Sunday, February 12, 2017

የኢትዮጵያ ሙዚቃ ዓይነቶች

ለጨዋታ ያህል?
የኢትዮጵያ ሙዚቃ በፊት በፊት በአራት ቅኝት ይከፈላል ሲባል እንሰማ ነበር፥ ባቲ፣ አምባሳል፣ ትዝታ እና አንቺ ሆዬ።
አሁን አሁን ግን የኢትዮጵያ ሙዚቃ በአምስት መከፈሉ ውስጥ ዐዋቂ ምንጮች ነግረውናል፥
1. ትዝታ (ለሴቶች ብቻ የተፈቀደ፣ ወንድ ምን ትዝታ አለው? ስንቷን አብሮ የተኛትን ሴት በትክክል ያስታውሳል?)
2. አማስል (የአንዱን ብሔር ከሌላው ቀይጦ የሚዘፈን)
3. ፍራሽ አዳሽ (ቃሉ እንደሚለው)
4. አገሬ ሆይ (ለዲያስፖራ የታለመ፣ ጭብጡ ቪዛ ማግኛ ብቻ የሆነ ሙዚቃ ነገር)
5. ባትና ዳሌሽ (የሰውነት አካላት መዘርዝር ወይም በፈረንጅኛ ሜኑ)
ምን ትላላችሁ ጎበዝ?

No comments:

Post a Comment