ዝግጅት በብሩክ በየነ ከኢትዮስታር አካዳሚ
0-1 ወር:
ጤናማ ለውጦች፡-
ፈጣን ክብደት መጨመር
ድንገቴ የሰውነት እንቅስቃሴ/ መወራጨት
ለረጅም ጊዜ መተኛት እና ምግብ ሲፈልግ መነሣት
መረዳቱን በማረጋገጥ የሚሰጥ ጠንከር ያለ ምላሽ።
የሚፈልገውን ለማግኘት ማልቀስ።
የሕክምና ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ለውጦች፦
አጥጋቢ ያልሆነ አመጋገብ ሁኔታ ወይም አርኪ ያልሆነ የክብደት ሁኔታ
ምላሽ አለመስጠት ወይም ዓይንን ማሸሽ
ከፍተኛ ትኩሳት (ከ38° ሴንቲግሬድ ወይም 100.4° ፋራናይት በላይ)
የመተንፈስ ችግር ወይም የማያቋርጥ ሳል
ጤናማ ያልሆነ የሰውነት እንቅስቃሴ ወይም ከመጠን በላይ መልፈስፈስ
1-3 ወራት፦
ጤናማ ለውጦች፡-
ፈገግታ እና ማልቀስ
የጭንቅላት እንቅስቃሴን የመቆጣጠር ችሎታ መጨመር
የበለጠ ንቁ መሆን እና ተግባቢነት
የተሻለ የጊዜ ቅጡ የታወቀ አስተኛኘት
ነገሮችን በዓይን እየተከታተሉ ማየት
የሕክምና ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ለውጦች፦
አጥጋቢ ያልሆነ ክብደት ወይም የአመጋገብ ችግር
ተግባቢነት ስሜት አለማሳየት ወይም ምላሽ አለመስጠት
የማያቋርጥ ትውከት ወይም ተቅማጥ
ያልተለመዱ ሽፍታዎች ወይም የቆዳ ለውጦች
የሚጠበቁ ዕድገትን የሚያሳዩ ለውጦች አለመታየት
3-6 ወራት
ጤናማ ለውጦች፡-
መገላበጥ
በድጋፍ መቀመጥ መቻል
መንተባተብ እና ተጨማሪ ድምፆችን ማሰማት
የሰው መልክ መለየት
የእጅና የዓይን ጥምረት መጎልበት
የሕክምና ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ለውጦች፦
ድንገተኛ የክብደት መጨመር ወይም መቀነስ
መንተባተብ ወይም ድምፅ ማሳማት ሁኔታ አለመኖር ወይም መዘግየት
የማያቋርጥ ትኩሳት ወይም ማናቸውም የበሽታ ምልክቶች
የመተንፈስ ወይም የመተንፈስ ችግር
በቀላሉ ቁጡ መሆን ወይም ያለማቋረጥ ማልቀስ
6-9 ወራት
ጤናማ ለውጦች፡-
መዳህ ወይም ለመዳህ መሞከር
ለመቆም መታተር/ መሞከር
ነገሮችን አፍ ውስጥ ማስገባትና መነካካት
ስሙ መጠራቱን ማወቁን ማረጋገጥ (ስሙን ለይቶ ማወቅ)
ከወተት ውጭ የላሙ ቀላል ምግቦችን መመገብ መጀመር
የሕክምና ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ለውጦች፦
ተፈላጊ የዕድገት ደረጃዎች ላይ አለመድረስ
ድንገት ክብደት መቀነስ ወይም ደካማ የምግብ ፍላጎት መኖር
የማያቋርጥ ከፍተኛ ትኩሳት ወይም የኢንፌክሽን ምልክቶች
ለመዋጥ መቸገር
በዙሪያው ላሉ ነገሮች ደንታ ቢስ መሆን ወይም ምላሽ ሰጪነቱ መቀነስ
9-12 ወራት
ጤናማ ለውጦች
ተደግፎ ወዲህ ወዲያ ማለት ወይም መራመድ
ዕቃዎችን ማመላከት እና ጠቁሞ ማሳየት
እንደ "ማማ" ወይም "ዳዳ" ያሉ ቀላል ቃላትን መናገር
ይበልጥ ራስን የመቻል ሁኔታ ማሳየት እና የማወቅ ጉጉት መጨመር
የሚታኘኩ ምግቦች መብላት
የሕክምና ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ለውጦች፦
በፊት ማድረግ ይችላቸው የነበሩ ነገሮችን ማድረግ አለመቻል
ከመጠን በላይ ቁጡ መሆን ወይም ረዘም ላለ ጊዜ ማልቀስ
ክብደት አለመጨመር ወይም ጉልህ የሆነ የክብደት መቀነስ
የመተንፈስ ችግር ወይም የማያቋርጥ ሳል
ማንኛቸውም ከላይ የተዘረዘሩት የዕድገት ምልክቶች መዘግየት ወይም ሌሎች አሳሳቢ ምልክቶች
ያስታውሱ፤ እያንዳንዱ ሕፃን የሚያድገው በራሱ መንገድ ነው፣ አንዱ ሊፈጥን ሌላው ደግሞ ሊዘገይ ይችላል። ስለ ልጅዎ ጤና ወይም ዕድገት የሚያሳስብዎት ነገር ወይም ሁኔታ ካለ፣ ትክክለኛውን ምርመራ ለማድረግና አስተማማኝ የሆነ ምላሽ ለማግኘት የጤና ባለሙያ ማነጋገር ይኖርብዎታል።
No comments:
Post a Comment