ፈራን
ወፍ እንደ ዘራው እህል በየሜዳው ፈራን
እንደ አረም እንደ ግራዋ በየጥጉ በቀልን
እንደ ፍል በየስርጓጡ ፈላን
እንደ አረም ፍሬ ፈርተን
ተንሰራፋን ፈራን
ግን፣ አንድ ቀን
ማናችሁ ሲሉ ማን እንላለን
ዛሬን ነው እንጂ ትናንትን
የት እናውቃለን
ብናውቅስ ምን እናመጣለን
አላችሁ ሲሉን
እየፈራን አለን እናላለን
ፈርተን እናፈራለን
በየፈሩ እንፈራለን
እኛ የጉድ ፍጡር ነን
ዝምብለን የፈራን
ጥር ሦስት፣ 2018 ዐዲስ ዐበባ