Thursday, February 28, 2019

ወርሐ የካቲት


የካቲት ፩
  • ፫፻፹፮ዓ/ም - በክርስትና ሃይማኖት የተከሰቱትን ተቃራኒ ትምህርቶች በጉባኤ ለመወሰን የቁስጥንጥንያው ንጉሥ ቀዳማዊ ቴዎዶስዮስ ባስተላለፈው ጥሪ መሠርተ ፩፻፶ ሊቃውንት፣ ኤጲስ ቆጶሳት በቁስጥንጥንያ ጉባኤ ተሳትፈው መቅዶንዮስን፤ አፖሊናሪዮስን እና ሌሎችን መናፍቃንን አወገዙ።

የካቲት ፪

የካቲት ፫
  • ፲፯፻፰ዓ/ም - በእስራት ላይ የነበሩት የ ፳፩ ዓመቱ ጎልማሳና የንጉሥ ኢያሱ አድያም ሰገድ ልጅ ዳግማዊ ዓፄ ዳዊት እንደነገሡ አዋጅ ተነገረ።
  • ፲፰፻፵፯ዓ/ም - ደጃዝማች ካሳ (ዓፄ ቴዎድሮስ)ና ደጃዝማች ውቤ ቧሂት ላይ ድንኳን ተክለው ተገናኙ። ደጃዝማች ካሳም የእንግሊዙን ሊቀ መኳስ ዮሐንስን (John Bell)በመንጥር አይተህ ንገረኝ አሉት። የሸማ ድንኳን ባየ ጊዜ ነገራቸው። ደጃዝማች ካሳም «አያሳድረኝ አላሳድረውም» ብለው ተናገሩ። ያንጊዜውንም ተነሣ አሉ። ባሰለፉትም ጊዜ እንዴህ ብለው በፍከራ ትንቢት ተናገሩ። «እንኳን ይህን ቁርጥማታም ወሎን፣ መትቼ የሻዋውን ንጉሥ እይዘዋለሁ። ስሜን ስሜን እንግርሀለሁ ያልሁህ ወታደር ስሜም ቴዎድሮስ ነው» አሉ። አስቀድሞ ገና በንጉሥ አምላክ በል። ስሜን ስሜን እነግርሀለሁ ብለው ነበርና። ያንጊዜውን እንዴህ አሉ። «ወታደር አይዞህ አትፍራ። የውቤ ነፍጥ የውቤ ነፍጥ ቢልህ የተለጎመው ጨርቅና ባሩድ ነው። አይነካህም» አሉት። እኔ የክርስቶስ በርያ ሁሉንም አሳይሀለሁ ወታደር ባሉ ጊዜ ሰልፍ ገጠመ። ደጃች ውቤም ተያዙ።

የካቲት ፬
የካቲት ፭
የካቲት ፮
  • ፲፭፻፶፭ዓ/ም - የ ፲፪ ዓመቱ ልጅ ማር (ጌታ) ሠርፀ ድንግል፣ አባታቸው አጼ ሚናስ ሲሞቱ በስመ መንግሥት መለክ ሰገድ ተብለው ነገሡ። አጼ ሠርፀ ድንግል የመንግሥት ሥራቸውን የሚሠሩት በእናታቸው በእቴጌ አድማስ ሰገድ ሥሉስ ኃይላ አማካይነት ነበር።
  • ፲፭፻፶፭ዓ/ም ኢትዮጵያን ከአራት ዓመታት በንጉሥነት የመሯት አፄ ሚናስ (ስመ መንግሥት፣ ቀዳማዊ አድማስ ሰገድ) በዕለተ እሑድ አረፉ፡፡ አጼ ሚናስ የአጼ ገላውዴዎስ ወንድምና የአጼ ልብነ ድንግል ልጅ ነበሩ።
  • ፲፱፻፶፫ዓ/ም የቀድሞዋ ኮንጎ ሊዮፖልድቪል (የአሁኗ የኮንጎ ሪፑብሊክ) የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ፓትሪስ ሉሙምባ መገደላቸው ይፋ ተደረገ።
የካቲት ፯
የካቲት ፰
የካቲት ፱
የካቲት ፲

የካቲት ፲፩

የካቲት ፲፪
  • ፲፱፻፳፱ዓ/ም - ለኢጣሊያ ንጉሣዊ ቤተሰብ አንድ ልዑል በመወለዱ ምክንያት በጄነራል ግራዚያኒ ትዕዛዝ በቀድሞው የገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት (የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጽር ግቢ ከተሰበሰቡት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፤ ለፋሺስቶቹ ያደሩ ከሀዲ ባንዳዎችና መኳንንት፤ የፋሺስት ባለ ሥልጣናት ወታደሮች በተሰበሰቡበት መኻል፣ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የእጅ ቦምብ ወርውረው አደጋ ሲጥሉ ግራዚያኒን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ተጎድተዋል። ይኸንን ድርጊት በመበቀል ሰበብ እዚያው ግቢ ውስጥ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተጨፈጨፉ፤ ቀጥሎም የተማሩ ወጣቶች፣ የጦር መኮንኖችና ካህናት፣ የደብረ ሊባኖስ መነኮሳት በሙሉ እየተለቀሙ ተጨፈጨፉ። የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በቤት ውስጥ እያስገቡ ከውጭ ቆልፈው ቤንዚን እያርከፈከፉ አቃጠሉአቸው። በአካፋ፣ በዶማ፣ በመጥረቢያ በተገኙበት ኢትዮጵያውያንን እየቆራረጡ የደም ጎርፍ አወረዱ። ፋሽስቶች የአዲስ አበባንና የአካባቢውን ሕዝብ በጅምላ ጨፈጨፉት። በሶስት ቀናት ፴ሺህ ሕዝብ መስዋዕትነት ተቀበለ።
  • ፲፱፻፸፩ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢቲ-ኤ-ኤፍ ደብልዩ (ET-AFW) ዲሲ ፫ (Douglas C-47B-10-DK፤ በደቡብ-ምዕራብ ኤርትራ በምትገኘው ባረንቱ ላይ በቦምብ ፍንዳታ ተከስክሶ ሲወድቅ አምስቱም ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። አየር ዠበቡም ከጥቅም ውጭ ሆኗል።

የካቲት ፲፫
የካቲት ፲፬
የካቲት ፲፭
የካቲት ፲፮
  • ፲፱፻፳፱ዓ/ም - በግራትዚያኒ የሚመራ የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት በዝዋይ አካባቢ የጦር አዝማቾቹን የራስ ደስታ ዳምጠውን እና የደጃዝማች በየነ መርድን አርበኞት ድል አደረጉ። ሁለቱም ኢትዮጵያውያን አዝማቾች ሕይወታቸውን በዚህ ዕለት ሰዉ። ኢጣሊያውያኑ ራስ ደስታን ከያዟቸው በኋላ በጥይት ደበደቧቸው፡፡
  • ፲፱፻፷፮ዓ/ም ኢትዮጵያ ላይ በፈነዳው አብዮት አስገዳጅነት የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የሕዝቡን ሸክም ለማቃለል የነዳጅ ዋጋ ቅነሳን የሚያካትት ኤኮኖሚያዊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ይፋ አደረገ።
  • ፲፱፻፳፱ዓ/ም - የግራዚያኒ ሠራዊት በአሩሲና በማረቆ ላይ ትልቅ ጦርነት አድርጎ፣ ራስ ደስታ ዳምጠው እና አብረዋቸው የነበሩትን የጦር አለቆች ማርኮ በዚህ ዕለት በፋሺስቶች እጅ ተገደሉ።
የካቲት ፲፯
  • ፲፱፻፷፭ዓ/ም - ቴኔኮ የተባለ የአሜሪካ ኩባንያ በኦጋዴን ግምቱ ፸፮ ቢሊዮን ሜትር ኩብ የሆነ ሰፊ የተፈጥሮ ነዳጅ (ጋዝ) እንዳገኘ አስታወቀ።
  • ፲፱፻፷፮ዓ/ም - ኢትዮጵያ ላይ በፈነዳው አብዮት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ በልዕልት ፀሐይ ሆስፒታል አካባቢ ተኩስ ተከፈተ። በዚሁ ዕለት የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ለወታደሮች የደሞዝ ጭመራ ለማድረግ መወሰኑን አስታወቀ።
የካቲት ፲፰
የካቲት ፲፱
የካቲት ፳
የካቲት ፳፩
የካቲት ፳፪
የካቲት ፳፫
የካቲት ፳፬

የካቲት ፳፭

የካቲት ፳፮
የካቲት ፳፯
  • ፲፱፻፵፱ዓ/ም - ጎልድ ኮስት ትባል የነበረችው የብሪታንያ ቅኝ ግዛት ጋና ተብላ ነጻ ሆነች። (በወቅቱ ከኢትዮጵያና ከላይቤሪያ ውጭ የመጀመሪያዋ ነጻ አገር መሆኗ ነው።)
የካቲት ፳፰
*****
የካቲት ፳፱
የካቲት ፴
(ወርሐ ግንቦት ይቀጥላል)
ምንጭ https://am.wikipedia.org/wiki/

ሳቢና ተሳቢ


አዛምድ አሉ "ቲቸር" ፈረንጁ መምሬ
አዛመድኩላቸው እኔም ጨማምሬ
ሰኔን ከሰኞ፣ ግንቦትን ከየካቲት
ወንፊት ከውኃ፣ ቤንዚንን ከእሳት
ጋንጩር ከደብተራ፣ እንጀራ ከወጥ
እጅ መንሻ ለባሻ፣ አስክሬንና ምስጥ
ሌባ ላመሉ ላይቀር መላሱ
ዓይንም ላፍንጫ ማልቀሱ
ያው አይቻል ነገር 
አዲስ ማቀናበር
ከእባብ እንቁላል እርግብ ማስፈልፈል
ዝንጀሮን እርሻ ትቶ በሬን ለቆ በገደል
ዱባና ቅል ያለ ጠባዩ አይበቅል
የመጥረቢያ ልጅ መዘለፊያ
ፈረስና ግልቢያ አህያና ልፊያ
ዶሮና ጥሬ እጅና አፍ ላይተላለፍ
አይጥና ድመት እርም ላይደጋገፍ
ሰኔ ብሎ ሰኞ የካቲት ብሎ ግንቦት
"ቲቸር" ቢፈልጉ ኤክስ ነው ይበሉት
እርስዎ በገዛ ራስዎ ያው በሚያውቁት
ሳቢና ተሳቢን አዛምድ ነው ያሉት
የካቲት 22፥ 2019 ዐርብ ማለዳ

ብሩክ በ.