Friday, March 1, 2019

ወርሐ ግንቦት


ወርሐ ግንቦት
ግንቦት ፩
·         ፲፱፻፳፰ ዓ/ም - የኢጣልያ ንጉሥ ቪክቶርዮ ኢማኑኤል ሣልሣዊ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ እና ግዛት በኢጣልያ አስተዳደር ሥር የሚያደርግ አዋጅ አስንገረው፣ ይሄንኑ አዋጅ ለዓለም መንግሥታት እንዲሰራጭ አዘዙ። የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትነት ማዕርግ ከዚህ ዕለት ጀምሮ የእሳቸውና የወራሾቻቸው እንደሆነ፣ የኢትዮጵያም ሕዝብ እና ግዛት በእንደራሴ እንደሚታደደር በዚሁ አዋጅ ይፋ ተደርገ።
·         ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - የኢጣልያ ንጉሥ ቪክቶርዮ ኢማኑኤል ሣልሣዊ፣ ከዙፋናቸው ወርደው ዘውዱ ወደንጉሥ ዳግማዊ ኡምቤርቶ ተዛወረ።
·         ፲፱፻፷፫ ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስ ስርዓተ ሲመት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናውኗል።
·         ፲፱፻፺፫ ዓ/ም - በጋና ርዕሰ ከተማ አክራ የእግር ኳስ ሜዳ በሚካሄድ ጨዋታ ላይ ተመልካች ሕዝብ በዳኛው ውሳኔ ባለመስማማቱ የተነሳውን ረብሻ ለማብረድ፣ ፖሊሶች የተኮሱት የጢስ ቦምብ ሕዝቡን የባሰውን ሲያተራምሰው በተከሰተው ትርምስና የሰው ግፊያ ፻፳፱ ሰዎች ተቸፍልቀው ህይወታቸውን አጡ።
·         ፲፰፻፵፬ ዓ/ም - ራስ መኮንን ከ ልዕልት ተናኘወርቅ ሣህለ ሥላሴ እና ከደጃዝማች ወልደሚካኤል ወልደ መለኮት ጎላ ወረዳ ደረፎ ማርያም በሚባል ሥፍራ ተወለዱ።
ግንቦት ፪
·         ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - ለሃያ ሰባት ዓመታት በእሥራት የቆዩት ኔልሰን ማንዴላ ለአገራቸው ደቡብ አፍሪቃ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚደንት በመሆን ቃለ-መሐላቸውን ፈጸሙ።
ግንቦት ፫
·         ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ “የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጣልቃ ገቦች በአገሪቱ ጉዳይ ውስጥ እየገቡ አስቸግረዋል በሚል መነሻ የፈረንሳይን፤ አሜሪካን፤ ግብጽን፤ የሶቪዬት ሕብረትን፤ የብሪታኒያን እና የዩጎዝላቪያን የልዑካን አለቆች ሰብስበው አነጋገሩ። በማግሥቱ ይፋ የተደረገው ጽሑፋዊ ቃለ-ጉባኤ አምባሳደሮቹ የተጠሩት “የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ጉዳዮች ላይ የባዕዳንን ጣልቃ ገብነት በብርቱ እንደሚቃወም እና በኢትዮጵያ ግዛትና ሉዐላዊነት ላይ የሚሰነዘሩትን ማናቸውንም እርምጃዎች ለመከላከል ቆራጥ መሆኑን እንዲገነዘቡ ነው።” ይላል።
·         ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከግብጽ ፕሬዚደንት ሳዳት ጋር ለውይይት ወደካይሮ ሲጓዙ፣ እግረ መንገዳቸውን ካርቱም ላይ አርፈው ከፕሬዚደንት ኒሜሪ ጋር ተለወያዩ።
ግንቦት ፬
·         ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የዮርዳኖስ ንጉሥ ሁሴን ለአራት ቀን ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።
ግንቦት ፭
·         ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - በቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ (የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) ተማሪዎች አድማ መቱ።
·         ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - ልዑል መኮንን ኃይለ ሥላሴ መስፍነ ሐረር በናዝሬት መንገድ ሞጆ አካባቢ ላይ በመኪና አደጋ በሞት ተለዩ።
ግንቦት ፮
*********
ግንቦት ፯
*********
ግንቦት ፰
·         ፲፱፻፰፩ ዓ/ም - በኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማርያም ላይ የመፈንቀለ መንግሥት ሙከራ ተደረገ።
·         ፲፱፻፴ ዓ/ም - ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ምሑር፤ አስተማሪ፤ ደራሲ እና የቅዱስ ያሬድ የሙዚቃ ትምሕርት ቤት መሥራች ዶክቶር አሸናፊ ከበደ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ተወለዱ።
·         ፲፰፻፷ ዓ/ም - የዓፄ ቴዎድሮስ ሚስት እና የልዑል ዓለማየሁ እናት፤ እቴጌ ጥሩነሽ በዚህ ዕለት አረፉ።
·         ፲፱፻፺ ዓ/ም - ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ምሑር፤ አስተማሪ፤ ደራሲ እና የቅዱስ ያሬድ የሙዚቃ ትምሕርት ቤት መሥራች ዶክቶር አሸናፊ ከበደ በዛሬው ዕለት በተወለዱ በስልሳ ዓመታቸው አረፉ።
ግንቦት ፱
·         ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የአዲስ አበባው ጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት የተመሠረተበትን ፳፭ኛ ዓመት በዓል ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በተገኙበት አከበረ።
ግንቦት ፲
*********
ግንቦት ፲፩
·         ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የኤርትራ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያጸደቀውን ሕገ-መንግሥቱን በመለወጥ አገሪቱን ከ’ኤርትራ መንግሥት’ ወደ ‘የ ኤርትራ አስተዳደር’ በመለወጥ ወደፊት ሙሉ የኢትዮጵያ አካል ለማድረግ የሚስችላትን ውሳኔ አጸደቀ።
ግንቦት ፲፪
·         ፲፬፻፹፮ ዓ/ም - ዓፄ እስክንድር በነገሡ በ፲፮ ዓመታቸው አረፉና በደብረ ወርቅ ተቀበሩ። ሥልጣነ መንግሥታቸውም ወደ ፯ ዓመቱ ልጃቸው ዓምደ ጽዮን ሣልሳዊ ተዘዋወረ። ሆኖም ዓምደ ጽዮን በነገሡ በ፯ ወራቸው ድንገት ስለሞቱ አልጋው ወደ አባታቸው ወንድም አጼ ናዖድ ተላልፏል።
·         ፲፯፻፲፫ ዓ/ም - አፄ ዳዊት ሣልሳዊ በዚህ ዕለት አረፉ።
ግንቦት ፲፫
·         ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - የየካቲት ፲፪ ቀን አዲስ አበባ ላይ ግራዚያኒ ላይ የተወረወረውን ቦምብ ምክንያት በማድረግ ፋሺስቶች ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገብተው ፫፻፳ መነኮሳትን በግፍ ጨፈጨፉ፤ ገዳሙንም አቃጠሉ።
·         ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የአሩሲ ጠቅላይ ግዛት (አሁን አርሲ) እንደራሴ ሆነው የተሾሙትን አቶ ተስፋ ቡሸን የጠቅላይ ግዛቱ ሕዝብ አባሮ አስወጣቸው።
·         ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - የኢሕዲሪ (የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ) ፕሬዚዳንትና የኢሠፓ (የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ) ዋና ጸሐፊ የነበሩት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አገር ጥለው በመኮብለል ዚምባብዌ ገቡ።
·         ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም በዚህ ዕለት አዲስ አበባ ተወለዱ።
ግንቦት ፲፬
*********
ግንቦት ፲፭
*********
ግንቦት ፲፮
·         ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ ራሷን የቻለች ሉዐላዊ አገር ሆነች።
ግንቦት ፲፯
·         የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት የተመሠረተበትን ዕለት በማስታወስ ይህ ዕለት በመላው የአፍሪቃ አኅጉር “የአፍሪቃ ቀን” ተብሎ ይከበራል።
·         ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - የ፴፪ ነጻ የአፍሪቃ አገራት መሪዎች አዲስ አበባ ላይ ተሰብስበው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትን መሠረቱ።
·         ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - በአዲስ አበባ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ፤ በከተማው አውቶብሶች እና ንብረት ላይ ጉዳት አደረሱ። በዚህም ምክንያት አሥር ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤቶች ተዘጉ።
ግንቦት ፲፰
·         ፲፯፻፲፫ ዓ/ም - ከወህኒ በወረዱ በሁለተኛው ቀን የአፄ አድያም ሰገድ ኢያሱ ልጅ አፄ በካፋ ጎንደር ላይ በጳጳሱ አባ ክርስቶዶሉ እና እጨጌ ተክለ ሃይማኖት ተቀብተው ነገሡ።
·         ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የሶቪዬት ሕብረት የኢንዱስትሪ እና የቴክኒክ ምርቶች አውደ ርዕይ አዲስ አበባ ላይ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመርቆ ተከፈተ።
·         ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት አሥረኛው የመሪዎች ስብሰባ አዲስ አበባ ተከፈተ።
ግንቦት ፲፱
·         ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኤርትራ ነጻ አውጪ ግንባር አባላት ጊንዳ ውስጥ በሉተራን ሚሲዮን ሆስፒታል ውስጥ የሚሠራ ዶክቶርን የመጥለፍ ሙከራ ሲያደርጉ አንዲት አስታማሚ (ነርስ) ተገደለች።
·         ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የቴሌኮሙኒኬሽን ሠራተኞች በአድማ ሥራቸውን አቆሙ።
ግንቦት ፳
·         ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው መኮንን መንግሥት የሚኒስትሮችን ለውጥ ይፋ አደረገ። ከነዚህም አንዱ የአገር ግዛት ሚኒስትር የነበሩትን ደጃዝማች ዘውዴ ገብረ ሥላሴን ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መዛወር ያካትታል።
·         ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - ኢሕአዴግ በዘመቻ ወጋገን አዲስ አበባን ተቆጣጠረ። አቶ መለስ ዜናዊ የሽግግሩ መንግሥት ፕሬዚዳንት ሆኑ።
ግንቦት ፳፩
·         ፲፰፻፸ ዓ/ም አፄ ዮሐንስ እና የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ በተገኙበት በወሎው ቦሩ ሜዳ ላይ የተካሄደው የሃይማኖት ክርክር እልባት አገኘ፡፡
ግንቦት ፳፪
·         ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመጽ ቆስቋሽነት የተሠየመው የሙስና እና የሥልጣን በደል መርማሪ ሸንጎ ሥራውን የሚመራበት ሕግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ።
ግንቦት ፳፫
·         ፲፱፻፯ ዓ/ም - ልጅ ኢያሱ አባታቸውን ራስ ሚካኤልን ደሴ ላይ ንጉሠ ወሎ ወ ትግሬ ብለው አነገሧቸው።
ግንቦት ፳፬
·         ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በ፳ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በትልቅነቱ በኢትዮጵያ ታሪክ አቻ የሌለው በ”ሪክተር” ሚዛን ስድስት ነጥብ ሰባት ያስመዘገበ የመሬት እንቅጥቅጥ ተከስቶ የማጀቴን ከተማ ሲደመስስ፣ በጎረቤቷ ካራቆሬ ደግሞ ከመቶ እጅ አርባ አምሥቱ መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። ከካራቆሬ በስተሰሜን የሚያልፈው ዋናው የአዲስ አበባ፦ አስመራ መንገድ እና ድልድዮችም እንቅጥቅጡ ባስከተለው የድንጋይ ናዳ ወደ አሥራ ሰባት ኪሎ ሜትር ርዝመት ላይ አደጋ ደረሰ
ግንቦት ፳፭
·         ፲፯፻፹፰ ዓ/ም - አመድ ከሰማይ ዘነበ።
·         ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የመጀመሪያዎቹን አራት ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት (አቡነ አብርሓም - የጎንደር እና የጎጃም፤ አቡነ ይስሐቅ - የትግሬ እና የስሜን፤ አቡነ ጴጥሮስ የወሎ እና የላስታ፤ አቡነ ሚካኤል - የኢሉባቡር እና የምዕራብ ኢትዮጵያ) ከግብጻዊው ሊቀ ጳጳሳት (አቡነ ቄርሎስ)ጋር ካይሮ ላይ ተቀብተው ተሾሙ።
ግንቦት ፳፮
·         ፲፯፻፷፭ ዓ/ም - የዓፄ በካፋ ሚስት የነበሩት እቴጌ ምንትዋብ በዚህ ዕለት አርፈው በቁስቋም ደብረ ጸሐይ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ።
ግንቦት ፳፯
·         ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በመከላከያ ሚኒስትር ጄኔራል ሊዩቢቺክ የሚመራ የዩጎዝላቪያ ወታደራዊ ቡድን ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ጋር አዲስ አበባ ላይ ያካሄደውን የአራት ቀን ውይይት ጀመረ።
ግንቦት ፳፰
·         ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - በአዲስ አበባ ከተማ በቆሎ ሰፈር አካባቢ የሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ በተነሣ ፍንዳታ በርካታ ሕይወት አለፈ፤ ብዙ ቤቶችና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።
ግንቦት ፳፱
*********
ግንቦት ፴
·         ፲፱፻፴፫ ዓ/ም - አዲስ ዘመን በሚለው መጠሪያ የሚታወቀው ብሔራዊ ጋዜጣ በይፋ ሥራ ጀመረ። የጋዜጣው ሥያሜ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከጠላት ወረራ በኋላ ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ/ም በድል አድራጊነት ሲገቡ «ይህ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የአዲስ ዘመን መጀመሪያ ነው» ማለታቸውን መሠረት ያደርጋል።
·         ፭፻፴ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዓፄ ካሌብ አረፉ።