ቡና እና ቦለቲካ
ሥርዓቱ
ጋዋም ሆነ ቡና፣ ቡናካላ ቁጢም ሆነ አሻራ
ሕዝብ
ጥሬ ቡና ነው ለዐሴር ዘር፣ ለንጉሡ የተዘራ።
ከጃቫ
ኢንዶኔዥያ እስከ ሱራኔም ደቡብ አሜሪካ
ከጥንት
እስተ ዛሬ ሲታይ የዚህች ዓለም ቦለቲካ
ተመስሎ
ሲታይ እንደ ቡና ሥርዓት፣
ባለ
ጊዜ ነገሥታት የሚያጣጥሙት፣
ሰልቅጠው
ወቅጠው አፍልተው የሚጠጡት
ሕዝብ ቡና ነው፣ የቡና ዱቄት።
ሥርዓቱ
ጋዋም ሆነ ቡና፣ ቡናካላ ቁጢም ሆነ አሻራ
ሕዝብ
ጥሬ ቡና ነው ለዐሴር ዘር፣ ለንጉሡ የተዘራ።
አያ
ምስኪን ቡና ኅዳር ሆነ ከፋ ተወልዶ
በእረኛው
ካልዲ ክፋት ከምድሩ ተሰዶ
በታላቋ
ጥንታዊት አክሱም ሆነ በዛሬዋ ኃያል አሜሪካ
ከኦቶማን
ቱርክ፣ ከሞሮኮ ደርቡሽ፣ ወይ የኛዋ አፍሪካ
ቡንቹም፣
ኮፊ፣ ካፌ፣ ካፈ ቡና ይባል ቡን
ይወክላል
ሕዝብን በእሳት የሚቆላውን
ብረት
ምጣድ ላይ ተንጋሎ የሚንጨረጨረውን።
ሥርዓቱ
ጋዋም ሆነ ቡና፣ ቡናካላ ቁጢም ሆነ አሻራ
ሕዝብ
ጥሬ ቡና ነው ለዐሴር ዘር፣ ለንጉሡ የተዘራ።
እንደ
ቡና አፊዋ፣ ቡና የምትቆላው፣ አፍላታም የምትጠጣው
ይኼ
ሥርዓት የሚሉት የዛር ውላጅ፣ በሷ ያደረው ቃፊር አወሊያው።
ሕዝብ
ነው የቡናው ፍሬ፣
ከብረት
ምጣዱ የተጣደ
ኋላውን
ሳያውቅ ለነፉቅራ፣
ለነዲራ እጅ ነስቶ የሰገደ።
ሥርዓቱ
ጋዋም ሆነ ቡና፣ ቡናካላ ቁጢም ሆነ አሻራ
ሕዝብ
ጥሬ ቡና ነው ለዐሴር ዘር፣ ለንጉሡ የተዘራ።
ይኼ
ደሞ ዓማጺ ነኝ ባይ ዘነጐላ፣
የማያረው
ጥሬ ቢቆላ፣ ቢቆላ፣
ቢልለት
እሱም መልሶ ሕዝቡን የሚቆላ
ከንቱ
የሚዳክር ላያመልጥ ከመቁያው ብረት ዘንግ
ከአስከባሪው
ባለ ጠብ-መንጃው ርጉም ባለ ቤልጅግ።
ሥርዓቱ
ጋዋም ሆነ ቡና፣ ቡናካላ ቁጢም ሆነ አሻራ
ሕዝብ
ጥሬ ቡና ነው ለዐሴር ዘር፣ ለንጉሡ የተዘራ።
ብረት
ምጣዱ ቢለያይ መቆያው በስመ አገር
ከፋርስ
እስከ ኩባ፣ ከሃይቲ እስከ ቀጠር
በትምህርት
በወግ የሚሉት ዘነዘና ሙቀጫ ተወቅጦ
እስኪልም
ተሰልቅጦ
በጀበና
በቡሽ የሚሉት ሕግ ታምቆ ተውጦ
ተንተክትኮ፣
ተንተክትኮ ላይቀርለት ህልፈት።
ሥርዓቱ
ጋዋም ሆነ ቡና፣ ቡናካላ ቁጢም ሆነ አሻራ
ሕዝብ
ጥሬ ቡና ነው ለዐሴር ዘር፣ ለንጉሡ የተዘራ።
በረከቦትና
ማቶት የባሕልና ሃይማኖት ተቋማት
ወዲህ
ደሞ አነስተኛ ሌማት፣ የቡና ገጸ-በረከት
ይኼ
ጊርጊራው ዕጣኑ ፕሬስ ተ’ባይ ከንቱ ሁከት
ሕዝቡ
ሲሆን ዱቄት፣ የነጋሢያኑ ፍጹም ስኬት
አቦል፣
ቶና ወይ ሲና፣ በረካ የሥርዓት ውጤት
ለቡና
ፍሬው አንዳች ላይፈይድለት
ላይቀርለት
መሆኑ በረከት፣ አጉል ጩኸት።
ሥርዓቱ
ጋዋም ሆነ ቡና፣ ቡናካላ ቁጢም ሆነ አሻራ
ሕዝብ
ጥሬ ቡና ነው ለዐሴር ዘር፣ ለንጉሡ የተዘራ።
ስኒ
በሚሉት አሰላለፍ መደብ፣ ከጀበናው ተቀድቶ
መቅረቡ
አይቀርም ያ ቡና ለንጉሡ ተፈልቶ
ቀሪው
ትዝታ ነው እንዲያው እንቶ ፈንቶ
ታሪክ
ተብሎ የሚነገር እንጉልፋቶ።
ሥርዓቱ
ጋዋም ሆነ ቡና፣ ቡናካላ ቁጢም ሆነ አሻራ
ሕዝብ
ጥሬ ቡና ነው ለዐሴር ዘር፣ ለንጉሡ የተዘራ።