ሁሉም ነገር እርስ በርሱ የተገናኘ ነው
Everything is interlinked
The
issue we will be focusing this week is "everything is interlinked: how far
is this true?"
የዚህ ሳምንት ርእሰ ጉዳያችን የሚያተኩረው "ሁሉም ነገር አንዱ ከአንዱ ጋር የተሰናሰነ (የተገናኘ፣ የተሳሰረ) ነው" የሚባል ነገር አለ። እናም ይህ ምን ያክል እውነት እንደሆነ እንመረምራለን። ምን ሐሳብ መጣላችሁ?
የዚህ ሳምንት ርእሰ ጉዳያችን የሚያተኩረው "ሁሉም ነገር አንዱ ከአንዱ ጋር የተሰናሰነ (የተገናኘ፣ የተሳሰረ) ነው" የሚባል ነገር አለ። እናም ይህ ምን ያክል እውነት እንደሆነ እንመረምራለን። ምን ሐሳብ መጣላችሁ?

ትኩረት አቅጣጫ ፩
"ሁሉም ነገሮች ምክንያቶችና ሁኔታዎች አንድ ላይ በአንድ ወቅት በአንድ ቦታ የሚከሰቱ እንደመሆናቸው አንድ ጊዜ ባንድ ቦታ አንዴ ይከሰቱና ደግሞ መልሰው አንድ ላይ ባንዴ ይጠፋሉ። ምንም ነገር ብቻውን በምድር ላይ ተከስቶ፣ ብቻውን ኖሮ አያውቅም፤ እያንዳንዱ ነገር ከእያንዳንዱ ሌላ ነገር ጋር የሆነ ዝምድና አለው።"

ምክር ወተግሣፅ
፩
ሁሉም ነገር ለበጎ ነው። አንዳችም ነገር ያለ ምክንያት አልተፈጠረም። በፀጋ ተቀበልና ኑርበት፣ ተማርበት !

ትኩረት አቅጣጫ ፪

አንድ ሰው ሙሉእ ስብእና እንዲኖረው እነዚህን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ገላጭ ባሕሪያት ሁሉ ማሟላት ይጠበቅበታል።
መጠናቸው በበዛ ቊጥር መለካታዊ ባሕሪው እያመዘነ የሚሔድ ሲሆን የነዚህን ባሕሪያት መጠናቸው ባነሰ ቁጥርና ተቃራኒው ባሕሪያቸው
በሰው ልጅ ላይ ሲሠለጥን የሰው እንስሳዊ ባሕሪያው እያየለ ይሔዳል።
የሙሉእ ስብእና መገለጫ ባሕሪያት፦
ፍቅር (Love)፣ ቅንነት (Openness)፣ ውዴታ (Passion)፣ ሰላም (Peace)፣ ፅኑእነት (Persistence)፣ ፈቃድ (Purpose)፣ ርጋታ (Serenity)፣ መንፈሳዊነት (Spirituality)፣ ብርቱነት (Steadfastness)፣ ድምቀት (Tenderness)፣ ሚዛን (Balance)፣ አንደበተ ርቱዕነት (Clarity)፣ በራስ መተማመን (Confidence)፣ ፈጠራ ችሎታ (Creativity)፣ ጉልበት (Energy)፣ ሃይማኖት (Faith)፣ ይቅር ባይነት (Forgiveness)፣ ነጻነት (Freedom)፣ አመስጋኝነት (Gratitude)፣ ግርማ ሞገስ (Grace)፣ ትሁትነት (Humility)፣ እውነት (Truth)፣ እምነት (Trust)፣ ሐሴት (Joy)፣ ተማሪነት (Learning)፣ ተንከባካቢነት (Nurturance)፣ ሥነ ምግባር (Morality)፣ መሻት (Objectivity)፣ ቀና አሳቢነት (Optimism)፣ ትዕግስት (Patience)፣ ተጫዋችነት (Playfulness)፣ ችግርን ተቋቋሚነት (Resilience)፣ ቀላልነት (Simplicity)፣ የአቋም ፅኑነት (Stability)፣ ጥንካሬ (Strength)፣ ተስፋ (Hope)፣ ሕያውነት (Vitality)፣ ቅቡልነት (Acceptance)፣ አለመናወጥ (Assertiveness)፣ ውበት (Beauty)፣ ቸርነት (Compassion)፣ ድፍረት (Courage)፣ የማወቅ ጉጉት (Curiosity)፣ ተነሣሽነት (Enthusiasm)፣ ግትር አለመሆን (Flexibility)፣ ኃይልነት (Fortitude)፣ ደግነት (Generosity)፣ ጨዋነት (Gentleness)፣ ስምም ለዛ (Harmony)፣ ጥንቁቅነት (Carefulness)፣ ቻይነት (Tolerance)፣ ርህሩህነት (Kindness)፣ ወጥነት (Integrity)
ምክር ወተግሣፅ ፪
እያንዳንዱ የምናደርገው ነገር ሁሉ ባንድ ሆነ በሌላ ምክንያት አሉታዊ ወይም አዎንታዊ ተፅዕኖ በሌሎች ላይ ያሳርፋል።
ሞተን ሥጋችንን ለምስጦች ኅልውና የምንገብረውን ያክል የምንሠራው ሥራ ሁሉ በሌሎች ትውልዶች ላይ ተፅዕኖ ሊያሳርፍ ይችላል። በዚህም
አሊያም ሊያመሰግነን ወይም ሊያስወቅሰን ይችላል።

ጆአን ውልፍጋንግ ቮን ጎቴ እንዲህ
ይለናል፦
በተፈጥሮ ውስጥ ምንም ነገር ብቻውን
ተነጥሎ አናየውም፤ ይልቁንስ እያንዳንዱ ነገር ከሆነ ከእርሱ በፊት፣ ከእርሱ ጎን ለጎን፣ ከእርሱ ሥር እና ከእርሱ በላይ ካለው
ሌላ ነገር ጋር የተገናኘ ነው።

ምክር ወተግሣፅ ፫
ለዚህም ነው መሰል ኦሊቨር ቬንደል ሆምስ አንድ ሰው ሙሉእነት እንዲኖረው በማሰብ የሚከተለውን ምክሩን ጣል ያደርጋል፦
« አእምሮው ብልህ የሆነ ግለሰብ ማግባት ያለበት ዓመለ ከይሲ የሆነን ግለሰብ ነው ። »

ትኩረት አቅጣጫ ፫
ሁሉም የበላይ አለው። ሁሉም የበላይ
ተቆጣጣሪ አለው።

ዓለም ከ3.8 ቢሊዮን ዓመታት በፊት
ስትፈጠር ሁሉም ለዛሬው ጊዜ ሆነ ለመጪው ጊዜ የሚያስፍልጋትን አሟልታ ይዛ መፈጠሯ አጃይብ የሚያሰኝ ሰማያዊ ምሥጢር ነው።

አፍንጫ ሲመታ ዓይን ያለቅሳል ለካ ይባላል። ለምን ? ምክንያቱም ሰውነታችን እርስ በርሳቸው
የተያያዙ ነገሮች ውህድ ነው። ይህ ብቻ አይደለም ሁሉም ነገሮች መንትያ አላቸው። ሁለት ዓይኖች፣ ሁለት በአንድ ጭንቅላት ላይ የገጠሙ
አንጎሎች፣ ሁለት ጆሮ፣ ሁለት ሳንባ፣ ሁለት ባንድ የገጠመ ልብ፣ ሁለት ኩላሊት፣ ሁለት አንጀት (ቅልቁና ትንሹ አንጀት)፣ ሁለት
እጅ፣ ሁለት እግር ወዘተ። አንዱ ያላንዱ መኖር ቢችልም የአንዱ ጉዳት ሌላው ላይ ጉዳትን ያመጣል።

ትኩረት አቅጣጫ ፬
አገሮች ራሳቸው ልክ
እንደ ሰው በምክንያት ተስተካክለው የተፈጠሩ ናቸው። ለአብነት ከአገሮች ሁሉ ሩሲያ በምክንያት ከሁሉም አገሮች ይልቅ ግዙፍ ነች።
በአጭሩ ሩሲያ እንደ እንስሳ ብትታይ ሩሲያ ማለት ድብ ነች። ግዙፍ። (ድብ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም። ከ20ኛ
ክፍለ ዘመን (1900) ወዲህ የተፈጠረ ቃል ይመስለኛል።) ካርታ ዘርግተን ወይም ሉል እያሸከረከርን ስናይ ሩሲያን በሁሉም የዓለም
ክፍሎች ላይ ማየት እንችላለን። ሩሲያ በአላስካ በኩል የአሜሪካ ጎረቤት ነች ! ታዲያ ይህን የምታክል ግዙፍ አገር በሚጢጢዋ ፓላንድ
ኅልውና ላይ የተመረኮዘች ነች። ፖላንድ ከሌለች ሩሲያ የለችም ማለት እስከሚቻል ደረጃ ድረስ። እንዴት እንደዚህ ሊሆን ይችላል ?
Amazing Russia, It is
everywhere in the world: east, west, north and south. However if tiny Poland is
removed, then this huge country disappears altogether. Why?

ኤብሉዌ ፎክስ የተባለ ጦማሪ ይህን ሁሉም ነገር የተገናኘ ነው የሚለውን ዓርፍ ነገር
በተመለከተ ሲፅፍ እንደሚከተለው ይለናል፦
ይህን ጉዳይ በምፅትና በቀናነት በተሞሉ ቃላት እገልፀዋለሁ። “የሁሉም ነገሮች መገናኘት ሕግጋት፤
በርግጥ በተፈጥሮ እና በሳይንስ ውስጥ ያሉ ሁሉም ነገሮች ባንድ ወይም በሌላ መልኩ የተገናኙ ናቸውን?
በቀላል አነጋገር አዎ። ሁሉም የሰው ልጅ ሊደርስበት የሚችለው ሕዋና የሕዋ አካል በሙሉ በኩዋርኮች (Quarks) እና ጉሎንስ (Gluons) የሚባሉ ንጥረ ነገሮች የተሠራ ነው። ይህ ላንተ በቂ ማስረጃ ሊሆንህ ካልቻለ ግን ኳንተም ፊዚክስን
መመልከት ትችላለህ። ሕዋ (universe) ያለምንም ጥርጥር ራሱን የቻል እርስ በራሱ
የተገናኘ ሳይንስ ነው።
ይህንን ፅንሰ ሐሳብ ትክክል እንዳልሆነ የማረጋግጥበት ምንም ዓይነት ማስረጃ የለኝም። በመሆኑም ደስ
ብሎኝ ይህንኑ ራሱ ከላይ የጠቀስኩትን ሕግ እንደ ተጨባጭነት ያለው
ሕግ አድርጌ እቀበለዋለሁ። እውነት ላይሆን የሚችልበት ብቸኛ አማራጭ አንድና አንድ ነው። እሱም እስካሁን የሰው ልጆች ስንታዘበው
ከኖርነው ውጭ የሆነ ባሕሪያት ያሉትን አዲስ ነገር ያገኘን እንደሆነ ብቻ ነው።
ሊዮናርዶ ዳ ቬንቺ ፦
ተፈጥሮ የሁሉም እውነተኛ ዕውቀት ምንጭ ነች። የራሷ የሆነ ሥነ አምክንዮ፣ የራሷ የሆነ ሕግጋት አላት።
ያለምንም ምክንያት የሚሆን ነገር የላትም። ያለምክንያትም ምንም የተፈጠረ አዲስ ነገር የለም።

ትኩረት አቅጣጫ ፭
የአይጥና የወፎች እከክኝ ልከክልህ ዝምድና
ባለፈው በኅዳር ወር መጨረሻ ወደ ባሌ ሔጄ ሳለሁ ያስተዋልኩትና ጠይቄ የተረዳሁት አስገራሚ የተፈጥሮ ነገር ነው። ባሌ ያለው ቀይ ቀበሮ በዋንኛነት ምግቡን በመሬት ውስጥ ጉድጓድ ሠርተው የተደበቁትን አይጠመጎጦች አድኖ በመብላት ላይ የተመረኮዘ ነው። ታዲያ የሜገርመው ነገር፣ ይኼ ቀይ ቀበሮ አይጦቹን እንዳይበላ በከፍተኛ ደረጃ የሚቃወሙትና ለአይጦቹም ቀይ ቀበሮ እንደመጣባቸው ምልክት እየሰጡ ከጉድጓዳቸው እንዳይወጡ ምልክት የሚሰጡዋቸው በአካባቢው ያሉት ወፎች ናቸው።
ምክንያት፦
አይጦቹ ጉድጓዳቸውን ሲቆፍሩ ለወፎቹ ትላትሎችን ከመሬት ውስጥ እያወጡ ቀለባቸውን ስለሚያስቀምጡላቸው።
አይጦቹ ጉድጓዳቸውን ሲቆፍሩ ለወፎቹ ትላትሎችን ከመሬት ውስጥ እያወጡ ቀለባቸውን ስለሚያስቀምጡላቸው።

“I like this place and could willingly waste my time in
it.”
― William Shakespeare
"ይኼ ቦታ ደስ ብሎኛልና ያለምንም ቅሬታ በደስታ ጊዜዬን እዚህ ላጠፋው እችላለሁ።"
ዊሊያም ሼክስፒር
― William Shakespeare
"ይኼ ቦታ ደስ ብሎኛልና ያለምንም ቅሬታ በደስታ ጊዜዬን እዚህ ላጠፋው እችላለሁ።"
ዊሊያም ሼክስፒር





ትኩረት አቅጣጫ ፮
አእምሮዋችን በምናብ ሕዋን ሊወክል ይችላል።
Our mind can vicariously represent the universe.




ትኩረት አቅጣጫ ፯
አእምሮዋችን በምናብ ሕዋን ሊወክል ይችላል። ሴልና ፕላኔቶችን ልብ ይሏል። እኛ ልክ እንደ
አንድ ሴል ነን ፥ በሕዋ ውስጥ
ስንታይ።
Everything is interconnected. Our
mind can vicariously represent the universe. Consider the "cell" and
the "planets".
We are as tiny as the cell when we're seen from the prospective of the
universe.




ትኩረት አቅጣጫ ፰
ሳንባችን እና ዛፍ አንድ ናቸው።
Our
lungs are the same as tree.


ትኩረት አቅጣጫ ፱
የላቲን አሜሪካው አማዞን ደን፣ የአፍሪካው ትሮፒካል ደን፣ የአውስትራልያ የባሕር ዛፍ ደን፣ የኒካራጉዋ የጥድ ደን፣ እና የደቡባዊ ምሥራቅ ደኖች የምድር ሳንባዎች ናቸው
The Amazon forest, the African
Tropical forest, the Australian eucalyptus forest, the Nicaraguan coniferous
forest, and the south east Asian forest are the lungs of the world.


ትኩረት አቅጣጫ ፲
ይኼ ገና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ላይ የተማርነው የምግብ ሰንሰለት በራሱ አንዳችን ያላንዳችን እንደማንኖር ያረጋግጣል።
This food chain pyramid that we
learnt while in elementary school has its own say about our inter-dependency to
live in this planet. We live concomitantly whether we like or not.


ትኩረት አቅጣጫ ፲፩
ዋናው በምድር ላይ ያለው ኦክስጂን ምንጭ ውቅያኖሶች ናቸው። በዓለም ላይ ካለው 50 በመቶ የሚሆነው ኦክስጂን የሚገኘው ከውቅያኖሶች ነው። አብዛኛው የምድር ኦክስጂን ፓይቶፕላንክቶን (phytoplankton) ከተባሉ ጥቃቅን በውቅያኖስ ውስጥ ከውሃው አካል ላይ ሞገዱ ላይ ከሚገኙ ተክሎች የሚመነጭ ነው። ሌላ ምን ነገሮችስ ኦክስጂንን ሊያመነጩ ይችላሉ? ማናቸውም ፎቶሰንተሲስ የሚጠቀም ነገር ሁሉ ኦክስጂንን ይፈጥራል! ይህ ማለት ሣሮች፣ ዛፎች፣ አበባዎች፣ ቁጥቋጦዎች፣ እና ሌሎች ሁሉም ዓይነት ተክሎችና ዕፅዋቶች ኦክሲጂንን ያመርታሉ። እንዲህ ነው እንግዲህ የምንተነፍሰውን ኦክስጂን የምናገኘው!
The major
source for oxygen on earth is Ocean. Nearly more than 50% of the oxygen comes
from ocean. Most of Earth’s oxygen comes from tiny ocean plants – called
phytoplankton – that live near the water’s surface and drift with the currents.
What other types of things might be producing oxygen? Anything that uses
photosynthesis! This means that grass, trees, flowers, bushes, and all of the
other plants are producing oxygen. That's where the rest of the oxygen comes
from!




ትኩረት አቅጣጫ ፲፪
በአርክቲክ፣ አንትራክቲካ፣ በውቅያኖሶች፣ በባሕር ዳርቻዎች፣ በትላልቅ እንደ ሂማሊያና ኪሊማንጃሮ፣ ራስ ደጀን ( ቱሪስት ተሳስቶ ስለጠራው አሁን ራስ ዳሽን የሚባለው) ከመሳሰሉ ተራሮች በረዶ እየቀለጠ ውሃ፣ ወንዝ ይሆናል። ውሃ ደግሞ ሕይወት ነው !
Water in particular, rivers in general are created or supplied
with water when icebergs from the Arctic, Antarctica, oceans, the seas, from
mountain summits like Himalayas, Kilimanjaro, Ras Dejen (distorted form created
by a tourist, which is now widely accepted and used as Ras Dashen). Water is
life and we get it from icebergs of course.




ትኩረት አቅጣጫ ፲፫
ተክሎች ደግሞ ውሃ ከዝናብ፣ ከወንዞች፣ ከመስኖ ወዘተ ያገኛሉ።
Plants get water from rain,
rivers, irrigation etc.





ትኩረት አቅጣጫ ፲፬
ሣርና ቅጠል በል እንስሳት ደግሞ ምግባቸውን ከተክሎች ያገኛሉ።
ሣርና ቅጠል በል እንስሳት ደግሞ ምግባቸውን ከተክሎች ያገኛሉ።
Herbivorous animals feed
themselves from plants.



ትኩረት አቅጣጫ ፲፭
ሰውና ሥጋ በል እንስሳት ደግሞ ቅጠልና ሣር
Humans and carnivorous
animals get their food from the herbivorous.



ትኩረት አቅጣጫ ፲፮
በቀን 24 ሺ ጊዜ እንተነፍሳለን
በቀን 24 ሰዓታት አሉ
በቀን 24 ሰዓታት አሉ
We breathe about 24 000 times a day.
There are 24 hours a day


ከሣቴ ብርሃን
ቡሩክ
አዲስ አበባ
ነሐሴ 28 (ዕለተ አማኑኤል)፥ 2018 (በራስ አቆጣጠር)
Brook
Beyene
Addis
Ababa, September 3, 2018