Monday, January 9, 2017

Criminology 101




ሥነ ወንጀል ዋን ኦ ዋን (Criminology 101)

ፉሊሶች ትናንት ማታ ልክ ጭፈራ ቤቱን ወረሩት። እኔ ሽንት ቤት ነበርኩ። እኔ ጋ የመጣው ፉሊስ ኪሴን ሲፈትሽ በስስ ፌስታል የተጠቀለለችዋን ካያ አገኘብኝ።

“በጭራሽ የኔ ጥፋት አይደለም፣ ምንም ማድረግ አልችልም?” አልኩት። “ይኸው ቅድም ጀምሮ ሽንት ቤቱ ውስጥ ልከተው እየሞከርኩ ነው። ግን እንዴት አባቱ እንደሆነ አላውቅም ይገባና ልክ ልሄድ ስል መልሶ ኪሴ ውስጥ ይመጣል። ምን ዓይነት ድግምት እንዳደረጉብኝ አላውቅም።”

“ምን እኔን ጅል ማድረግህ ነው። ለእንደዚህ ዓይነት ቀልድ ያንተ ቢጤውን ፋራ ፈልግ!” ብሎ ሸቤ ሊወስደኝ ቀጥል በሚል ዓይነት ጎሸም አድርጎ ወደፊት መንገዱን አሳየኝ።

የሞት ሞቴን “ማርያምን! ካላመንክ እዚችው ላሳይህ እችላለሁ!”

በኩራት ፈገግ ብሎ እንደ መጠራጠር እያለ ፌስታሌን ሰጠኝና “እስኪ እንየው! ኪስህ ውስጥ ባላገኘው ግን ወዮልህ!”

“አረ ግድ የለም” አልኩ እና ሽንት ቤት ውስጥ ከትቼ ውሃውን ለቀቅኩበት። እሱም ትግስት ባጣ መቁነጥነጥ “እሺ የኔ ባለ ድግምት! በል አሁን ኪስህን አሳየኝ!”

“ለምንድነው የማሳይህ?” ብዬ ፍጥጥ።
“ሐሺሹ!”
እኔም መልሼ “የምን ሐሺሽ?”

A policeman searched me in a Nightclub toilet last night and found a small bag of class A drugs.

“It’s not my fault,” I said, “Every time I try flushing them down the toilet they magically appear back in my pocket again.”

I said, “I’ll prove it to you if you want me to!”

“Go on then.” He smiled, handing me the bag.

“After flushing them, he looked at me and said, “Well, show me your pocket then.”

“What for?!” I asked.

He said, “The drugs.”

I said, “What drugs?”

Friday, January 6, 2017

አትማር ልጄ !



አትማር ልጄ !

ወገን ዘመድ ባይኖር ሀብት ባይኖረኝ ከእጄ
ያንተ መማር ላገር ለዘመዱ ለሁሉ ካልበጄ
ያንተ አስኳላ የሰው ልጅ ከፈጀ
የተከልከው ዕፅ ሳይበቅል ካረጀ

መማርህ ላንተም ለኛ ካልበጄ
ለምን ትማራለህ፣ አትማር ልጄ

ሌቱም ሰላም ነው ፀጥታ የሰፈነበት
ሠርቶ የደከመ አርፎ የሚተኛበት
ዱር አራዊት ግን ግዳይ የሚወጣበት
ከዋክብቱም ሰማይን የሚኩሉበት


እና ያንተ መማር ካረገህ የቀን አውሬ
ድንጋይ ከጣልክብን እንደ እብድ ገመሬ
ዘር ከልጓም ይስባል ሲባል ካልገባህ
የባዕድ ጅኒ ከሰፈረብህ ከጫንቃህ

መማርህ ላንተም ለኛ ካልበጄ
ለምን ትማራለህ፣ አትማር ልጄ

የራስህን ቀዬ የራስህን ታዛ ካልጠቀምክ
ያባትህ ሞፈር እርፍና ቀንበር ካስጠላክ
ከኤረር ማዶ ከሰማይም በላይ ከራማ ከላይኛው ጠፈር
ከባሕር ጥልቀቱ ከምድር ጓዳ ስምጥ ብትመረምር
ዕውቀት ላይኖረው መጨረሻ
ለጉዞህም ወደብ መድረሻ


ላትደርስ ከሆነ የጀመርከው ከወዲያኛው ጥግ
ልትቆነጽል ከሆነ ጥበብን በትንሹ ልትለግግ
የዕውቅተ ፍኖት ያ የሚታይ ከወዲያ
መንገዱ ሰፊ ነው ወለል ያለ ጥርጊያ
በማወቅ ውስጥ ስላለ እያወቁ ማለቅ
ተው ልጄ በልክህ እንደ ራስህ ዕወቅ
መጥነህ ደቁስ መጥነህ አድቅቅ

መማርህ ላንተም ለኛ ካልበጄ
ለምን ትማራለህ፣ አትማር ልጄ

እንዳታሳጣኝ እኔን ጧሪና ቀባሪ
አታዛንቀው ባክህ አላፊን ከኗሪ
ማወቁን ዕወቅ ግን በራስህ ልክ ዕወቅ
የሰው ስታንቧችር የራስህን እንዳትነጠቅ

ላጫውትህ ጨዋታ እንደ ልጅነትህ
የዘርህን ትተህ ደሞ እንዳያንዘረዝርህ
እምዬ ቅሌት ያብሽ ገለባ
ሜዳ ነው ብዬ ገደል ልገባ
እንዳይሆን ነገርህ ልጄ ለራስህ ዕወቅ
አርቀህ ተመልከት ረዥም እንድትዘልቅ

መማርህ ላንተም ለኛ ካልበጄ
ለምን ትማራለህ፣ አትማር ልጄ

ሕፃን እንኳ ባቅሙ እንዲያውቅ እናቱን በጠረኗ
ለአገርም መሆን ይበቃታል አገር መሆኗ
ካልቆምክላት በሸንጎ፣ ባውድ ባደባባይ
ካልሞገትክላት ለሷ በሊቃውንቱ ጉባይ

ስኰናህን ካለመንከው ይቅርብህ መንገዱን አትጀምረው
የሰው ልጅ ዕድሜ እንጂ ዕውቀት መጨረሻ የለው
ዐውቃለሁ ማለት ግብዝነት ነው ባትውቅ ነው የሚሻለው

ዓይንህን ጥለህ በሰው ዓይን ከምታይ
ጎጆህን ጠልተህ ከምትባል ዘበናይ
ዋና ሳታውቅ ከምትገባ ከቀላይ
በሰው አሮፒላ ከምትበር በሰማይ
አደራ ልጄ፣ ራስህን ስታውቅ  
ሌላ ምንም እንዳታውቅ

በቅጡ ሳታውቅ የኛን ትንሹ ሐይቅ
ባሕር ላይ ብትራቀቅ
ማናችንም ላንባጅ
ታንገላታናለህ እንጅ
ታንኳህ ቀዳዳ አለው ብዙም አይዘልቅ
አንተም ከንቱ አትልፋ እኛም አንሳቀቅ
ዕውቀት ቀሊል መስሎህ የጀመርከው ጉዞ
ይቀንጨር ግድየለም ዐጽጾ ይቅር ታርዞ

መማርህ ላንተም ለኛ ካልበጄ
ለምን ትማራለህ፣ አትማር ልጄ

በዕለት መድሃኒዓለም የታህሳሱ፣ በ2009 አዲስ አበባ፣ ዶን ብሩኖ

Wednesday, January 4, 2017

One joke of Mugabe quotes in Facebook; translated into Amharic



አዙሪት
አለቃዋ ጸሐፊውን ከቢሮው ጠራትና
“ለአንድ ሳምንት ከከተማ ወጣ እንላለን፣ ስለዚህ ተዘጋጂ።”
ጸሐፊም በታዘዘችው መሠረት ውስጧ ፍንድቅድቅ እየለ ድምጽዋን እንዳያሳብቅ በመጠንቀቅ ወዲያው ወደ ባልትቤቷ ደወለችና
“ፍቅሬ፣ ነገ የፊልድ ሥራ ታዝዤ ከአለቆቼ ጋር ወደ ክፍለ ሃገር ለአንድ ሳምንት መሄዴ ነው። ስለዚህ ልጆቹን አንተ ስለምትይዝ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርግ”
ባልየውም ልቡ በደስታ ጮቤ እየረገጠ ወደ ውሽሚቱ ደወለ።
“ሚስቴ ለአንድ ሳምንት ክፍለ ሃገር ትሄዳለች፣ እና ሳምንቱን አብረን ብናሳልፍ ምን ይመስልሻል?”
ውሽሚት በግሏ እየተከፈላት ለምታስጠነው ተማሪ ትደውልና፦
“ከነገ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በጣም አስቸኳይ የግል ሥራ አለብኝ። ስለዚህ እኔ ጋ ለመማር መምጣት የለብህም።”
ተማሪው ልጅም ወደ አያቱ ይደውልና፦
“አያቴ፣ የግል አስጠኚዬ ስለማይመቻት ለአንድ ሳምንት የትምህርት ጥናት የለኝም። ስለዚህ ሳምንቱን ከናንተ ጋር ብሆን ምን ይመስልሃል?”
አያትየው ወደ ጸሐፊው ደወለና፦
“ይቅርታ ከከተማ መውጣት የምንችል አይመስለኝም። እኔ እና የልጅ ልጄ አብረን ሳምንቱን ማሳለፍ አለብን።”
ጸሐፊዋ ወደ ባሏ መልሳ ትደውልና
“አለቆቼ አንዳንድ ችግሮች አጋጥሟቸው የጉዞ ፕሮግራሙን ሰርዘውታል።”
ባል ወዲያው ለውሽማው መልሶ ይደውልና
“ሳምንቱን ባክሽ አብረን መሆን አንችልም። ሚስቴ ጉዞ ፕሮግራሟን ሰርዛዋለች”
ውሽሚት ለተማሪው ልጅ መልሳ ትደውልና
“በዚህ ሳምንት እንደ ተለመደው ትምህርት ይኖረናል። መምጣት ትችላለህ!”
ተማሪው ልጅም ወደ አያቱ ይደውልና፦
“አያቴ! ሳምንቱን ይቅርታ አብረን ማሳለፍ አንችልም። አስተማሪዬ ስልክ ደውላልኝ እሷ ጋር ለመማር መሄድ እንዳለብኝ ነግራኛለች”
አያትየው ወደ ጸሐፊው አሁንም ይደውልና፦
“ይቅርታ መልሼ ደውልኩ! አሁንም ሐሳብ ልቀይር ነው። የልጅ ልጄ ትምህርት አለበት። ስለዚህ አይመጣም፣ እና እንደ ተባባልነው ጉዟችንን መሄድ እንችላለን።”  
ይኼን አዙሪት ማን ሊያስቆመው ይችላል?

ከ FaceBook ገጽ ከሙጋቤ ቀልዶች የተተረጐመ ታሳስ 26፥ 2017 ዶን ቡሩኖ

Boss says to his secretary, “We are
traveling abroad for the week, so make arrangements.”
The secretary makes a call to her
husband, “My boss and I will be
traveling abroad for the week, so look after kids.” The husband makes call to secret lover, “My wife is going abroad for the week, so let’s spend the week together.” The secret lover makes a call to a little boy whom she is giving private lessons, “I’m going to be busy throughout the week, so you need not come for classes.” The little boy makes call to his grandfather, “Grandpa, I don’t have classes for the week, because my teacher is going to be busy. Let’s spend the week together.” The
grandpa makes a call to his secretary, “I’m afraid we won’t be traveling again. My grandson and I are going to spend the week together.” The secretary makes a call to her husband, “My boss has some personal matters to attend
to, so our trip is cancelled.” The
husband makes a call to secret lover, “We cannot spend the week together, my wife has cancelled her trip.” The secret lover makes a call to little boy, “We will still have classes as usual this week.” The little boy makes a call to his
grandfather, “Grandpa! I’m sorry we won’t be able to spend the week together. My teacher called and said that I have to attend classes.” The grandpa makes a call to his secretary, “Change of plans! My grandson is no more coming. So we are still traveling this week. Make arrangements.” Can someone pliz tell me who is controlling this chain?