Thursday, July 26, 2018

አድራሻዬ ይኸውና !

አድራሻዬ ይኸውና !

ተመቃብሬም ዘንድ አትድረሱ
ነፍሴ ታውቃለች የለሁም በሱ
በገጾች መካከል መጽሐፍ ገልጣችሁ
አትሮንስ ዘርግታችሁ፣ መዛግብት አገላብጣችሁ
ሰነድ መርምራችሁ ፈልጉኝ ታገኙኛላችሁ።
ከሰዎች አንደበት ላይ ንቅሳት ሆኜያለሁና
እኔም ላገሬ ውለታዋን ከፍያለሁና
አሮጌው ተማሪ ቤቴ እኔን ፍለጋ አትሒዱ
ተአሮጌው ቤቴ እንዳታንጎዳጉዱ
ምሥጢሬ ታደባባይ ወጥቷል ጉዱ
ታውቁኝ ተነበረ ቦታም አትፈልጉኝ
ዛሬ ደከመኝ መሰለኝ ሌላ ገደብ አሰኘኝ
ሰው ነኝና ድንገት ፥ ደከመኝ መሰለኝ
እና ፥ እና ዛሬ ፥ ዛሬ እና
በሰዎች ልብ ውስጥ እነሆ ተኝቼያለሁና
የፈለገኝ ይምጣ አድራሻዬ ይኸውና !

መታሰቢያነቱ ለኢንጀነር ስመኘው በቀለ የሕዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ በዕለተ ዕርገታቸው ሐምሌ 19 ፥ 2010

ብሩክ በየነ

መነሻ ሐሳብ

“Do not go to my grave. 
Mary knows, I am not there. 
Look for me in between pages 
and on people’s lips.
Do not go to my old school. 
Do not go to my old house —
I am not in any of those places. 
Look for me in your hearts 
and greet me there.” 
― Kamand Kojouri

No comments:

Post a Comment