዎት ላይ #804*00002020*165239*IMEI
በማለት ይጻፉ እና የስልክ ቁጥር እንዲያስገቡ ሞባይልዎት ሲጠይቅዎት የፍቅረኛዎትን ስልክ ቁጥር ያስገቡ (ልብ ያድርጉ ቁጥሩ 09 ብሎ መጀመር የለበትም ትክክለኛው አጻጻፍ (+2519) ብሎ የሚጀምር ነው። ከዚያ በወረቀት ጽፈው የያዙትን የፍቅረኛዎትን የIMEI ቁጥር መሰላል ተጭነው ይጻፊ እና ወደ #804* መልሰው ይላኩ።
4. ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ ኮድ ሲደርስሽ የፍቅረኛሽ ስልክ በእጅሽ ስለገባ ልክ ቀሪ ሒሳብሽን ለማወቅ እንደታደርጊው #804* ተጭነሽ ተደውይና ስልኩ መቀየሩን ሲጠይቅሽ ትክክል መሆኑን 1 ቁጥርን በመጫን ታረጋግጪያለሽ። አዲስ ፒን ኮድ ትፈልጊ እንደሆነ ሲጠይቅሽ አሁንም 1 ን በመጫን አዲስ ኮድ ታስገቢያለሽ ለምሳሌ 8576።
5. ወደ ስልክዎ መልእክት መላላኪያ መተግበሪያ (ኧፕልኬሽን) ይሂዱ እና ያንን ኮድ በማስገባት ወደ #994*02*Voice record ይላኩት። ከትንሽ ቆይታ በኋላ እንደዚህ የመሰለ ኮድ 65231 ቀጥሎም ተከታታይነት ያላቸው ሌላ ቁጥሮች ይደርስዎታል። ይህ በአውቶማቲክ የፍቅረኛዎን ገቢ እና ወጪ ውሂብ (ዳታ) በዝርዝር ዘርግፎ እጅዎ ላይ ያስቀምጥልዎታል። ማስታወሻ፦ ከዚህ ቀጥሎ ያለው በጣም በጥንቃቄ እና ወዲያውኑ ማድረግ ያለብዎት ነው፦
6. እስካሁን ድረስ ይህን እንቶ ፈንቶ እያነበቡ ከቆዩ ያለ ምንም ጥርጥር በቅናት ታመዋል ማለት ነው....ለፍቅረኛዎ፣ ለራስዎም ሆነ ለሰፈር ለአገሩ ደኅንነት ሲባል ብዙ ዕቃ ሳያበላሹ በአቅራቢያዎ ወደ የሚገኝ የአእምሮ ሕክምና መስጫ ተቋም በመሄድ ይመርመሩ።
ጊዜዎትን በማባከን ስለተባበሩኝ አመሰግናለሁ። ኤፕሪል ዘ ፉል ስለ ደረሰ ለማሟሟቅ ነው!
 
 
የተተረጎመበት ጽሑፍ ምንጭ፦
 
HOW TO CHECK IF YOUR PARTNER IS CHEATING ON YOU.
1. Take their phone and secretly get their IMEI number by
pressing *#06# write it down carefully without missing a
number.
2. Get your IMEI number and your last recharge voucher
serial number.
3. Wait until it's midnight when the computers are about to
reset to a new day and then type *00002020*165239*IMEI
number from your phone and the phone numbers of your
partner and their IMEI number then send to 756331.
4. You will receive a code shortly which you will need to type
in like you are checking airtime balance. Eg. *12345# in their
phone and send. It'll show a combination of five numbers
which will be your password.
5. Go to your phone type in the message that code and send
to 3652248. You'll shortly receive a code E.G 65231 at first in
a sequence with other numbers. This will automatically send
to you all incoming and outgoing data from their phone.
NB: This is the most important part;
6. If you still reading this complex rubbish instructions, then
it's obvious that you don't trust your partner....Therefore
find someone you can trust before you get hypertension.
Love is about trust.
Thank you for letting me waste ur time.

Monday, March 6, 2017

ቀስ በቀስ ቻይና በእግሯ ትሄዳለች

ቀስ በቀስ ቻይና በእግሯ ትሄዳለች

የኛና የቻይና የፍቅራችን ጡዘት
የመናበባችን የአንድነታችን ልኬት
ለነሱ ሥራቸው ለኛም ተረት ተረት
ፍሬውን ያፈራል አይቀር እንደ ዘበት
እነ ቹንግ፣ እነ ቹ፣ እነ ፔንግ የዘሩት ፍሬ ሲያፈራ
ቤስት ቢፎር ተብሎ በስቃጥላ ሲታሸግ እንጀራ
ጫት በቡጥሌ ሲሸጥ እንደ ቢራ
የቻይና ሰልዳቶ እድርን ሲመራ
ቹቹ ቹንግ ዕቁብ ሰብሳቢ ዳኛ ሲባል
ገመቹ ቹ ሃን ሲሆን ፓርላማ አባል
ያሳመመን እምዬ ቻይና መልሶ ያከመን ለታ
የቻይና ዲቃላ ክራር እየመታ ሲጫወት ትዝታ
የቻይና ደብተራ ማኅሌት የቆመ ቀን
አበበ ዘይቱንግ ሼኪ ሆኖ ቁርዓን ሲቀራልን
በቻይ-ማርኛ ትምህርት ሲቀዳልን
በቻይ-ግርኛ ሙያ ስንሠለጥን
በቻይ-ሮምኛ የተግባባን ለታ
ቻይንኛ ሲሆን የኛ ፊደል ገበታ
ማዳም ቾንግን ገረንችኤል በሰርግ ሲያገባ
ማዳም ሶንግን ገመቺስ ሊጠብስ ሲያግባባ
ማዳም ፔንግ ጠጅ ጥላ ሊፍታና ሲቆሮ ከጠጡላት
ማዳም ቺንግ አብሲጥ ጥላ እንጀራ ከወጣላት
በተከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን
የባሕል ልብሱን ለብሶ ሸክፎ ኮተቱን
አደባባይ የወጣ ዕለት ሊያሳይ ትርዒቱን
እነ ቡቺ፣ እነ መቻል ከመንደር ሲጠፉ
እነ ውሮ እንደ ዶሮ በንኩቤተር ሲቀፍቀፉ
ነውርና ኩነኔን ኤክስፖርት አርገናቸው
ይሉኝታና ሼምን ጠብሰን በልተናቸው
እና . . . እና አንቺ አለሚቱ ነሽ ጫልቱ የበረገድሽው ጭን
ፍሬ ባያፈራ ነው አብዝቶ የሚቆጨን
አንተም ተክላይ፣ አንተም ቢራቱ፣ የገለባችሁት ቀሚስ
ትንቢቱ ይፈፀም ዘንድ ይወለዳል አንድ ቅዱስ
እና በዚህ መልኩ ዓይናችን ጠቦ. . . ጠቦ. . . ጭራሽ የጠፋ ዕለት
ያ ቅዱስ ቻይና ይመራናል እጃችንን ይዞ አንድ ቀን ወደፊት
ያኔ ከእንቅልፋችን እንነቃ እና እንተርታለን ተረት
ለተረት ማን ብሎን ተክነነዋል ድሮም ከጥንት
«ቀስ በቀስ ቻይና በእግሯ ትሄዳለች
አገር የሚያክል ነገር ክፍለ ሃገሬ ትላለች።»
የካቲት 8፣ 2009 ዓ.ም.
ብሩክ በየነ

Monday, February 13, 2017

JOINT OFFICIAL STATEMENT FROM HUSBANDS/BOYFRIENDS ASSOCIATION OF ZAMBIA OF THIS YEARS VALENTINE 2017

JOINT OFFICIAL STATEMENT FROM HUSBANDS/BOYFRIENDS ASSOCIATION OF ZAMBIA OF THIS YEARS VALENTINE 2017
We the National Association of Husbands And Boyfriends' (NAHAB), wish to announce our annual 3 days maintenance works which will commence on 13 FEB and end on 16 FEB.
Please note that all cell phones will not be working during this period. To this effect so note that all relationship commitments are henceforth suspended and will only be reinstated on the 17 FEB.
we duly apologise for any inconvenience to our wives and girlfrends as well as side chicks who were hoping to be with us on valentines day.
The inconvenience caused is deeply regretted but necessary!!!
NAHAB....Protecting exploited boyfriend and Poor husband rights!!
DISCLAIMER: Notice to all members: if you are unable to reach our offices or customer care line for help that evil day called valentines, the safest way for you to escape these ladies is to pretend to be stuck in Mamba were the road cut into half. If that doesn't work say you are in Sesheke and the only bus 🚌 that reaches there is Mazandhu which is unfortunately suspended so you are stuck. But these women are clever and might pull off a sharp one on you so in the event that you get captured at home, muntu wandi just fall sick. In fact become very sick 😷 and start fitting and vomiting. 😰😰😰😰😰
Spending money unnecessary on flowers and chocolate and red dresses like a fool will not be condoned! Any such member caught doing such will be expelled from our organization. Times are hard in this Edgar Lungu economy. 2017 finance minister Felix Mutati has all encouraged us to tighten our belts. So why should you foolishly blow your hard earned loot?😒😒😒😒
We therefore strongly advice members to show discretion on the unnecessary things they waste money on.
Disclaimer: Please not that should the above instructions backfire on you, the union will not be held liable if you are dumped or go the next six months without sex. However it's your money so do as you please muntu wandi. Our job is to advise and protect. We have done that. The rest is up to you. If you have a good woman she won't pay attention to such nonsense and get mad as to why you did not bringing chocolate, flowers and all such nonsense. But if you have a pushi my guy you are on your own
Signed: NAHAB PRESIDENT
Mwaba Mutale
Cc: Boyfriends Association of Zambia (BBZ)
Cc: Blessers Association of Zambia
Cc: Tired and Bored Husbands Association of Zambia (TBAZ)
Cc: Shipwe Shipwe Union of Loafers and Other Stranded People
Cc: Cheaters Association of Zambia (CHAZ)
Viva NAHAB, Viva!!!!

Sunday, February 12, 2017

የኢትዮጵያ ሙዚቃ ዓይነቶች

ለጨዋታ ያህል?
የኢትዮጵያ ሙዚቃ በፊት በፊት በአራት ቅኝት ይከፈላል ሲባል እንሰማ ነበር፥ ባቲ፣ አምባሳል፣ ትዝታ እና አንቺ ሆዬ።
አሁን አሁን ግን የኢትዮጵያ ሙዚቃ በአምስት መከፈሉ ውስጥ ዐዋቂ ምንጮች ነግረውናል፥
1. ትዝታ (ለሴቶች ብቻ የተፈቀደ፣ ወንድ ምን ትዝታ አለው? ስንቷን አብሮ የተኛትን ሴት በትክክል ያስታውሳል?)
2. አማስል (የአንዱን ብሔር ከሌላው ቀይጦ የሚዘፈን)
3. ፍራሽ አዳሽ (ቃሉ እንደሚለው)
4. አገሬ ሆይ (ለዲያስፖራ የታለመ፣ ጭብጡ ቪዛ ማግኛ ብቻ የሆነ ሙዚቃ ነገር)
5. ባትና ዳሌሽ (የሰውነት አካላት መዘርዝር ወይም በፈረንጅኛ ሜኑ)
ምን ትላላችሁ ጎበዝ?

*Menstruation Testimony!* የጌታ ምስክርነት

የጌታ ምስክርነት

በቤተክርስትያን የምስክርነት ቃል የሚሰማበት የአምልኮ ጊዜ ላይ የፓስተሩ የ16 ዓመት ልጅ ወደ መድረኩ ወጣች እና የሚከተለውን ምስክርነት ሰጠች. . .

"የጌታ ስም የተባረከ ይሁን! እየሱስ ጌታ  ነው!"

ሁሉም አማኝ በደስታ ተውጦ "ሃሌሉያ" አለ። ምስክርነቷን ቀጠለች፦

"ዕድሜዬ አሥራ ሦስት ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ በማህፀኔ ላይ ከባድ ሕመም በየወሩ ይሰማኝ ነበር። ይህ ብቻ አይደለም በከፍተኛ ደረጃ እደማ ነበር። ስቃዩ እንዴት ከባድ እንደሆነ ለመናገር ቃላት የሉኝም። አንዳንድ ጊዜ ሕመሙ ሳያቋርጥ እስከ አምስት ቀን ሁሉ የሚቆይበት ጊዜ ሁሉ ነበር።

አሁን ግን መጽሐፍ ቅዱስን ከወንድም ቢንያም ጋር እሱ ቤት በጥንቃቄ ካጠናሁ እና እየሱስን እንደ ግል አዳኜ አድርጌ ከተቀበልኩ በኋላ ወደ ጌታ በመጸለይ አሁን ይኸው ላለፉት ሦስት ወራት አንድም ቀን ታምሜ አላውቅም። የሚፈሰኝ ደም ቆሟል። እንደምታዩት እያማረብኝ እና እየወፈርኩ ነው። አሁን ትንሽ ትንሽ ጠዋት ጠዋት ላይ፣ የሚያስመልሰኝን ነገር በማስቆም ጌታ ጤናዬን ሙሉ በሙሉ እንዲመልስልኝ ከወንድም ቢንያም ጋር አብረን እየጸለይን ነው። እንደሚያድነኝም እርግጠኛ ነኝ። የጌታ ስም የተባረከ ይሁን!!!"

በቤተክርስቲያኑ የነበረ መዕምን በሙሉ በጸጥታ ተዋጠ!

ወንድም ቢንያም ከፒያኖው ጀርባ ፌንት ሠራ።

እናትዋ "ነው እንዴ?. . ." 

*Menstruation Testimony!*
During the testimony period in church service; The 16-years
old Pastor's daughter stood up and said....
"Praise the Lord!"
Everybody shouted with joy, "Hallelujah". She continued:
"since the age of 13, I've been experiencing serious pain and
bleeding every month and it was unbearable. At times it
would last for 3-5 days.
But now, after a series of Bible studies and prayers with
brother Solomon in his house, the monthly pains and blood
flow have stopped for more than 3 months now. No more
pain, no more bleeding. You can see I'm even getting fatter
and prettier.
And I'm believing God to perfect my healing as we have
started to pray seriously about the small problem of
vomiting, especially in the morning. Praise the Lord".
The whole church was silent!
Brother Solomon fainted behind the piano.
The mother was like "HaH!!!!